6 ኪሎ ዩኒቨርሲቲ ውጥረት ነግሷል፤ የታጠቁ ኃይሎች ወደ ዩኒቨርሲቲው ገብተዋል

ጋዜጠኛ ዳዊት ሰለሞን
ጋዜጠኛ ዳዊት ሰለሞን ከአዲስ አበባ እንደዘገበው እንደ ሰደድ እሳት በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት እየተዛመተ የሚገኘው ተቃውሞ ዛሬ ማረፊያውን አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ አድርጓል፡፡ በአሁኑ ሰዓት ራሳቸውን ከጥቃት ለመከላከል የሚያስችላቸውን ትጥቅ በአግባቡ የታጠቁ ልዩ ሃይሎች ወደ ትምህርት ቤቱ ዘልቀው ገብተዋል፡፡ የዩኒቨርስቲው ፕሬዘዳንት ዶክተር አድማሱ ጥያቄ ያቀረቡ ተማሪዎችን በማነጋገር ከሚመለከተው አካል ጋር በመነጋገር መፍትሄ እንደሚፈልጉ ነግረዋቸዋል፡፡

ተጨማሪ መረጃ እንደደረሰን እናቀብላችኋለን

ይህ በእንዲህ እንዳለ በአዲስ አበባ በተለይም በቤተመንግስት አካባቢ ያለው ጥበቃ በከፍተኛ ሁኔታ እንደጨምረ ተያይዞ ለዘ-ሐበሻ የደረሰው መረጃ አመለከተ። ይህን የጥበቃ መጠናከር በኢትዮጵያ የተለያዩ ክልሎች የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የአዲስ አበባን ማስተር ፕላን በመቃወም ባነሱት ተቃውሞ የተነሳ መንግስት ከፍተኛ ስጋት ውስጥ እንዳለ የሚገልጽ ነው ሲሉ አንዳንድ የውስጥ አዋቂዎች ይናገራሉ። በተለይም ተማሪዎቹ ባነሱት ተቃውሞ ላይ ሕወሓት ጠፍጥፎ የሰራው ኦሕአዴድ አባላት አቋማቸው ለ2 መከፈሉን የደረሰን መረጃ ያመለክታል።

ተጨማሪ ያንብቡ:   የትግራይ ሕዝብ የኛ ወገን ነው - ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ

1 Comment

  1. TemariwOchachin yemimekrachihu 1 hunu. Betleyayu negrooch, bezer behaymanoot atleyayu. Yeskezare ciqona befetari hayil maktemiyawu new. Beslfochu wusti andand sihtetoch linoru yichilalu. Inezeh sitetooch besecurity hayiloch aliyam be andandi qimegna gileseboch lihn yichilal. Yihe chanse ye Ethiopiaan hizb mamlete yelebeteem. Tiglu more yeteqenaaje endihn Facebook fiteru, lememekakriya.

Comments are closed.

Share