የሚሊዮኖች ድምፅ ለመሬት ባለቤትነት” በሚል መሪቃል በደሴ የተደረገው የተቃውሞ ሰልፍ በተሳካ ሁኔታ ተጠናቋል

Millions of voices for freedom – UD

የሚሊዮኖች ድምፅ ለመሬት ባለቤትነት” በሚል መሪቃል በደሴ የተደረገው የተቃውሞ ሰልፍ በተሳካ ሁኔታ ተጠናቋል፡፡ በስፍራው የሚገኙት የአንድነት ፓርቲ ከፍተና አመራሮችና የዞን አመራሮች በሰልፉ ለተሳተፈው የደሴ ህዝብ ምስጋና አቅርበዋል፡፡ #Dese #UDJ “እድሜ ለአንድነት አስተነፈሰን” የደሴ ነዋሪ.  ይህ ሁሉ አልፎ ዛሬ ህዝቡ በነቂስ ወጥቶ በአስተዳደሩ ላይ በተለይም በመሬት ይዞታ ባለቤትነት ጉዳይ እና አላግባብ ስለታሰሩት ኢትዮጵያውያን ድምጹን ከፍ አድርጎ እያሰማ ይገኛል:: ሰላማዊ ሰልፉ እንደተጀመረ ፖሊስ መንገዱን በመዝጋት ሰልፈኛውን ለማወክ ጥረት አድርጎ ነበር:: ህዝቡ ግን ፖሊስን እየጣሰ ሰልፉን በሰላማዊ መንገድ እያደረገ ነው::

የደሴው ሰልፍ በተሳካ ሁኔታ እየተካሔደ ቢሆንም የአዲስ አበባው ዋና ጽ/ቤት ከፍተኛ በሆነ የፖሊስ ሀይል ተከቧል፡፡

ተቃውሞ ሰልፍ ላይ ከሚስተጋቡ መፈክሮች ውስጥ
– መሬት ለህዝብ ይመለስ
– ጭቆና በቃን
– ድል የህዝብ ነው
– በግፍ የታሰሩ ይፈቱ

– አንድነት ኃይል ነው
– የፖለቲካ እስረኞች ይፈቱ

 

ተጨማሪ ያንብቡ:  ሙስሊም ወጣቶች ከደቡብ ወሎ እየተሰደዱ ነው

3 Comments

  1. Proud of you, Dessie. United we are stronger and remove this dictatorial regime that has consumed millions of our youths in cold blood. They would not see the date of the coming election. They would disappear in a tandem. No retreat No surrender!

  2. ሰላማዊ ሰልፍ ማድረግ መቻልን ልክ እንደ ልዩ ችሎታ አድርጎ ማቅረብ መሞከር እጅግ በጣም ያሳዝናል፥፥ ወያኔ የኢትዮጵያን ሕዝብ በአስከፊ 23 የግዛት ዓመታት ውስጥ የፈለገውን በአደባባይ ገሎ፣ ኦሮሞው ለኢትዮጵያ አገሩ ደህንነት ከሌሎች ወንድሞቹ ጋር በመሆን አቅሙ የቻለውን ያህል መስዋዕትነት እንዳልከለ ሁሉ በሆነ ባልሆነው ኦነግ ነህ እየተባለ (ለእንግልቱም ኢትዮጵያዊነቱ ተነፍጎት) መንገላጋቱ፣ አማራው ትምክዕተኛ እየተባለ በጠላትነት በሚሳደድበት ግዜ እንዴት ሰላማዊ ሰልፍ ማድረግ መቻልን እንደ ልዩ ችልታ አድርጎ ማቅረብ ለምንስ አስፈለገ???
    በርግጥ ይህንን ስል ሰላማዊ ሰልፈ ማካሄዱ በራሱ ፈታኝ መሆኑን መገንዘብ ተስኖኝ ሳይሆን ከሰላማዊ ሰልፍ ባሻገር በብርሀን ፍጥነት የባንዳዉን የወያኔ ስረአት አሽቅንጥሮ ለመጣል የሰላማዊ ሰልፍ ማካሄድን እንድ አንድ ስልት እንጅ እንደ ግብ መታየት የለበትም ካለበለዚያ ይህ ለወያኔ እንደማስተንፈሻ ቆጥሮት እቃቃ ጨዋታ እንዳይሆን እንዳንዘናጋ ለማለት እንጅ ሰላማዊ ሰልፉም ዘንቦ ተባርቆ መሆኑን ሁላችንም የምናቀዉ ሀቅ ነዉ!!!

    ድል ለኢትዮዽያ አንድነት!

Comments are closed.

Share