ክሽን ያለ የኢትዮጵውያን ሰላማዊ ሰልፍ ሲዊዝ – በርን።

ከሥርጉተ ሥላሴ 26.06.2014 (26.06.2014) በሰከነችው ሲዊዝ ማዕከላዊ መዲና በበርን ዛሬ ዕለተ -ሃሙስ 26.06.2014 ከዚዊዝ ከተለያዩ ከተሞች የመጡ ኢትዮጵውያን ሁለመናው ክሽን ያለ ሀገራዊ ሰላማዊ ሰልፍ አደረጉ።  „የሰብዕዊ መብት ረገጣ በኢትዮጵያ ያደረሰውን በደል“ ማዕከል ያደረገው ሰላማዊ ሰልፍ ኢትዮጵዊነት ያጎላ፤ ኢትዮጵያዊነትን ያደመቀ፤ ብሄራዊ ስሜትን ያስዋበ ነበር። ሰላማዊ ሰልፉ ከሲዊዝ ማዕከላዊ መንግሥት ቢሮ በቅርብ እረቀት እንዲሁም በፖሊስና በአስተዳደር የተለያዩ አካላት አካባቢያዊ ሙቀት ባልተለዬው፤ በርዕሰ መዲናዋ አንጎል ቦታ በባይዘንሃውስፕላትስ የተካሄደ ስለነበረ በቂ አድማጭ ነበረው። በግልጽ አዬር ላይ ባላው የገብያ አናት ቦታ ላይ ሰልፉ መካሄዱ በአጭር ጊዜ፣ በተወሰነ አቅም ሰፊ መልዕክትን ማስተላላፍ የቻለ፤ ለመደመጥም አቅም የነበረው ነበር ማለትም ይቻላል። በተጫማሪም ከሰልፉ ጋር በተጓዳኝ የተከወነው ድንቅ ጅምር በጀርመንኛ ቋንቋ ያለውን የዘረኛና አንባገነናዊ አገዛዝ ውስጠ – አረመኔነት የገለጸ አጭር በራሪ ጹሑፍ በቅርብ ለማድምጥ ለተጠጉት ሆነ በአካባቢው ለነበሩ የሀገሬው ሰዎች መታደሉ ዬሰልፉን መሰረታዊ ዓለማ ከተለመደው በተለዬ ሁኔታ የተሻለ አድርጎታል። ሲዊዘርላንድ ውስጥ የሚካሄዱት የነጻነት ትግሎች ባህሬያት ከሌላው አካባቢ የሚለዬው ጥሪውን አድምጠው ችለው በሥፍራው የሚገኙት ወገኖች ለመጡበት ጉዳይ በሙሉ ኃይልና ከልብ በመነጨ ፍላጎት ያልተገኙትንም ወገኖቻቸውን ድምጽ አክለው የሚከውኑ በመሆኑ፤ ጥቂቶች ግን ብዙ ተግባርን ለመወጣት ያላቸው ብቁ አቅም ከሌሎች አካባቢዎች ባላነሰ ተሳትፎው የተመጣጠነ እንዲሆን ያስችለዋል። በተገኘው ሃይል ማናቸውም ሃላፊነት ደምቆና አምሮበት ለግብ መብቃት ሲዊዝን ከሌሎች ጋር እኩል እንድታራመድ የሚያደርገው ብልሃት ያለው ከዚህ ላይ ነው። ዛሬም እንደተለመደው ታዳሚዎቹ በሰላማዊ ሰልፉ ላይ አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ሰንድቅዓላማቸውን በውስጣቸው በማወለብለብ እናት ሀገራቸው ከእነሱ የምትፈልገውን ለማድረግ የቆረጡ በቂ ሰልፈኞች በቦታው ተገኝተው የሀገራቸውን፤ የወገኖቻቸውን እንባ ተጋርተዋል። በእንግልት ላይ ለሚገኙ የብዕር አርቦኞቻቸው ወንጀሎኞች አለመሆናቸውን አበክረው ገልጸዋል። የግንባር ሥጋ ለሆኑት የፖለቲካና፤ የሃይማኖት መሬዎቻቸውንም ከጎናችን ነን ሲሉ በአንድ ድምጽ ቃላቸውን በውልና በኪዳን አዋውለውታል። በተጨማሪም የሲወዝ መንግሥት ለጀግና አበራ ኃይለመድህን አበራ ያደረገለትን መልካም ነገር ሁሉ በማድነቅ ምስጋናቸውን በአኃታዊ መንፈስ ገልጸዋል። እንዲሁም በእንግልት ላይ ለሚገኙ መኖሪያ ፈቃድ ላላገኙ ወንድምና እህቶቻቸውም የሲዊዝ መንግሥት ጉዳያቸውን  በአግባቡ ያይ ዘንድ በትሁት መንፈስ ጠይቀዋል። ከዚህም ሌላ የወያኔ ሃርነት ትግራይ ዘረኛ አጋዛዝ በወጣት የዩንቨርስቲ ተማሪዎች ላይ የወሰደውን ከሰብዊነት ውጪ የሆነውን አረመኔያዊ ድርጊት አውግዘዋል።  የሲዊዝ መንግሥትም እንዲህ ላላ የዘረኛ አንባገነናዊ ወንጀለኛ ሥርአት የሚሰጠውን ማናቸውንም እርዳታ በአግባቡ ይመረምረው ዘንድ በአጽህኖት አሳስበዋል። ሰልፈኞቹን በመቀላቀል ንግግር ያደረጉት በሲዊዝ የሰብእዊ መብት ተሟገች የሆኑት ወ/ሮ ዚሞንም ኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን የመብት ረገጣ በቅርብ እንደሚከታተሉ በመግለጽ ኢትዮጵውያን በተሰደዱበት ሀገር መደመጥ እንዲችሉ፤ ጉዳያቸው በአግባቡ መታዬት እንዲችል፤ ጥበቃም እንዲደረግላቸው ትግላቸውን ከሌሎች አጋር ሀገሮች ጋር ማቀናጀት እንደለባቻው አበክረው ገልጸዋል። ስለሆነም ሰኔ 28.2014 በሚዘጋጀው ሰላማዊ ሰልፍ ኢትዮጵውያን እንዲገኙ አሳስበዋል። ሰላማዊ ሰልፉ በተገባው ሁኔታ የሰልፉ መሰረታዊ ኣለማ ተብራርቶ ተጀምረ። ወሸኔ! ቆይታውንም በመገምገም ከሲዊዝ መንግሥት ጋር ያደረገውን ግንኙነት በማብሰር ለቀጣዩም የመንፈስ ስንቅ ቆጣጠሮ በፍቅር – ተጠናቋል። ማለፊያ! በዕለቱ በቀጣዩ ወር ሃምሌ 26.2014 በሲዊዘርላንድ በበርን ለማካሄድ በታቀደው „የኢሳት የእኔ ነው“ የማጠናከሪያ ስብሰባ የተዘጋጀው የጥሪ ወረቀት ለሰልፈኞች በነፍስ ወከፍ ታድሏል። ዋው! – ወርቅ ተግባር። የመግቢያ ትኬትና መጸሐፍትም ተሽጧል። ክውና — የዛሬ ሰላማዊ ሰልፍ የተደራጀ – የተቀናጀ -መሪ የነበረው – ሁለገብ ተግባራትን በአግባቡ የከወነ እኔም የተደሰትኩበትና ሁለመናዬ ያልባከነበት የልቤን ያደረሰ ሰላማዊ ሰልፍ ነበር ማለት እችላለሁ። ጊዜ – አቅም – ነገ ሁሉንም እንዲህ መስመር አስይዞ መምራት ከተቻለ ጥቂቶች ምርጥ ዘሮች ናቸው እጥፍ ድርብ ከእቅድ በላይ ማምረት ይችላሉ። ድክመቶችን ሆነ ስህተቶችን በአግባቡ አጥንቶ መፍትሄቸው እንዲመራቸውም መንገድ መጥረግ በቀላሉ ይቻላል። ችግርን እራሱን ማድመጥ – ስክነት!   የእኔ ውድ  …. የሀገረዎት ጉዳይ ያስጨንቀዎታልን፤ ሰንደቀዎት አስከብሮት እንደኖረ እንዲቀጥል ይሻሉን? ነገን ትውልዳዊ ድርሻዎትን በመወጣት ለትውልድ ማስረከብ ይፈልጋሉን? መሬተዎት – አፈረዎት – ጠረነዎት – ሽው  -ውል  ብሎዎታልን? …. ጨለማን ላማንጋትስ ቆርጠዋል? ጥቃትን ታቅፎ፤ እህህን ሰንቆስ መኖርስ ሰልችቶታልን? ከሆነ … ማስታወቂያ!   1. „ኢሳት የእኔ ነው“ ቀን —– 26.07.2014 በሚቀጥለው ወር በሃምሌ እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር – አድራሻ —– Edis Star – Bar und Billardhalle Dorfstrasse 22 3084 Wabern በእለቱ – ይገኙና አደራን ያክበሩ –   2. የስደተኞችን ጥያቄ ዕውቅና ለማሰጠት የተጠራ ሲውዝ አቀፍ የሶሊዳሪቲ ሰላማዊ ሰልፍ   Power of the People (የስደተኛመብትተሟጋች) ያዘጋጀውሰላማዊሰልፍመረጃለምትሹ። ቀን —–  28.06.2014 በዚህ በያዘንው ሰኔ ወር እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር …. ቦታ —– Schütezenmatte, Bern ሰአት —–  14.00 ስልክ —– ሶሎቶርን 0764467862- 0764197279 – 0764089287 በርን 0765042974 – አራው 0768194142 – ባዝል 0765420878 – ዙሪክ 0764822240 ትራንስፖርት በነፃ አስተባበሪዎችን በዬክሀገሩ በማግኘት ይከወናል።   ክብረቶቼ – የኔዎቹ፤ ለነበረን መልካም ጊዜ ውስጤን ሸልሜ፤ ነፃነቴን ለሰጠኝ ዘሃበሻን ከልብ አመስግኜ ውበቶቼን ታዳሚዎቼን ደግሞ ውድድ አድርጌ  ልሰናበት ወደደድኩ። መልካም ጊዜ ….. ሃሙስ ሀምሌ 3.07.2014 አዬር ላይ ደግሞ እንገናኝ ጊዜው ከኖረዎት ….. Radio Tsegaye ወይንም በዚህ ሊንክ እንገናኝ።  www.tsegaye.ethio.info Aktuell Sendung   ጠላትን ማሸንፍ የሚቻለው እኔን እራሴን ማሸነፍ ስችል ብቻ ይሆናል! ኢትዮጵያዊነት እኔነቴን የሸለመኝ የውስጤ ጸሐይ ነው!

  • wir sind geistige Gefangenen  እኛ የመንፈስ እስረኞች ነን።
ተጨማሪ ያንብቡ:  ከባድ አደጋ ላይ ነን ግጭቱ ወደ መኮንኖች ተሸጋግሯል” አበባው አፈረጠው - “ኦሮሞዎቹ ይታጠቁ፣ ሌሎች ትጥቁን ያውርዱ” አብይ አህመድ

እግዚአብሄር ይስጥልኝ።

1 Comment

  1. ከ አለበል እናት አገር ወይም እናት አለም ሃገር ወገኑን የሚወድና የወገን ብሶትን ከልብ ብሎም ማነኝ ብሎ ይጠይቃልና ዛርዬ ያለንበትን ስንመለከት ለሃገራቺን የሞቱትን ሳይሆን እኛም ሞተን ልጆቻችንን እንዳንግድል / የታሪቅ ድሃ/ እንዳናደርግ ስለመፈራ;; አምላክ ከናት አገርና ከኢትትዮጵያ ህዝብ ጋር ይሁን;; አንቺንም አምላክ ካንቺ ጋር ይሁን. አመስግናለሁ;;

Comments are closed.

Share