ከሰማያዊ ፓርቲ የሰላማዊ ሰልፍ አስተባባሪ ኮሚቴ ለመምህራን የተላለፈ ጥሪ

April 21, 2014

ለተከበራችሁ የኢትዮጵያ መምህራን በሙሉ!!! ለአንድ አገር ብልጽግና ትምህርት ቁልፍ ስለመሆኑ ለማንም አጠያያቂ አይደለም፡፡ ለዚህም ሲባል መንግስታት ለትምህርት የሚሰጡት ትኩረት በቀዳሚነት ቦታ ላይ ይገኛል፡፡ በአገራችን ያለው ነባራዊ ሁኔታ ግን ከዚህ ጋር በእጅጉ የሚቃረን ነው፡፡ የትምህርት ፖሊሲ ከመቸውም ጊዜ በባሰ ሁኔታ ለእናንተ ለመምህራኖች የማያሰራ፣ ብቁ የተማረ ዜጋ የማይፈራበትና ለአገርም የማይጠቅም ሆኗል፡፡ ሁሉንም ነገር ለስልጣናቸው በሚያመች መልኩ የሚዘውሩት የወቅቱ ገዥዎች ትምህርት ከንጉሱና በደርግም ጊዜ ከነበረው በባሰ ደረጃ እንዲገኝ አድርገውታል፡፡

ውድ የአገራችን መምህራኖች፤ በአሁኑ ወቅት መምህር በደርግና በኃይለስላሴ ዘመን ከነበረው ክብር ስለመውረዱ ከእናንተ ውጭ እማኝ መጥራት አያስፈልግም፡፡ መምህራኖች በማስተማር ብቃታቸውና ትምህርት ደረጃቸው፣ በስራ ዘመናቸው፣ በአጠቃላይ ለቀጣዩ ትውልድና ለአገራቸው በሚያበረክቱት ሳይሆን ለስርዓቱ ባላቸው ቅርበትና ርቀት እንደሚመዘኑም እናንተው ራሳችሁ የምታሳልፉት የዕለት ተዕለት ጭቆና በመሆኑ ሀቁ ከእናንተ የተደበቀ አይደለም፡፡

በስራችሁ ላይ የሚደረግባችሁ ጣልቃ ገብነት ተባብሶ መቀጠሉም የአደባባይ ሚስጥር ሆኗል፡፡ የገዥው ፓርቲ ያልተማረ ካድሬ ከእናንተ የተሻለ ተጠቃሚ በሆነበት አገር መጭውን ትውልድ የምትቀርጹት እናንተ መምህራን ግን ኑሮን ለመግፋት ተቸግራችኋል፡፡ በደሞዝ ጭማሬ ስም የ70 ብር ያልበለጠ ጭማሪ ልክ እንደ ቀሪው ጭቁን የኢትዮጵያ ህዝብ በእናንተም ላይ ስርዓቱ እየቀለደ ቀጥሏል፡፡ በነጻነት ለማስተማር አለመቻላችሁና እንዲሁም የሚገባችሁን ክብርና ክፍያ ባለማግኘታችሁ ተሸማቅቃችሁ እንደምትኖሩ የታወቀ ሀቅ ነው፡፡

መምህር ለራሱ ብቻ ሳይሆን አገሩንና ቀጣዩን ትውልድም የሚቀርጽ ፈጣሪ የማህበረሰባችን ክፍል ነው፡፡ ሆኖም የኢትዮጵያ መምህራን ስለ ራሳችሁ መብት እንኳ ጮኽ ብላችሁ ስትከራከሩ፣ ስታስተምሩ አይታይም፡፡ ከስርዓቱ አፋኝነት አንጻር ለእናንተ የሚከራከሩ ማህበራትም የሉም፡፡ በጣም የሚያሳዝነው በ1960ዎቹ እነዚህ ማህበራት ለአባላቶቻቸው ከመቆም አልፈው ለአገራቸው ህዝብ ድምጽ እንደነበሩ ስናስብ ነው፡፡ በዛ ዘመን ከየትኛውም ተቀጣሪ በላይ ሲከበርና ሲከፈለው የነበረው መምህር ‹‹እኔ ተጠቃሚ ነኝ!›› ብሎ የህዝቡን ችግር ጀሮ ዳባ ልበስ ብሎ አላለፈም፡፡

በአሁኑ ወቅት እናንተም ችግር ውስጥ ወድቃችሁ፣ አገራችንም በሚያሳዝን ምስቅልቅል ላይ ሆና ድምጻችሁ አይሰማም፡፡ መብታችሁ ሲነጠቅ፣ ህዝብ መብቱን ሲቀማ፣ ከቀዬው ሲፈናቀል፣ አገራችን ስትዋረድ….በርካታ በደልና ግፍ ሲደርስ ማስተማር፣ መተቸት፣ ጮህ ብሎ መናገር የነበረበት መምህር የጋን መብራት ሆኗል ማለት ይቀላል፡፡

ፓርቲያችን ሰማያዊ መምህራንን ጨምሮ የአገሪቱ ህዝብ በአሳዛኝ ጭቆና ላይ በመሆኑ የተነጠቁትን መብቶች ለማስመለስ ሚያዝያ 19/2006 ዓ.ም ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ ጠርቷል፡፡ በዚህ ሰልፍ የተነጠቃችሁትን የማስተማር ነጻነት፣ ክብር፣ እንዲሁም እንደ አንድ ኢትዮጵያዊ ዜጋ ያጣችኋቸውን መብቶች ጮህ ብላችሁ እንድትናገሩ፣ ህዝብ መብቱን በነጻነት መጠየቅ እንደሚችል እንድታስተምሩ ጥሪ አቅርቦላችኋል፡፡ መምህር የጋን መብራት በሆነባት አገር ትውልድ ወደባሰ ጨለማና ጭቆና ማምራቱ የማይቀር በመሆኑ መምህራን የሙያም ሆነ አገራዊ ግዴታችሁን በመወጣት የእናንተንም ሆነ የቀሪውን ኢትዮጵያዊ ወገናችሁን መብት ለማስመለስ በምናደርገው የትግል ጉዞ ግንባር ቀደሙን ስፍራ ይዛችሁ ህዝብ እንድታታግሉ በድጋሚ ጥሪ እናቀርባለን፡፡

 

3 Comments

  1. Semayawi minamin yemiluachu astelita partiwoch hulu gedel gibu ebakachu. Kesiriatu meraranet belay yastelagn yenante asabi-mesaynet new. Ene betam taketegn mesmat ke 97tu mircha yetemarnew neger binor egnan meswat adirgo enante litekem baynet new. Yih sirachu degmo ahun goltual. Silezi kurtegna akuam eskelelachu dires andim memhir ejun endemayasgeba emenu. Asibu memhir mogn adelem. Beterefe silechigrachu lemawurat kefelegachu be email enawura

    • Yetebalew bemulu tikikil new. Semayawiwoch. Enezih sewoch ende qircha siga kefafilewon mebtachinin regtew hod aderi beltew yemaytegbu kadirewochin medibewbin yemnagarewun yeteqawami targa eyeletefubet beafena eyegezun mehonu yeadebaby mistir new. Mebtachin sigefa, hager bemaytegbu jiboch sitizeref besirachin talqa gebtew endashachew sifenechu befrihat quch bilen eyayen new. Gin eske meche? Firihatna zimita keto mefthe lihon ayichlim. Lembtachin entagel mot mechem aykerim. Befirihatim eyemtin eko new. Dimokrasi, fitih nafeken gin dabo aydelem aytadelim joro yalew yisma!!

Comments are closed.

Previous Story

ስለፍትህ ሲባል ስርዓቱ ይፍረስ! ፫ (ተመስገን ደሳለኝ)

Next Story

ምክር ለሰማያዊ ፓርቲ (በክፍያለው ገብረመድኅን)

Latest from Blog

አዲስአበባ ተኩስ ተከፈተ “ለመደራደር ዝግጁ ነን” አረጋ ከበደ | አብይ አደገኛውን ካርድ መዘዙ | አዲሱ አዋጅና የቀረበበት ተቃውሞ “የሞተም ሰው ንብረት ይጣራል | ጌታቸው ያጋለጠው ጸብ

አዲስአበባ ተኩስ ተከፈተ “ለመደራደር ዝግጁ ነን” አረጋ ከበደ\  አዲሱ አዋጅና የቀረበበት ተቃውሞ “የሞተም ሰው ንብረት ይጣራል አብይ አደገኛውን ካርድ መዘዙ ጌታቸው ያጋለጠው ጸብ

ከመጠምጠም መማርን እናስቀድም!

;በላይነህ አባተ (abatebelai@yahoo.com) አብዛኛው አንባቢ ተገንዝቧል ብዬ እንደምገምተው ሕዝብ ለቡና ቲራቲም፣ ለግብዣ፣ ለበዓል፣ ለሰረግ፣ ለሐዘን፣ ለእድር፣ ለእቁብ ለውይይትና ለሌሎችም ማህበረሰባዊ ጉዳዮች ሲገናኝ የሚበዛው አድማጭ ሳይሆን ተናጋሪ  ወይም ደግሞ ለመናገር  መቀመጫውን ከወንበር ወይም
Go toTop