July 2, 2014
7 mins read

አቶ አንዳርጋቸው በየመን መንግስት ከታገቱ በሁዋላ የኢትዮጵያ ትምባሆ ድርጅት ለየመን ኩባንያ ተሰጠ

የግንቦት 7 አመራር አባል በየመን መንግስት ታግተው ከተያዙ ከአንድ ሳምንት ወዲህ የፕራይቬታይዜይሽንና የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ተቆጣጣሪ ኤጀንሲ ውሳኔ መስጠት በተቸገረበት የብሔራዊ ትምባሆ ድርጅት ሽያጭ ጉዳይ ላይ፣ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ውሳኔ በመስጠት ለየመን ኩባንያዎች ከፍተኛ የአክሲዮን ድርሻ እንዲወስዱ ተደረገ::

በአሁኑ ወቅት የመን አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን አግታ ባለችበት ወቅት የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የየመኑ ኩባንያ ሼባ ኢንቨስትመንት የብሔራዊ ትምባሆ ድርጅት 60 በመቶ ባለቤት እንዲሆን መወሰኑ በርካታ ፖለቲከኞችን እያነጋገረ ይገኛል;:

ሪፖርተር ጋዜጣ እንደዘገበው የ70 ዓመት ዕድሜ ባለቤት የሆነው ብሔራዊ ትምባሆ ድርጅት 22 በመቶ የሚሆነው አክሲዮን ከ1991 ዓ.ም. ጀምሮ በየመኑ ሼባ ኢንቨስትመንት ሲያዝ፣ ቀሪው 78 በመቶ አክሲዮን ደግሞ በመንግሥት የተያዘ ነበር፡፡

የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት በወሰነው አዲስ ውሳኔ ሼባ ኢንቨስትመንት ተጨማሪ 38 በመቶ አክሲዮን ከመንግሥት ላይ እንዲገዛ የሚፈቅድ በመሆኑ፣ ሼባ ኢንቨስትመንት በብሔራዊ ትምባሆ ድርጅት አክሲዮን ላይ አንበሳውን ድርሻ 60 በመቶ ሲይዝ፣ መንግሥት ደግሞ 40 በመቶ ድርሻ ይዞ ይቀጥላል፡፡

ሼባ ኢንቨስትመንት እንዲገዛ ለተፈቀደለት 38 በመቶ አክሲዮን 1.3 ቢሊዮን ብር መክፈል እንደሚጠበቅበት የፕራይቬታይዜሽንና የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ተቆጣጣሪ ኤጀንሲ ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ኃላፊ አቶ ወንዳፍራሽ አሰፋ ለሪፖርተር ገልጸው፣ ኩባንያው ይህንኑ ገንዘብ እንደከፈለ የስም ዝውውር እንደሚደረግ አስታውቀዋል፡፡

ብዙም ባልተመለመደ ሁኔታ የብሔራዊ ትምባሆ ድርጅት አክሲዮን ሽያጭ ላይ የፕራይቬታይዜሽን ኤጀንሲ የሥራ አመራር ቦርድ ውሳኔ ለመስጠት የተቸገረው በሁለት ምክንያቶች መሆኑን ምንጮች ይገልጻሉ፡፡ የመጀመርያው ድርጅቱ በሲጋራ ላይ ብቸኛ መብት (ሞኖፖሊ ራይት) ያለው በመሆኑ፣ ይህ የብቸኝነት መብት የየመኑ ኩባንያ ከፍተኛ ድርሻ በሚይዝበት ወቅት ምን መሆን አለበት? የሚለው ጉዳይ ላይ አቋም መያዝ ባለመቻሉ ነው፡፡ ሁለተኛው ጉዳይ ደግሞ ትምባሆ ድርጅት በተለያዩ የታክስ ዓይነቶች በየዓመቱ ከ1.3 ቢሊዮን ብር በላይ ለመንግሥት የሚያስገባ ከመሆኑም በተጨማሪ፣ ትርፋማ ከሆኑ የመንግሥት የልማት ድርጅቶች መካከል አንዱ በመሆኑ፣ ለመንግሥት ግምጃ ቤት ከፍተኛ ገንዘብ ፈሰስ የሚያደርግ ነው የሚለው ጉዳይ ቦርዱ በአክሲዮኑ ሽያጭ ላይ ለመወሰን እንዲቸገር ማድረጉ ነው፡፡

በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የሲቪል ሰርቪስና የመልካም አስተዳደር ክላስተር አስተባባሪና የሲቪል ሰርቪስ ሚኒስትር በሆኑት ወ/ሮ አስቴር ማሞ የሚመራው የፕራይቬታይዜሽን ቦርድ በእነዚህ ጉዳዮች ላይ የመንግሥትን አቅጣጫ በግልጽ ባለመረዳቱ፣ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት አቅጣጫ እንዲሰጠው መጠየቁን መዘገባችን ይታወሳል፡፡ ነገር ግን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ሁለቱም ጉዳዮች እንዳሉ ሆነው የአክሲዮን ሽያጩ እንዲከናወን በማዘዙ፣ ባለፈው ሳምንት ሐሙስ የተሰበሰበው የፕራይቬይታዜሽን ቦርድ የየመኑ ኩባንያ ከፍተኛ ባለድርሻ መሆን የሚያስችለውን ውሳኔ እንዲወስን ማድረጉን ምንጮች ገልጸዋል፡፡

ትምባሆ ድርጅት በተለያዩ አካባቢዎች የትምባሆ ልማት የሚያካሂድባቸው የእርሻ መሬቶች ባለቤት ነው፡፡ የድርጅቱ መሥርያ ቤት ከሜክሲኮ አደባባይ ወደ ሳር ቤት በሚወስደው መንገድ ከአፍሪካ ኅብረት ፊት ለፊት የሚገኝ ሲሆን፣ ለፀጥታ አመቺ አይደለም በሚል መሥርያ ቤቱ ከዚህ ቦታ ተነስቶ ወደ አቃቂ አካባቢ እንዲዛወር ተወስኗል፡፡ ምንጮቹ እንደገለጹት ድርጅቱ ቃሊቲ አካባቢ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በተረከበው ቦታ ላይ የሚያካሂደውን ግንባታ ሲያጠናቅቅ፣ ለበርካታ ዓመታት ከነበረበት ቦታ ይነሳል ሲል ሪፖርተር ዘገባውን አጠናቁአል::

ውድ አንባቢያን በኢትዮጵያ አትራፊና ከፍተኛ ታክስ ከፋይ ከሆኑ ትላልቅ የመንግስ ኩባንያዎች መካከል አንዱ የሆነው የብሔራዊ ትምባሆ ድርጅት አቶ አንዳርጋቸው ከታሰሩ ወዲህ ለየመኑ ኩባንያ በጠቅላይ ሚኒስተር መስሪያ ቤት ትዕዛዝ ሙሉ በሙሉ እንዲተላለፍ መደረጉ ዙሪያ ምን ትላላችሁ?

5 Comments

  1. I come to believe that ANDARGACHEW arrest has something to do with G7 people, if G7 conspirators were not part of the plot to hand Andargachew to WOYANE, G7 would not be silent and keep his arrest for a week,
    I think Anadargachew is already now in the hands of WOYANES may be that is why G7 kept his arrest till his transfer to Ethiopia completed otherwise Ethiopians should have been informed about his arrest right after his detention hence Ethiopians will force YEMENE not to hand him to WOYANE now it is already late

    he is betrayed by his comrades and the evidence lies in the interview of Mr Epherem Madebos interview he gave to ESAT claiming that they heard about his arrest from Eye witnesses and have no any contact with the YEMEN government in those seven days however ESAT told us G7 was working behind the doors for his release for a week

    አቶ ኤፌሬም ለኢሳት በሰጡት ኢንተርቭው የአቶ አንዳርጋቸውን መታሰር ያወቁበት መንገድ ከአይን ምስክሮች ባገኙት መረጃ እንደሆነ ይናገራሉ እንጅ ስለመታሰሩ ምንም አይነት መረጃ ከየመን መንግስት ያገኙት ማረጋገጫ የለም….
    ስለሰውየው በየመን መንግስት መታሰር እና ስላለበት እስር ሁኔታ ሳያረጋግጡ እና ማረጋገጫ ሳያገኙ እንዴት ነው ሰውየውን ለማስፈታት በሚስጥር ጥረት ሲደረግ ነበር የሚሉን??????

    የአቶ አንዳርጋቸውን መታሰር ግምቦት ሰባት ለምንድን ነው ኢትዮፕያዊያን አንዳይሰሙ የፈለገው????? አቶ አንዳርጋቸው በርግጥ አሁን በወያኔ እስር ቤት ውስጥ ላለመሆናቸው ማስረጃችን ምንድን ነው?????

    ግምቦት 7 ውስጥ ያሉ ሰወች አንዳርጋቸውን ክደውታል እንደዛ ባይሆን ኖሮ ሰውየው እንደታሰር ወዲያውኑ ኢትዮጵያዊን ሊያውቁ እና በየመን መንግስት ላይ ተጽእኖ እንዲያደርጉ ወዲያኑ ነበር መስማት የነበረባቸው አሁን ግን ለአንዳርጋቸው እንዳንድረስለት ለማደርግ እንጅ የሱን መታሰር በሚስጥር መያዙ ምንም አይነት ውሃ የሚቋጥር ምክንያት አይኖርም

    ጀግናው እና ወርቁ የኢትዮፕያ ልጅ አንዳርጋቸው ለወያነ ተላልፈው ከተሰጡ ውንጀለኛው የየመን መንግስት እና ወያኔ ብቻ ሳይሆን መታሰሩን ከኢትዮጵያዊያን ጆሮ ለሳምንት ሚስጥር ያደርገው ግንቦት 7 ጭምር መሆኑን ድርጅቱ እንዲያውቀው እንፈልጋለን

    በርግጥም ወያኔ ከግንቦት 7 ውስጥ ሊያስረው እና ሊገድለው የሚፈልገው ብቸኛ ሰው ቢኖር ጀግናው እና ደፋሩን አንዳርጋቸውን ብቻ ነው

  2. ጀግናው አንበሳውና የንጹሑ ኢትዮጵያ ልጅ በጥንብአሆ አይለወጥም አንድ ቀን ከነጥንብአሆአቸው መቃብር ይወርዳሉ የኢትዮጵያ አምላክ ፍርዱ አይዘገይም ነገ ሌላ ቀን ነው

  3. You one say that it has to de with leyayachew tiges ( i mean andargachw) detention. Possible Woyane sale’s the whole country not only timbahomonopol. Cry to your country than to an individual. he used to be woyanes friend and Ethiopia’s enemy.

  4. ፋብሪካ መስጠት ምን ይክብደዋል አገር እየቆረሰ ለሚቸበችብ መንግስት!!

  5. ምን ይህ ብቻ በመካኒሣ ለቡ 5000ካሬ የሚውል ቦታ ለየመኑ የሥለላ ቡድን መሥኪድ እንዲሠሩበትና ሌላውን ደግሞ ወደፊት የምናየው ይሆናል ሽያ ወይሥ ሱኒ ……?

Comments are closed.

medical mistakes
Previous Story

Health: 10 አስደንጋጭ የህክምና ስህተቶች

Next Story

በረመዳን ጾም ወቅት በስፋት የሚበላው ቴምር ለጤና ያለው 10 በረከቶች

Latest from Blog

“መነሻችን እዚህ መዳረሻችን እዚያ” የሚለው የዲያስፖራ ከንቱ አታካራ! – ክፍል ሁለት

በላይነህ አባተ (abatebelai@yahoo.com) በአንዳንድ ስብሰባዎችና የሕዝብ መገናኛ መድረኮች የሚታየው የአንዳንድ ዲያስፖራዎች  “መነሻችን እዚህ መዳረሻችን እዚያ” የበከተ ከንቱ አታካራ በልጅነታችን ወላጆቻችን ትምህርት እንዲሆነን ይተርኩልን የነበረውን ከጫጉላ ወጥተው ጎጆ ለመመስረት የታከቱ ሁለት ያልበሰሉ ባልና ሚስትን ታሪክ

መነሻችን አማራ መድረሻችን አማራ እና ወያኔያዊ መሠረቱ

የማይወጣ እንጀራ ከምጣዱ ያስታውቃል። የዛሬን አያድርገውና የትግሬ ልሂቆች “ትግራይ የጦቢያ መሠረት ናት ።  ጦቢያ ያለ ትግራይ፣ ትግራይ ያለ ጦቢያ ሊታሰቡ አይችሉም” በማለት ጦቢያዊ ከኛ ወዲያ ላሳር እያሉ አለቅጥ ይመጻደቁ፣ ይኩራሩ፣ ይታበዩ ነበር። ወያኔ

አቶ ታዲዮስ ታንቱ በተከሰሱባቸው ወንጀሎች ጥፋተኛ ተባሉ

ለአመታት በእረስር ላይ የሚገኙት  አቶ ታዲዮስ ታንቱ በተከሰሱባቸው የጥላቻ ንግግር ማሰራጨት እና የዕርስ በዕርስ ግጭት መቀስቀስ ወንጀሎች ጥፋተኛ መባላቸው ታውቋል፡፡ አቶ ታዲዮስ ታንቱ በተከሰሱበት ክሶች በዛሬ ቀጠሮ የጥፋተኝነት ፍርድ የሰጠው የፌደራል ከፍተኛ

ከ”ችርቻሮ” ድል አልፎ ለመሄድ የአንድነት አስፈላጊነት – ግርማ ካሳ

በአሁኑ ጊዜ ሁለት የፋኖ አሰላለፎች አሉ:: መኖር ያልነበረበት:: አንከር ሜዲያ ከሁለቱም አሰላለፎች፣ ሁለት ፋኖ መሪዎች ጋር ቃለ ምልልስ አድርጋለች፡፡ ሁለቱን አደመጥኩ፡፡ በሰማሁት ነገር ተደስቻለሁ:: ትልቅ ተስፋ እንድሰንቅም አድርጎኛል:: የአማራ ህዝባዊ ድርጅት የፖለቲካ
Go toTop