ከምእራብ እና ምስራቅ ወለጋ የተፈናቀሉ የአማራ ተወላጅ ኢትዮጵያውያን ፍትህ አሁንም ድረስ አለማግኘታቸውን ገለጹ

ምንጭ : ኢሳት

አማራዎች በከፍተኛ ችግር ውስጥ እንገኛለን አሉ

ከምእራብ ወለጋ ዞን ከጊምቢ ወረዳ እንዲሁም ከቀሌም ወለጋ ዞን የተፈናቀሉ የአማራ ተወላጅ ኢትዮጵያውያን ንብረታቸው ተዘርፎ ከአካባቢው እንዲወጡ ከተደረገ በሁዋላ፣ ችግራቸውን ለአማራ ክልል ርእሰ ማስተዳድር እንዲሁም ለፌደራሉ መንግስት ቢያመለክቱም የሚሰማቸው ማጣታቸውን ገልጸዋል።

ኢሳት ካነጋገራቸው የተፈናቃዮች ተወካዮች መካከል አንዳንዶች እንደገለጹት የአማራ ክልልም ሆነ የፌደራሉ መንግስት በክልሎች ጉዳይ ጣልቃ አንገባም በሚል ምክንያት ለጥያቄያቸው መልስ ለመስጠት ፈቃደኞች አልሆኑም። ከመንግስት የሚሰጠው መልስ ተስፋ እንዳስቆረጣቸውም ተፈናቃዮች ገልጸዋል

የተፈናቃይ ተወካዮች እንደሚሉት ከፍተኛ ችግር ከነበረበት ከሚያዚያ 22 እስከ ግንቦት2 በነበረው ጊዜ ለደረሰው የሰው ህይወት እንዲሁም ለጠፋው ከፍተኛ ንብረት የአካባቢው ባለስልጣናት እና በክልሉ ተሰማርቶ የሚገኘው ልዩ ሃይል እጅ አለበት። ባለስልጣናቱ የችግሩ አሳሳቢነት ሲነገራቸው መልስ ለመስጠት ፈቃደኞች ባለመሆናቸው ከፍተኛ ውድመት እንዲደርስ ምክንያት መሆኑን የተፈናቃዮች ተወካዮች ተናግረዋል።

በተለይም ጉዳዩን እንዲያጣራ በቅርቡ የተቋቋመው አጣሪ ኮሚቴ ማስረጃዎችን አስቀድሞ ይፋ እያደረገና የምስክሮችንና የጠቁዋሚዎችን ስሞች አስቀድሞ ይፋ እያደረገ ህዝቡ በድጋሚ እንዲጋጭ ጥረት እያደረገ ነው በማለት ተወካዮች ገልጸዋል።

በጊምቢና በቄለም ያሉ ዘመዶቻቸውን በስልክ ለማግኘት መቻላቸውን የሚናገሩት ተፈናቃዮች፣ አካባቢውን ለቀው እንዲወጡ ዛቻና ማስፈራራቱ እንደቀጠለ መሆኑን እንደነገሩዋቸው አስረድተዋል።

ከኦሮምያና ከፌደራል የተውጣጡ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት ማክሰኞ ወደ ጊምቢ በማቅናት ነዋሪውን እያነጋገሩ ነው። እስካሁን ድረስ በመንግስት በኩል ተፈናቃዮችን በተመለከተ የተሰጠ ይፋዊ መግለጫ የለም።

በጊምቢ ተነስቶ በነበረው ግጭት የአንድ ሰው ህይወት ሲወድም፣ አንድ ፎቅና ሁለት መኖሪያ ቤቶች ተቃጥለዋል፤ በርካታ ቤቶችም ተዘርፈዋል።

ተጨማሪ ያንብቡ:  የአልሸባብን የሽብር ተልዕኮ ሊፈጽም ነበር የተባለ ግለሰብ ተያዘ

2 Comments

  1. ዽሮ አማራው በነበረው የበላይነት የኦሮሞን መሬት ወሮ ጡት ቆርጦ ገድሎ ያስቃየው ዛሬ ባለተራ ሆነ…….ቦ ጊዘ ለኩሉ
    ይልሃል….እንደዚ ነው……
    ወደ አማራ ክልል ብትሄዱ ኦሮሞ የሚባል የለም እንኩዋን መሬት ሊኖረው……
    የአማራን የበላይነት ላይነሳ የቀበረ መንግስት…….!!!!!! በአትዮጵያዊነት ስም ሌላውን ባርያ አርጎ መግዛት….አይሰራም
    አማሮች በሰፈሩት ገና አልተሰፈረላቸውም……….አማራ ክልል መሬት ስለጠፋ ነው ኦሮሚያ የሰፈሩት ቂቂቂቂ……….ቂቂቂ

  2. abc kkkk you don’t know your history, the land you call Oromiya was the land of other indigenous people like ENARYA, DAMOT, GAFAT, AMHARA, and GURAGE and HADYA, Oromo invaders of the 16 century killed and expelled Amharas and exterminated other tribes from their indigenous land and this is even written by foreign historians who witnessed the brutality of Oromos who came to Ethiopia to kill and take other people land

    The Amhara people is betrayed by AMHARA elites that is why we are seeing this kind killings and displacement went unpunished and unreported to the international Genocide Prevention Commission and the criminals of OLF who were responsible for the killings of THOUSANDS OF AMAHRAS are living freely in the west among us this is because the stupidity and negligence of AMAHRA ELITES to show sympathy about the death and displacement of innocent Amahra WOMEN and Children

    the worst crime of AMHARA ELITES is not only the lack of interest to stop the Genocide on Amharas but it is their unwillingness to teach Amharas about their eternal enemies like OLF, TPLF, and SHABIA,
    If Amahra people were taught about these deadly enemies long time ago they could have well equipped ideologically and militarily to defend themselves, it is because of the betrayal of AMHARA MUHURANS Amahrans are suffering and being killed like animals

Comments are closed.

Share