አስደንጋጭ የእሳት አደጋ

ምንሊክ ሳልሳዊ
ከጎተራ ማሳለጫ ወደ ቄራ በጓዝ ላይ የነበረ ነዳጅ የጫነ የፈሳሽ ማመላለሻ መኪና ከነተሳቢውና ተሳፋሪ ጭኖ ከቄራ በኩል ይጓዝ የነበረ ሚኒባስ ታክሲ ሞሐ ለስላሳ መጠጦች ፋብሪካ(ፔፕሲ) ፊት ለፊት ራሳቸውን ከመጋጨት ለማትረፍ ባደረጉት ጥረት ተሳቢው ታክሲው ላይ ተገልብጦ በደረሰ ከፍተነኛ የእሳት አደጋ ሰዎች ተቃጠሉ።

በአሁኑ ሰዓት የተቃጠሉ አስክሬኖች እየተለቀመ ነው።ተጎጂዎች ወደ ሆስፒታል እየተወሰዱ ነው።አደጋው ከደረሰ አንድ ሰዓት ሆኖታል። የዐይን እማኞች እንደተናገሩት ተሳቢው ታክሲው ላይ በወደቀበት ቅጽበት ሚኒባስ ውስጥ ያሉትን ሰዎች ለማትረፍ ርብርብር የተደረገ ቢሆንም ተሳቢው ውስጥ የነበረው ነዳጅ በመፍሰሱ በድንገት ከፍተኛ እሳት ተነስቷል።በዚህን ጊዜ ሁሉም ራሱን ለማዳን መራወጥ ጀመረ።

እንደምንም ከሚኒባሱ ውስጥ የወጡ ሰዎች እሳት እየነደደባቸው ራሳቸውን ለማትረፍ ሲሞክሩ ታይተዋል። አደጋውን ተከትሎም በአካባቢው ወዲያው የደረሱ መኪኖች ተጋጭተዋል። አካባቢው በከፍተኛ ጭስ ታፍኖ ነበር። (ምንሊክ ሳልሳዊ)

ተጨማሪ ያንብቡ:  የተባበሩት መንግሥታት የፀጥታው ምክር ቤት አባላት ለኢትዮጵያ ያላቸውን ድጋፍ አሳይተዋል

1 Comment

  1. really sad, the government of Ethiopia should take measure in implementing special roads and restrictions on commercial specialty oil and gas trucks and speed restriction license suspension can help to reduce the problems

Comments are closed.

Share