June 27, 2014
1 min read

ጀግናዋ (ይቅርታ “አሸባሪዋ”) አልጋነሽ ገብሩ! (አብርሃ ደስታ)

10489640

የወይዘሮ አልጋነሽ ፎቶግራፍ እስከምናገኝ ድረስ በቀበሌ መታወቅያዋ ላይ ያለ ፎቶ እንጠቀም እስቲ። “መታወቅያዋ አልታደሰም” ተብላ የህግ ጠበቃ ተከልክላ ነበር። ማን ያሳድስላታል? መንግስትኮ የለም። በቃ ህገመንግስትና ህገመንግስታዊ ስርዓቱ በኃይል ለመናድ ሞክራለች ተብላ በሽብር የተከሰሰች የዘመኑ ጀግናችን አልጋነሽ ገብሩ ናት። ህፃን ልጆች አሏት። ትናንት ማታ ዘነበ ታደሰ የተባለ የ12 ዓመት የአልጋነሽ ልጅና ምልአት ካህሱ የተባለች የጎረቤት ልጅ በኲሓ ፖሊስ ታስረው በወረዳው የፀጥታ ሓላፊ፣ የኲሓ መርማሪ ፖሊስና ሌላ የፖሊስ አባል ተደብድበው ከእስር በዋስ ተለቀዋል። የታሰሩበት ምክንያት “ረብሸዋል” የሚል ነው። ረብሸው ምን አደረጉ? እንደ እናታቸው መንግስት አሸበሩ ወይስ የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ አደረጉ? ደሞ የ12 ዓመት ህፃናት ይታሰራሉ? ጥረቱ ሁሉ በአልጋነሽ ላይ ተፅዕኖ ለማሳረፍ ያለመ ነው።

2 Comments

  1. አዬህ አብርሽ ወያኔ አይሁድ ነው? ለህጻነት መንፈስ እንኳን ትንሽ የማይጠነቀቅ። ነገን የገደለ ዛሬንም የረሸነ። ስለዚህም ወያኔ መነቀል አለበት። ለወቅታዊ መረጃው እጅግ ከልብ አመስግንሃለሁ። በርታ አባቱ! አዎን ወያኔ የሚያስራቸው አሸባሪ ናቸው ለእኛ ደግሞ ጀግኖቻችን ናቸው። ሴቶች ከቆረጡ ድልን አምጠው የመውለድ አቅማቸው ብቁ ነው። የማህጸናቸው የደም ዕንባ እዬርን የማንካኳት አቅም አለውና!

    እግዚአብሄር ይስጥልኝ።

  2. This is not new news. Woyane was killing kids and feeding poison to those who do not abide by its Albanian style communism. Find and read their history back in the bushes. What they are doing in our country at the present time is the same as the past except now, they do have more destructive forces in place. Take a look of Eritrea and Ethiopia are we really better off now than the past? NO, we just got two masters for the same people. Your story is the extension of the misery we witness around our beloved country. So sad to read underage kids are treated in such rough manner by the forces that fleece our country and its people using them as a tool.

Comments are closed.

Previous Story

ክሽን ያለ የኢትዮጵውያን ሰላማዊ ሰልፍ ሲዊዝ – በርን።

Next Story

ህወሓቶች የመቐለን ሰለማዊ ሰልፍ ለመከልከል ወስነዋል። (አብርሃ ደስታ)

Latest from Blog

አስቸኳይ ህዝባዊ ጥሪ

July 24, 2024 ዓለማቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያዊያን መብት Global alliance for the Rights of Ethiopians (GARE) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሳቻ ጎዝዲ ቀበሌ በደረሰው የመሬት መንሸራተት የብዙ ወገኖቻችንን ህይዎት ማለፉን
Go toTop