አቶ ሙሼ ሰሙ ከኢዴፓ አባልነታቸው ለቀቁ

ከዳዊት ሰለሞን

ከአቶ ልደቱ አያሌው ጋር በመሆን ፓርቲው ከተመሰረተበት 1992 ጀምሮ በህዝብ ግኑኝነት፣ በጸሀፊነትና በፕሬዘዳንትነት ያገለገሉት አቶ ሙሼ ሰሙ ከሁለት ሳምንት በፊት ለፓርቲው ጽ/ቤት ባስገቡት ባለ ሶስት መስመር ደብዳቤ ከፓርቲው የማእከላዊ ኮሚቴ አባልነታቸውና ከተራ አባልነት ጭምር ኢዴፓን ለመልቀቅ መወሰናቸውን አስታውቀዋል፡፡

ሙሼ ለ14 ዓመት ያህል የተጓዙበትን ፓርቲ ለመልቀቅ የወሰኑት በምን ምክንያት እንደሆነ በደብዳቤያቸው ያልገለጹ በመሆኑ የፓርቲው አመራሮች ምክንያቱን ለመግለጽ መቸገራቸውን ምንጮች አስረድተዋል፡፡ ደብዳቤውን ስለማስገባታቸው በስልክ የተጠየቁት ሙሼ ‹‹በራሴ መንገድ ምክንያቴን ይፋ አድርጋለሁ››ብለዋል፡፡

ሙሼ ኢዴፓን ለመጨረሻ ግዜ ያገለገሉት በፕሬዘዳንትነት ሲሆን አንድ ተርም ብቻ በቦታው ካገለገሉ በኋላ በድጋሚ የመመረጥ ዕድል እያላቸው በፈቃዳቸው ራሳቸውን ከዕጩነት ማግለላቸው አባላቱን ሲያነጋግር ቆይቷል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  የህዝበ ሙስሊሙ ኮሚቴ ጠበቃ ተማም አባቡልጉ የጥብቅና ሙያቸው ኮሚቴዎቹ የጥፋተኝነት ብይን በተላለፈበት ቀን መሰረዙ ታወቀ

1 Comment

  1. ተልኦኮህን ፈጽመሀል ብሎ ያሰናበተው ፈጣሪው ወያኒ ነው:: ልደቱ ህዝብን ማወናበድ ከማይችልበት ደረጃ ሲደርስ ወያነ ጥጉን እንዳስያዘው ማለት ነው:: እነሱና መሰሎቻቸው ሀገር ከወያኒ ነጻ ስትወጣ የህዝብ ፍርድ ይጠብቃቸዋል::

Comments are closed.

Share