የወንድማችን ግርማ የሺጥላን ነፍስ ነጥቀዋል- ጠ/ሚ ዐቢይ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 19፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የአማራ ክልል ብልጽግና ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ የነበሩት ግርማ የሺጥላ ህልፈት የተሰማቸውን ሃዘን ገልጸዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት የሀዘን መግለጫ ፥“ሐሳብን በሐሳብ ማሸነፍ ያቃታቸው አካላት የወንድማችንን የግርማ የሺጥላን ነፍስ ነጥቀዋል” ብለዋል።
ልዩነትን በሠለጠነ መንገድ መፍታት ባህል በሆነበት ክፍለ ዘመን፣ በሐሳብ የተለየንን ሁሉ በጠመንጃ ለማሳመን መነሣት የጽንፈኝነት የመጨረሻው ጥግ ነው ሲሉም ገልጸዋል።
ተወልዶ ባደገበት አካባቢ፣ ከእኛ የተለየ ሐሳብ ማሰብ አልነበረበትም ብለው የሚያምኑ ነውጠኛ ጽንፈኞች የፈጸሙት አስነዋሪና አሰቃቂ ተግባር መሆኑን አንስተዋል፡፡
ጽንፈኝነትን በጊዜ ታግለን ካላስወገድነው ወደ መጨራረስ እንደሚወስደን ጉልሕ ማሳያ ነው ሲሉም አጽንኦት ሰጥተዋል።
Source:  Fana
ተጨማሪ ያንብቡ:  በሰሜን ሸዋ ዞን የተፈፀመውን ጥቃት የሚያወግዝ የተቃውሞ ሰልፍ በደብረ ብርሃን ከተማ ተካሄደ

10 Comments

 1. ቀድመህ ስላለቀስክ እጅህ ንፁህ ነው ማለት አይደለም።
  ባለፉት አምስት ዓመታት ካየናቸው ድራማዎች አንፃር የአቶ ግርማ የሺጥላ አሟሟትም የቁማሩ ቀጣይ ክፍል እንጂ የተለየ እንደማይሆን እገምታለሁ።
  ነፍስ ይማር!

 2. እንዴ ባለፈው ዶር በሉኝ ሲለን የነበረው አይደለም እንዴ ምን ነካው? በዚህ ጉዳይ ላይ ጌታቸው ረዳ ወይ ሽመልስ አብዲሳ ሊኖሩበት ይችላሉ ለማንኛውም ጥናት እናካሂዳለን።

 3. እኔ ወታደር ነኝ። ጄኔራል ነኝ። መለዮን ጥየ ሲብል ልብስ ለብሼ ነው የመጣሁ። ለምንድን ነው? እንደ አንድ የኦሮሞ ልጅ መሳተፍ ሥለምፈልግ ነው። እኛ እየሰራን ያለነው ለኦሮሞ ጥቅም እና ክብር ነው። ጠቅላይ ሚኒስቴር ዶር አብይም የሚሰራው ለኦሮሞ ክብር እና ጥቅም ነው። የሚቻል ከኾነ በምሥራቅ አፍሪካ በወታደራዊ አደረጃጀት፣ በኢኮኖሚ፣ በዲፕሎማሲ እና በፖለቲካው የታፈረች እና የተከበረች ታላቋን ኦሮምያ ሀገር ለመመሥረት ነው የምንሠራው። ይህንን ካልቻልን ግን በኦሮሞ ፍላጎት ብቻ የምትተዳደር ኢትዮጵያን እንመሠረታለን። ኹላችሁም የኦሮሞ ልጆች አግዙን። ”

  ብርሃኑ ጁላ ደብረ ዘይት ስብሰባቸው ላይ ከተናገረው!

  እና ይሄ ሰውዬ ከሁሉም አቅጣጫ ለመጣው የመከላከያ ሰራዊት አባላት መሪ ነው? አመራሩስ ፍትሀዊ ይሆናል?

  • ጁላ መች የብሄራዊ መከላከያ መሪ ነኝ አለህ? ነኝ ባላለው ለምን ትከስዋለህ የኦሮሞ ነኝ ነው ያለው። የኢትዮጵያ መከላከያ መሪዎቹ አብረሃ በላይ(ህወአት) አብይ መሃመድ(ኦነግ) ብርሃኑ ጁላ በሞጋሳ ኦሮሞ የሆነ የከምባታና ሃድያ ሰው ሲሆን ጄነራል አበባው ትግሬ ነው ይባላል አገውነቱን ግን እሱም ተቀብሏል። ስለዚህ ጦሩ የፌደራል ቢሆንም መሪዎቹ ግን ፌደራሉች አይደሉም።

 4. ሰውየው ሀገር የመምራት ብቃት ባይኖረውም ሰውን የማስገደል ብቃት አለው. ስመኘው በቀለን, አምባቸውን , አሳምነው ፅጌን, ሳእረ መኮንን, ሃጫሉ , ግርማ የሽጥላ ገና ይቀጥላል.

  • Deru ድሩ ነህ ደሩ ከስር ባማርኛ ጽፈህ ከላይ ላቲን ለመን አስፈለገህ ይመችህ ብሮ ነገርን ቀለል ማድረግ ነው።
   ሳእረ መኮንንን ሚስቱ ነች ይባላል የገደለችው ጄነራል ገዛይም ነው ይባላል እንደ ጥላሁን ገሰሰ ሞት ድፍን ያለ ነገር ነው ገዛይም እሱ ቤት መልከስከስ ይወድ ነበር ይላሉ ትግሬዎች ብቻቸውን ሲያወሩ። ሃጫሉን ጁዋርና ሽመልስ ናቸው ያስገደሉት ይባላል። ሁሉንም ኮለኔሉ ላይ ማሳረፍ አግባብ አይሆንም ከሚገባው በላይ ወንጀል ስለሰራ ትንንሿን ሌሎች ይረክቡት።

   ወይ ጉድ አሳምነው ላይ ሲውረገረጉ የነበሩት እወደድ ባዮች በተራ ተራ እየተለቀሙ ነው ማለት ነው? ቀጥሎ የአሩሲ ኦሮሞ፤የሃረር ኦሮም፤የባሌ ኦሮሞ፤የጅማና የኢሉባቦር ኦሮም እያለ የወለጋው ኦሮሞ ላይ ይነሳል ትንሽ መጠበቅ ነው። እነ ሽመልስ ቀረጣጥፈው የጦቢያን ሃብት ሲበሉ እነ መራራ ጉዲና፤እነ በቀለ ገርባ እነ ዳውድ ኢብሳ ከመረቁ ያንሳቸዋል? ታየ ደንዳስ ላይ ሰላም ሳይኖር የሰላም ሚኒስቴር ሁነሃል ብሎ ሰው ላይ ማላገጥ ምን ይሉታል? አቶ ታየ ሊያብድ ነው ይላሉ ምንም ስራ የለውም ጋዜጣ ይሰጠዋል ጋዜጣው ላይ አይኑን ተክሎ ሽመልስ የሰራውን ስራ ሲያብሰለስል ጊዜው ይሄዳል። ዛሬ ዋነኛዋ ሰው አዳነች አበበች ነች የ350000 ቀሚስ መልበሷን ስንቱ ሰው ያውቃል? አሁን ትላንት ከአሩሲ የመጣች ሴት ትመስላለች? አሁንማ አካሄዷ እራሱ አንጀሊና ጆንስን መስሏል ቀደም ሲል እንደሷ በድመት እርምጃ የሚወረገረጉት ክብርት መአዛ አሸናፊ ነበሩ ዛሬ ላይ ምን እንደሆኑ ባላውቅም። እረ ይመቻቸው ለመግዛት የተመቸ ህዝብ ነው

 5. አይ አብይ አህመድ ጅራፍ ራሱ ገርፎ ራሱ ይጮሃል: ገድዩ እኮ አንትው ራስህ ነህ: አይ ኬኛ እያረዳችሁም የሰው ሞት ትነጥቃላችሁ ለነገሩ እናንተ ምን አለባችሁ ብታርዱም ብታቃጥሉም ባለጊዜ ናችሁ ማን ይቃወማችኋል ?

 6. ጁላ መች የብሄራዊ መከላከያ መሪ ነኝ አለህ? ነኝ ባላለው ለምን ትከስዋለህ የኦሮሞ ነኝ ነው ያለው። የኢትዮጵያ መከላከያ መሪዎቹ አብረሃ በላይ(ህወአት) አብይ መሃመድ(ኦነግ) ብርሃኑ ጁላ በሞጋሳ ኦሮሞ የሆነ የከምባታና ሃድያ ሰው ሲሆን ጄነራል አበባው ትግሬ ነው ይባላል አገውነቱን ግን እሱም ተቀብሏል። ስለዚህ ጦሩ የፌደራል ቢሆንም መሪዎቹ ግን ፌደራሉች አይደሉም።

 7. ተጠርጣሪ አብይ አህመድ: ተነሳሽነት፣ ዘዴ (መሣሪያ) እና ዕድል?

  ለምን? እንዴት? መቼ ነው?
  ነፍሰ ገዳዩ ማን እንደሆነ ለማወቅ እነዚህ እንደ ቁልፍ ጥያቄዎች የሚነሱ ናቸው።
  ሦስቱ ጥያቄዎች በሌላ አነጋገር ተነሳሽነት፣ ዘዴ (መሣሪያ) እና ዕድል ተብለው ይገለጻሉ።
  አብይ አህመድ በግድያው ተጠርጣሪ ከሆነ ባሕርይና ድርጊቱ ሶስቱን ጥያቄዎች ያረካ እንደሆነ እንመለከታለን።

  ተነሳሽነት
  የአብይ ወቃታዊ ትኩረት ከሆነውና አማራውን ትጥቅ ለማስፈታት ከወሰደው እርምጃ አንጻር ግድያው በአማራ ክልል ላይ አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ለማወጅ እና በአማራው ላይ የጀመረውን ጦርነት ማባባሻ ነው።
  ቀድሞውንም አብይ 200ሺህ የሚያህል ሰራዊት በአማራ ክልል እና አካባቢው አስፍሮ የእሱን ትእዛዝ እየጠበቀ ነው። የአማራ ክልል በሺዎች የሚቆጠሩ የልዩ ሃይሎች እና የስለላ ሰራተኞች መጨናነቅም ሲነገር ቆይቷል። የዐማራው ታጣቂዎች እስከ አሁን ድረስ አብይን ሙሉ ጦርነት ሊያውጅባቸው የሚያስችል ሰበብ ነፍገውታል። ስለዚህ አማራውን ትጥቅ የማስፈታት ዘመቻውን ከፍ ለማድረግ የሚያስችል ሰበብ ለመፍጠር አላማ አለው።
  ማለት ነው። በግርማ የሺጥላ ግድያ አትራፊ የሚሆን ለመሆንም በብርሃን ፍጥነት እየተንደረደረ መሆኑ ግልጽ ነው።

  ዘዴ/መሣሪያ
  አቢይ ከመትረየስ እስከ ሰው አልባ አውሮፕላኖች ድረስ – ግርማ የሺጥላን ከነአጃቢዎቹ ምንም አይነት ማስረጃ ሳያስቀሩ ተኩስ ከፍቶ ለማውደም አቅሙ አለው። የአማራ ክልል በተለይም ሸዋ ኦህዴድ የሚመራው መከላከያን ጨምሮ በኦህዴድ ወታደራዊ እና የመረጃ ሃይሎች ተጨናንቋል።

  ዕድል
  ግሪማ የሺጥላ በአብይ የሪፐብሊካን ጋርድ (ከኦሮሚያ ልዩ ሃይል በተጨማሪ) ጥበቃ ሥር ስለነበረ አብይ አህመድ ይህን ወንጀል ለመስራት ሰፊ እድል ነበረው።

  ለእነዚህ ጥያቄዎች የተጠርጣሪውን የኋላ ታሪክ ማከል እንችላለን።
  ጠ/ሚኒስትር ሆኖ በቆየበት አምስት አመታት ውስጥ፣ አብይ በተለያዩ ግድያዎች እጁ አለበት፡-
  1. የአማራ ክልል ፕሬዝዳንት አምባቸው መኮንን
  2. የአማራ ክልል የጸጥታ ኃላፊ ጄኔራል አሳምነው ጽጌ
  3. የአማራ ክልል ጠቅላይ አቃቤ ህግ አቶ ምግባሩ ከበደ
  4. የGERD ዋና ኢንጂነር ስመኘው በቀለ
  5. የጦር ሰራዊት አዛዥ ጀነራል ሰዓረ መኮንን
  6. አርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ
  በአንድም ሆነ በሌላ መንገድ ከላይ የተጠቀሱት ሰዎች በአብይ ዘንድ ለስልጣን መጠናከር እንቅፋት ተደርገው ይታዩ ነበር። ሀጫሉ በህይወት ቢኖር ኖሮ የአብይ ከህወሓት ጋር ዳንኪራ እና ኮክቴል ፓርቲ ከፍተኛ ተቃውሞ ይገጥመው ነበር፥ አርቲስቱ እንዲህ አይነት የፖለቲካ ዝሙትን በግልፅ አውግዞ ነበር።

  ከላይ የተገለጹት ግድያዎች እና የግሪማ የሺጥላ ግድያ ከአብይ ባህሪ ጋር ምን ያመሳስላቸዋል?
  በሁሉም ጉዳዮች አብይ ከሳሽ፣ ምስክር እና ዳኛ ነበር።
  ግድያው ከተፈፀመ በኋላ ወጥቶ ገዳዩ ማን እንደሆነ፣ ዓላማው ምን እንደሆነና ምን ዓይነት ፍርድ እንደሚገባው ይጠቁማል። አቢይ ይህን የሚያደርገው ገና በገለልተኛ አካል ምርመራ እና ፍትሃዊ አሰራር እውነታውን እና ትክክለኛ ፍትህን ለማስገኘት ምንም ጊዜ ሳያባክን ነው።

  ከላይ የተገለጹት ግድያዎችን እና የግሪማ የሺጥላን ግድያ ከኦህዴድ የሴራ ታሪክ አኳያ ምን ያመሳስላቸዋል?
  ኦህዴድ የህወሓትን አስነዋሪ ሃውዜናዊ ስትራቴጂ ገልብጦ የተካነበት መሆኑ ይታወቃል። ሃውዜናዊ ስትራቴጂ ምንድን ነው? ይህ በኢትዮጵያ ፖለቲካ የፈጠራ ባለቤትነት መብቱ የሕወሃት የሆነ እኩይ የሴራ ስልት ነው። ስልቱ የራስን ካምፕ ማጥቃት እና ጠላት ጥቃቱን እንደፈፀመ እንዲመስል ጉዳዮችን ማቀናበር ሲሆን በዚህም ምክንያት በሚፈጠረው ቁጣ፣ ብስጭት እና የበቀል ስሜት ራሳቸው አጥቂዎቹ ተጠቃሚ ይሆናሉ። የሴራ ስልቱ ስሙን ያገኘው ህወሓት የማዕከላዊ እና ደቡብ የትግራይ ተወላጆችን ለዓላማው ለማሰባሰብ ባደረገው አስነዋሪ የሀውዜን እልቂት ነው። ስልቱን ህወሓት ብዙ ጊዜ ተጠቅሞበታል።
  ኦህዴድ በህወሀት እንደተፈለፈለ እና እንደተቀፈቀፈ ጫጩት ድርጅት ሃውዜናዊ ስትራቴጂን በአግባቡ ተጠቅሞበታል። እንደውም ድርጅቱ ይህን ስልት አዘውትሮ ከመጠቀሙ አንፃር OPDO የዚህ ደባ ሱስ ሆኗል ማለት እንችላለን። የኢሬቻ እልቂት በራሱ በስትራቴጂ ፈጣሪው በሕወሃት ላይ የተፈፀመ የኦህዴድ ሃውዜናዊ ስትራቴጂ ሴራ ትግበራ መሆኑ ይታወቃል።

  ስለዚህ በአብይ አህመድ ወይም በኦህዴድ የተፈፀመ የግርማ የሺጥላ ግድያ ከዚህ ሃውዜናዊ የወንጀልና እና በገዛ ወንጀል ተጠቃሚነት ስትራቴጂ ጋር ይስማማል።

 8. Liar and fascist abiy ahmed is trying his best to incriminate Mere Wodajo in the death of Hode Ader Girma. Of course using the technology of DEEP FAKE in which the voice of a person is digitally altered so that it appears to be someone else`s, typically used maliciously.`

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share