ካርቱም ለምትገኙ ስደተኞች በሙሉ – በሱዳን የሚገኙትን 5ቱን የወያኔ ሰላዮች/ ተላላኪዎች ይወቁ

August 31, 2014

በሱዳን ከሚገኙ ሃገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን የተላለፈ ጥሪ፦

በሱዳን ሀገር ለምትገኙ ኢትዮጽያውያን በሙሉ መብታችን ሰብአዊ ክብራችን ለዘመናት በስደት በምንኖርበት ሀገረ ሱዳን በ ዩን ኤች ሲ አር በኩል ከፍተኛ አድሎ በደል እንደሚደረግብን ለማንም ግልፅ ነው። ይሂም የኛ ዝምታና አንድነት አለመኖር እረሳችንን እንደጎዳን በማንም ይታወቃል በሕብረት በአንድነት ቆመን መብታችን ለማስከበር እንዳንታገል ያደረግን የወያኔ ረቂቅ ተንኮል መሆኑ ለማንም ግልፅ ነው። ይህንን አሳዛኝ ሕይወት ማንም በየቤቱ ይናገራወል በቅርብ በሚያውቀው ጓደኛ ጎረቤት ይወያይበታል የስደተኛ መብታችንም እንዳናስከብር እንደኛው የስደተኛ መታወቂያ የያዙ ለረዥም ዓመት በጉርብትና በመሀበር በእድር የምናውቃቸው ሁለት አይነት መታወቂያ ያላቸው እስስት ሰላዮችን ስደተኛው ማህበረሰብ በይሉኝታ እስከ ዛሬ በዝምታ ሲያልፋቸው ኖረዋል። እነሆ እሰከ ዛሬ የስደተኛ መብታችን ከመጋራት አልፎ እኛን መስለው ሲሰልሉን እያየን እየሰማን አንድ ለአምስት በሚባል በስለላ ስራ ተሰማርተው በቤተክርስትያን በእድር በጉርብትና በየፀበል ፀዲቁ በዩ ኤን ኤች ሲ አር በኮር ስደተኛው በሚገኝበት በስውር ተመድበው ሰርገው በመግባት በከፍተኛ ደረጃ እየተንቀሳቀሱ ይገኛሉ። እነዚህ ከሀዲ ባንዳዎች ሰርቶ የሚኖረውን ስደተኛ እለት በእለት እየተከታተሉ ለወያኔ ኢንባሲ ዘርፈው ለማይጠግቡ ኢትዮጽያን ሸጠው ለማይረኩ ቅጥረኞች ማንኛውንም እንቅስቃሴ ሪፖርት ያደርጋሉ። ከዚህ በኋላ ዝምታችን ሰብረን ዝምታ ለበጓም አልባጃት እንዲሉ ከዚህ በታች ስማቸው የተዘረዘሩትን ወራዳ እንደ ሚሸጥ ስጋ ምንግዜም እራሳቸውን በፍርፋሪ የሚሸጡ በፍፁም ኢትዮጽያዊ ክብር
የለላቸውን በስደተኛ ስም ስደተኛ ነን የሚሉትን ከሀዲ ባንዳዎችን ከዛሬ ጀምሮ በካርቱም በተለያዩ ቦታዎች በበሀሪ በእምድሩማን በጅሬፍ በሰሀፋ ሸሪክ በሰሀፋ ዘለጥ በጀብራ በጎዝ በዴም ውስጥ የሚገኙትን ተራ በተራ እናጋልጣለን ለግዜው።……..
የካርቱም ከተማ ከፊል ገጽታ (ፎቶ ፋይል)
1ኛ. አየልኝ ተድላ መኮነን (ኰከቤ)፡− ይህ ግለሰብ በ2005 የተቋቋመው የስደተኞች ኮሚቴ ውስጥ አባል ሆኖ እየሰራ እያለ በኮሚቴ አባላት መካከል ጠንካራ እንቅስቃሴ ያደርጉ የነበሩትን ወያኔ ሆነዋል ብሎ በማስወራትና ክፍፍል በመፍጠር ኰሚቲው እንዲፈራርስ ትልቅ ሚና ተጫውቶዋል። በዚህ ሳይቆም ከኢትዮጵያ ሸሽቶ የመጣ አንድ የግንቦት 7 ዓባል አቶ አንዱአለም የተባለ ሰውየ እዚህ ካርቱም እንዲታፈንም ከፍተኛ አስተዋጾ ካደረጉት ሰዎች አንዱ ነው። COR እና UNHCR ሲሄድ ተቃዋሚ መስሎ የሚቀርብ በተግባር ግን የወያኔ ቅጥረኛ የሆነ ግለሠብ ነው።

2ኛ. ወርቁ አለባቸው (ባሪያው) ፡− ግለሰቡ የወያኔው የማፍያ ቡድን መሪ የነበረው የመለሰ ዜናዊ የሃዘን ቀን በሚከበርበት ቀን የሟቹን ፎቶ ይዞ ምሾ ሲወርድ እና ያዙኝ ልቀቁኝ ሲል ባጋጣሚ ፎቶው ይቀደዳል ወያኔ ለመሆን ይረዳኛል ብሎ ያሰበው እለቅሶ ወያኔ በሆኑት ሆን ብለህ ነው የቀደድከው አንተ ሆዳም ዓማራ ተብሎ ተዋረደ እና ተደበደበበት። ከዛን ቀን በሆላ ጠቅልሎ እንደገባ በአደባባይ አስመሰከረ።

3ኛ. ተስፉ የሽወንድም ፡− በዘመነ ደርግ በጎንደር ውስጥ በኢሰፓ ውስጥ ሲሰራ የነበረ ሲሆን ስደት ከገባበት ጊዜ ጀምሮ በየሄደበት ወሬ በመለቃቀም ለኢንባሲው የሚያቀብል አደገኛ ወሬ አነፍናፊ የሆነ ግለሰብ ነው።

4ኛ. ሽዋየ ሲሳይ ፡− በባሏ መሞት አማራነቷን ያወቀችው ቀዳማዊ ዕመቤት እየተባለች ስትሞካሽ የነበረችው አዚብ መስፍን ሱዳን ስትመጣ በቤቷ ተቀብላ በማስተናገድ ብቻ ሳትወሰን የስለላም ስራ በመስራት ሪፖርት የምታቀርብ ናት።

5ኛ. መኪ ጉራጌው ፡− በመባል የሚታወቀ ኦምዱሩማን የሚኖር ይሂው ግለሰብ ኦምዱሩማን የሚኖሩ ስደተኞችን በማማበል ስደተኞች በኢንባሲው ውስጥ በተዋቀረው እድር እንዲሳተፉ እና የተለያየ ጥቅማጥቅም እንደሚያገኙ በማሳመን የአባላት ምልመላ ያካደርጋል። እግረመንገዱንም ለኢምባሲው በመሰለል መረጃ ያቀብላል።

ወድ ኢትዮጽያዊ እነዚህ ለሆዳቸው ያደሩ አሳልፈው እንደሰጡህ ይታወቃል ሌሎችም አንድ ለአምስት በሚል በወያኔ የስላላ መረብ የተጠረነፉ እንደተለከፈ ውሻ በየስደተኛው ቤት የሚክለፈለፉ በአማራ በትግሬ በኦሮሞ በጉራጌ በደቡብ መሀበራት ስም የተደራጁ እንዳሉ ይታወቃል እነዚህ ወገን ሀገርን የሚሸጡ ደላለዎችን በማንኛውም መልኩ ከማንኛወም ማህበራዊ ግንኙነት እንዲገለሉ ማድረግ አለብን። ከአሁን በሆላ በስደተኛው ስም መነገድ እንዲያቆሙ ልንነግራቸው ይገባል። እንደማይራሩሉልህ ይታወቃልና ስለዚህ በይሉኝታ መብታችን ና የኢትዮጽያን ክብር ከአሁን በፊት አሳልፈን የሰጠነው ይብቃል እንበላችው ! በጋራ እንዋጋቸው !!!

ይህንን በረሪ ወረቀት ኮፒ እያደረክ ያላነበበው እንዲያነበው ትብብርህን አንጠይቃለን !
ለመብትህ ለክብርህ ተነስ !!!

1 Comment

 1. የኢንተርኔትና የፊስቡክ ሜዲያ የሽንት ቤት ግድግዳ አይደለም!!
  አልበርታንስታይ የኒኩለርን ቀመር ሲፈለስፍ ለጦር መሳሪያ ይሆናል ብሎ አልነበረም። ሩሲያዊው ሻለቃ ከላሽንኮቭ፣ ኤኬም 47 የሰራው ሩሲያን ከጀርመን ወረራ ለመከላከል እንጅ ይሄን ያህል በአለም ላይ ተበትኖ ለሰው ልጆች መግደያ መዋሉን ባውቅ ኑሮ ከመጀመሪያው አልሰራውም ነበር ሲል በጸጸት ገልጿል። አሁንም ፌስቡክንና የኢንተርኔትን ሶሻል ሜዲያ የፈጠሩ ሰወችም ከወዲሁ መላ ካላበጁለት፣ ማንም ባለጌ የትም ተደብቆ የሰው ልጆችን ማጥፌ ካዋለው ከጥቅሙ ማይተናነስ ችግር መፍጠሩ አይቀሬ ነው።
  ከላይ ምታዩትን ጽሁፍ አቅራቢወች እኔ ከምኖርበት ሱዳን ውጭ ኗሪ መሆናቸውን ራሱ የጽሁፉ ርእስ ይናገራል። እናም ማን እንዲህ ሊያደርግ ይችላል? ሚለውን ጎረቤት ከጓደኛና ከአካባቢ ሊኖረኝ ይችል የነበረውን ጥርጣሬ አስወግዶ ትክክለኛውን ጠላቴን ለይቸ እንድውቅ አድርጎኛል።ከሳሾቸ ኮከብ ተድላ በቁጥር አንድ የወያኔ ቅጥረኛ ነው፣ ብለው አምባቢን ለማሳመንና ሰወች ከኔ እንዲርቁ ለማድርግ ቢቻለ አንድ ሁለት ብለው፣የተወሰነ ማስረጃ ማቅረብ ነበረባቸው።ያለዚያ ደግሞ ማንነታቸውን(ስማቸውን) ግልጽ ማድረግ ተገቢ ነበር። ምክንያቱም እነኝህ ሰወች ከግል ቂምና ጥላቻ ተነስተው የኔን ስም ለማጥፋት የደፈሩትን ያህል በግልጽ ቀርበው፣አዎ! ኮከብ ተድላ ወያኔ ነው” ብለው ለመከራክር ቢደፍሩ ኑሮ፣እነሱንም እኔንም ሚያውቁ ሰወች፣ ከየግል ስብእናችንና የጀርባ ታሪካችን ተነስተው በአንዳችን ላይ መፍረድ ያስችላቸው ነበር።
  ስለሆነም እንዲሁ በግል ቁርሾ ተነስቶ የሰውን ስም ማጉደፍ እንዲሁ ተራ የማስታወቂያ ስራ ስላልሆነ፣ አምባቢያን ከላይ ስለኔ የቀረበውን የሃሰት ውንጀላ መሰረተቢስነት ከዚህ አኩያ ተረድተው አስተያየት እንዲሰጡበት በትህትና እጠይቃለሁ!! በተረፈ ከልይ ስም አጥፊው የደደቦች ቡድን እንደ ክስ ባቀረባቸው 3 ነጥቦችን ግልጽ ማብራሪያ ልስጥና በሚቀጥለው ዘ-ሃበሻ ጋዜጣ፣ ስለነኝህ ሰወች ማንነት ዘርዝር መረጃ ይዠ እስክመለስ ትንሽ ተናግሬ ላብቃ።
  1ኛ=ኮከብ ተድላ በስደተኛው ኮሚቴ ውስጥ ሳለ ኮሚቴውን ለመከፋፈል ሚና ተጫውቷል የሚል ነጥብ ተነስቷል፣ በቅድሚያ ስለራሴ እንዲህ ነበርኩ ብየ ለማውራት ፈልጌ አልመሆኑን እንዲታወቅልኝ እፈልጋለሁ።እኔ በስደተኛው ኮሜቴ ውስጥ መኖር ብቻ ሳይሆን፣ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻ የኮሚቴው ሊቀመንበር እንደነበርኩ ግልጽ መታወቅ አለበት። ለዚያውም እንደናንተ ወገኔን በጀርባው መትቸ ለአምባገነን አለቆቸ ግዳይ አቅርቤ ያገኘሁት ሳይሆን በተባበርሩት መንግስታት የስደተኞች ተመካች መስሪያ ቤትና የሱዳን መንግስት’ስደተኞች ተወካዮቻቸውን መምረጥ አለባቸው” ብለው ባዘጋጁት የምርጫ ሂደት ሽወች በተገኙበት በሕዝብ ተመርጨ ነው።ከዚይም በየ ስድስት ወሩ በሊቀመንበርነቱ ይቀጥል አይቀጥል በሚል ክሚቲው ቬቶ እያደረገ ወያኔና የሱዳን መንግስት ኮሚቴው የቅንጅት አባል ነው ፣ብለው እስክከአገዱት እለት ድረስ በሊቀመንበርነት አገልግያለሁ። ኮሚቴው በቆይታው ሽንትና ስንት የጆለቲካ ስደተኞችን ከወያኔ መንጋጋ እያወጣን ወደ ካናዳ አውስትራሊያና አውሮፓ የመሄድ እድል እንዲያገኙ አድርገናል።ዛሬም ያኔ በሱድን ባለስልጣነት ያገኘሁትን እውቅና ተጠቅሜ፣ ያለበቂ ምክንያት የታሰሩ ወገኖችን የማስፈታትና የተብደሉትን ፍትህ እንዲያገኙ የማድረግ እድሉ አለኝ።
  2ኛ=ከአዲስ አበባ የመጣ የግንቦት 7አባል ወይም የቅንጅት የምክር ቤት አባል የነረን ሰው”ኮከብ ተድላ በወያኔ እንዲታፈን አድርጓል ይላል።ይህ እንግዲህ አንዷአለም አያሊውን ማለታቸው ነው። በርግጥ አንዷአለም አያሌው ካርቱም በነበረበት ወቅት በጣም የቅርብ ጓደኛየ ነበር። ግን ደግሞ አሁንም በህይወት ስላለ ማን እንዳሳፈነው ራሱ ሊናገር ይችላል።እስር ቤት ስንቅ ሊያቀብሉት ሚሄዱ ዘመዶቹ ጠይቀው ማን እንዳሳፈነው ጠይቀው ሊናገሩ ይችላሉ።ታናሽ ወንድሙ መሳፍንት አያሌው እናንተ ከምትኖሩበት የሲውድን ነዋሪ ስለሆነ ሂዱና ጠይቃችሁ ተረዱ።
  3ኛ=እኔን የጎዳሁ መስሏችሁ ስሜን በቁጥር አንድ ወያኔነት አስቀምጣችሁ የረጅም ዘመን ጓደናችሁን የተስፉ ሽወንድምን በሁለተኛ ደረጃ ወያኔት ስሙ በመጠቀሱ ያኮርፋችሁ ካልሆነ በስቀር ወያኔ ስለመሆኑ እናንተ ሳትጠይቁት ራሱ ይነግራችሁ ነበር።ይልቅ የተስፉን ወያኔት የሰማችሁት ዛሬ ከሆነ 20 አመት ከመረጃ ወደኋላ መቅረታችሁን የረጋግጣል። ካርቱም ለሚኖረው ኢትዮጵያዊ ተስፉ የሽወንድም ወያኔ ነው ክምትሉ ይልቅ” ሴት ልጀ የወያኔ ጀኔራል ባል አገባችልኝ”ብትል የምስራች!!እንኳን ደስ ያለህ!! እንልህ ነበር።
  በመጨረሻም ወያኔወ እኛን መናቅ ቢያንሳቸው እንጅ አይበዛባቸውም። ለምን ቢባል አብዛኛው ህዝባችን ተላትና ወዳጁን ያማያውቅ፣ከ40 አመት በፊት በነበረ የአጥቢያዳኛ አስተሳሰብ ተሸብቦ የኢንተርኔት ራቦል ጽሃፊ ገዝቶ “እንዲህ ብለህ ጻፍ”እያለ የሰውን ስም ጥላሸት ለመቀባት ሲሮጥ ማየት ከወያኔ የዘረኝነት በሽታ አይተናነስም።
  በመሰረቱ አውርፓ መሄድ መለት በራሱ፣ምን እበላከሚል ስንፍና ከወለደው ጭንቀት ያድን ካልሆነ በስተቀር በራሱ ስልጣኔ አያመጣም። ትምህርትን እድሜ አይወስነውም፣አዋቂ ሰወች አልጋላይ ተጋድመው ትንፋሻቸ እስኪዘጋ አዲስ ነገር ይማራሉ። እናንተም እንደ ኮሶ የተጣባችሁን የአሉቧልታ አባዜ ለመላቀቅ ፍቱኑ መዳህኒት ትምህርት መሆኑን ተረድታችሁ የሰለጠነውን የአውሮፓን ብሀል፣ቋንቋ ፣ቲክኖሎጅና ነጻ አስተሳሰብ ተምራችሁ ለመለውጥ(እንደገና ለመወለድ)ሞክሩ!!!
  ኮከብ ተድላ
  ካርቱም ሱዳን
  02/09/2014

Comments are closed.

Previous Story

የጋዜጣ አዙዋሪዎች ስራ ሊያቆሙ ነው

Next Story

ሰማያዊ ፓርቲ፤ ጠቅላላ ጉባኤ ለመጥራት ውዝግብ ውስጥ ይገኛል

Latest from Blog

የአበባው ታደሰ እና የአረጋ ከበደ ፍርጠጣ | ስለአማራ ክልል ከነዋሪዎች የተሰማው | አበባው ጉ’ድ ሆነ – “አበባውን ሳትይዙ እንዳትመጡ”|“በባህርዳር ተከበናል፣ ከፍተኛ አዛዦች ተመተዋል” | “ፋኖ መንግ’ስት ሆኗል” ጄ/ሉ |

የአበባው ታደሰ እና የአረጋ ከበደ ፍርጠጣ አበባው ጉ’ድ ሆነ – “አበባውን ሳትይዙ እንዳትመጡ”|“በባህርዳር ተከበናል፣ ከፍተኛ አዛዦች ተመተዋል”| “እጅ ከመስጠት ውጭ አማራጭ አይኖረንም” ፊ/ማ “ፋኖ መንግ’ስት ሆኗል” ጄ/ሉ |

ከውጭ በተላከ ገንዘብ ሀብት አፍርቶ የተላከበትን ደረሰኝ ያላቀረበ ንብረቱ እንዲወረስ የሚደነግግ አዋጅ ቀረበ

ዮሐንስ አንበርብር በጥፋተኝነት ላይ ያልተመሠረተ ንብረት የመውረስ ድንጋጌም በአዋጁ ተካቷል አዋጁ የሚፀድቅ ከሆነ 10 ዓመት ወደኃላ ተመልሶ ተፈጻሚ ይሆናል ከውጭ በተላከ ገንዘብ ሀብት አፍርቶ የተላከበትን ደረሰኝ ያላቀረበ ሰው ወይም ሊታወቅ ከሚችል ገቢው በላይ ሀብት አፍርቶ ምንጩ ሕጋዊ መሆኑን ማረጋገጥ ያልቻለ ሰው፣ ንብረት በመንግሥት እንዲወረስ የሚፈቅድ ድንጋጌ የያዘ
Go toTop