ሰበር ዜና:- ጋዜጠኛ ተሰማ ደሳለኝ ሀገር ጥሎ ተሰደደ መንግስት አሁንም ሌላ ጋዜጠኛ አስሯል

የኢትዮጵያ መንግስት በቅርቡ በጋዜጠኞች እና ብሎገሮች ላይ የፈፀመውን እስር ተከትሎ የኢቦኒ መፅሔት መስራች እና ማኔጂንግ ዳይሬክተር የነበረው ጋዜጠኛ ተሰማ ደሳለኝ ሀገር ጥሎ ተሰደደ፡፡ ጋዜጠኛው በሀገሪቱ ያለው የፕሬስ ነፃነት አፈና ተጠናክሮ በመቀጠሉ እና መንግስት ሊወስደው ያሰበውን እርምጃ በመሸሽ እንደተሰደደ ምንጮቻችን አረጋግጠዋል፡፡ በተለይ የኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴሌቪዥን፣ አዲስ ዘመን ጋዜጣ፣ ዛሚ ኤፍ ኤም፣ እና በሌሎች የኢህአዴግ ደጋፊ ናቸው በሚባሉ እንደነ አይጋ ፎረም እና ሆርን አፌይርስ የመሳሰሉ ድህረ-ገሮች የተለያዩ ጋዜጠኞች እና የኢትዮጵያ ዞን 9 ብሎገሮች እንዲታሰሩ እና እንደሚታሰሩ ፍንጭ መስጠታቸው ለስደቱ ምክንያት መሆኑ ተጠቁሟል፡፡ከመጪው ምርጫ 2007 ዓ.ም. በፊት የመንግስትን ብልሹ አሰራር እና ኢሰብዓዊ ድርጊት በመኮነን ያጋልጣሉ የተባሉ የነፃው ፕሬስ ጋዜጠኞች እና ብሎገሮች እንደሚታሰሩ በተለያየ ጊዜ የተነገረ ቢሆንም፤ በቅርቡ 3 ጋዜጠኞች እና 6 ብሎገሮች መታሰራቸው ይታወቃል፡፡ በመንግስት የተወሰደው የጋዜጠኞች እና ብሎገሮች እስር ተከትሎ ሌሎችም ሊታሰሩ እንደሚችሉ በተዘዋዋሪ መንገድ መገለፁን ተከትሎ ከጋዜጠኛ ተሰማ ደሳለኝ በፊት ጋዜጠኛ በትረ ያዕቆብ እና ፍስሃ ያዜን ጨምሮ አራት ጋዜጠኞች መሰደዳቸው ታውቋል፡፡ ጋዜጠኞቹ ከሀገር ጥለው መሰደዳቸው በስተቀር እስካሁን ያሉበትን ሁኔታ ማረጋገጥ አልተቻለም፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ የእንቁ መፅሔት ዋና አዘጋጅ ጋዜጠኛ ኤልያስ ገብሩ ከስራው ጋር በተያያዘ በእንቁ መፅሔት በተፃፈ ፅሑፍ ከማዕከላዊ ቃሉን እንዲሰጥ በስልክ በተደረገለት ጥሪ ትናንት ሰኞ ግንቦት 18 ቀን 2006 ዓ.ም. ወደስፍራው ቢያቀናም ማረፊያው እዛው ማዕከላዊ እስር ቤት ሆኗል፡፡ ይሁን እንጂ ዛሬ በዋስ ይለቀቃል ተብሎ ቢጠበቅም እስር ቤቱ ፍርድ ቤት አቅርቦት የዋስ መብት ሳይከበርለት ለተጨማሪ 7 ቀናት እዛው ማዕከላዊ ታስሮ እንዲቆይ ተጠይቆበት በእስር ላይ ይገኛል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  የኢትዮጵያ ኮምዩኒቲ በሚኖሶታ የሚያዘጋጀው የኢትዮጵያ ቀን ጁላይ 23 ይከበራል - ሲራክ ህይሉ
Bisrat Woldemichael

 

 

2 Comments

  1. I am advising to all Ethiopian, who fled their country because of persecution, don’t come to where we have been subjected to inexplicable suffering because of the stand we have taken against the dictatorial, divisive and ethnocentric regime-Kenya!
    Kenya is a staunch supporter of EPRDF/TPLF and Opposing EPRDF/TPLF in Kenya is a punishable crime on the country’s unwritten law.

  2. >>>ኢህአዴግ የገጠመውን የኪራይ ሰብሳቢ፣የሙሰኛ፣ጥቅማጥቅመኖች የእኔ የእኔ ብቻ አትድረስብኝ ያንተን እንካፈል… ቁርሾ አመፅን ቀስቅሶ ንብረት ሲያወድም፣ ባንክ ሲያዘርፍ፣ ግለሰቦች የለፉበት ንብረት በእሳት ሲቃጠል…ሞኝ ያገኘው ፈሊጥ! “የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ተደበደቡ፣ አበዱ፣ ፈነዱ፣ አለቁ” እያሉ ቁስለኛና እሬሳ በመቁጠር የግል የፓለቲካ ፍጆታቸውን በድሃ ልጅ ደም ሲያባዙ ሲያካፍሉ የከረሙት የኢህአዴግ ደጋፊና-ተደጋፊ.. ተቃዋሚና- ተቋቋሚ አንዲሁም መሐል ሰፋሪው እነ ጭር ሲል አንወድም አጋር ፓርቲዎችን ጨምሮ ከቀበሌ-እስከ ክልል ከገጠር እስከ አህጉር ሲቀውጡት ሰነበቱ።

    **ህወአት/ኢህአዴግ ምኑ ሞኝ ነው የተካናበትን ዘዴ…ለተጎጂው ኦሮሞ ጭዳ ማቅረብ ስላለበት “አቶ ኤሊያስ ገብሩን ወደ መሰዊያው አቀረበ” የኦሮሞ የዩኒቨርስቲ ተማሪ ሕገ-መንግስቱን ጥሶ ሳያስፈቅድ ንብረትና ሰው እያጠፋ ሰላማዊ ሰልፍ እያለ ሲቀውጠው አልተጠየቀም ጭራሽም ሕገ-መንግስታዊና ተገቢ ጥያቄ ተባለ።(ለመሆኑ በጋራ ማስተዳዳርና የከተማ ልማት የሚከለክል ህገመንግስት አለ? ለመሆኑ ሕዝቤ መንገድ ጤና ጣቢያ መጓጓዣ የጥቃቅን አንዱስትሪ ባላቤትና ተጠቃሚ አይሁን ‘ገበሬና ሁለት በሬ’ ብቻ የሚል ዜጋ የየት ሀገር ሰው ነው? ለመሆኑ ይህ ሁሉ ወጣት ተምሮ ት ሊሄድ ነው? ምን ሰርቶ ቤተሰብ ሊመሰርት ነው!?ድሃው ገበሬ አይለፍለት ቋንቋውና ዘለዓላም የኖረበት የኩበት ጭስ..የአልቅት ውሃ..የድንጋይ መደብ ለወገቡ ፈረደበት ማነው? በእርግጥ የእነኝህ የመካካለኛና ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የትምህርት ሥርዓት ብቃትና ጥራቱ አይንና ጆሮ አዕምሮ ባለው ሰው ይመራል? ወይንስ ያው ልማታዊ ካድሬ መፈልፈያ ሆኗል የሚባለው እውነት ነው።? እኛ ከውስጥ እናንተ ከውጭ ድረሱ ተብሎ በቅንጅት የተሰራውን አመፅና ሽብር ያልታወቁ ግለሰቦች ተቀላቀሉበት ይላሉ።ያልታወቀ ግለሰብ እንዴት በከተማውና በሀገሩ ኖረ? መሳሪያ ከየት አመጣ? ምን አልባት የክልሉ ፖሊስ ደህንነት አቀብሎ ይሆን? ቀድሞም “ክርስቲያን ቀና ብሎ ካየን አንገቱን በሜንጫ እንለዋለን ሲሉ ከፓለቲካ ተንታኝነት ወደ ፖለቲካ በታኝነት የመከላከያውንና ፖለቲካል ኢኮኖሚውን በአመፅ እንነጥቃለን የሚሉትን በኢህአዴግ በውስጥ ክንፍ አድርጎ በጂነዲን ሳዶ ሚስጥር አቀባይነት ለተቀነባባረው ሴራ ወይንም ከኢህአዴግ በሥነምግባር ጉድለት ተባረው ዛሬ ዙሪያውን በማዋቀጥ ተልካሻ የታሪክ መፅሐፍ በመቸርቸር ግን የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ሆነው ወጣቱን ለፀብ የሚጋብዙትን ሰላም በማደፍረስ የልማት የሀገር ሰላምና ዕድገትን የሚያደናቅፉትን መንግስት እየረዳና እየተንከባከበ ያላቸውን ሕጋዊ የፓርቲ ፍቃድ የሚያስነጥቅ አመፅ በግላጭ በአደባባይ መፈክር እያሰሙ ሲቀሰቅሱ ምንም በቂ እርምጃ ሳይወስድ በንጹሃን ደካማ ጋዜጠኞች(ተቺ) ፀሀፊያን ላይ የሚደርሰው አፈናና እንግልት፣ አድሎዓዊ እስር ..ከሜንጫ እስኪሪብቶ ጋዜጣና ትችት ከፈራ በእውነቱ ኢህአዴግ ከነበረበት ደረጃ በጣም ዝቅ ያደረገው ድሃ ታጋዮች የተሰውለት ዓለማና ተግባሩ ሁሉ በጥቂት ጥቅማጥቅመኞችና አስመሳይ አድርባዮች የተጠለፈበት አንደሆነ ሊረዳ ይገባል። “መድረክ ሲፋቅ ኢህአዴግ” ነው ማለቱ ከጥቅሙ ጉዳቱ ያመዝናል!!!ይታሰብበት>>>ሐሳብን በሀሳብ መሞገት እነጂ አትፃፍ አታፅፍ ማለት አድሎዓዊ በቀል የፈሪ ዱላ ያስመስላል በግለሰቡ ጋዜጣ ላይ ተፃፈ ለተባለው ነጥብ ሞጋች ፅሑፍ ማውጣት ብልህነት ነው።አራት ነጥብ። “ንብረትና የሰው ህይወት ያጠፋነው የተፃፈ አንብበን ጭንቅላታችን ተናውጦ ነው” የሚለው የየዋህ መከላከያ መልስ ግን “ነጻ እንድናወጣችሁ አከሌን ክሰሱና ዴሞክራሲያዊነታችንን በበቀል እናሳያችሁ ተብለው ነው። ይህም ቢኒያም ከበደ በአምቦ ዩኒቨርስቲ ያነጋገራቸው ልጆች ቃል በቃል የተነገራቸው አስኪጠፋባቸው ግን በትክክል ዛሬ ግለሰቡ የተከሰሰበትን ነጥብ አስረድተዋል የኦሮሞ ጎምቱ ሊሂቃንም ያንኑ በተለያየ ሚዲያ አብራርተውታል ። ለምን ይዋሻል!? ሕዝብ እና መንግስት ህግ ማክበር አለበት…በዚህ ዘመን ውይይት እንጂ ንበረትም ሰውም መጥፋት የለበትም። የተማረ ያስተማር!ያልተማረ ይማር!ዕድገትና ብልጽግና በጋራ ለጋራ ለእኛ እነጂ ለእኔ ብቻ ማለት ይቅር።ሰላማዊ ጋዜጠኞች ፖለቲከኞች ጸሐፊያን ነፃ ይሁኑ በለው!

Comments are closed.

Share