ከአማራ ክልል የወጡ አዳዲስ መረጃዎች! | ከይልቃል ከፋለ እና ጌታቸው ረዳ መተቃቀፍ ባሻገር!

ከአማራ ክልል የወጡ አዳዲስ መረጃዎች! | ከይልቃል ከፋለ እና ጌታቸው ረዳ መተቃቀፍ ባሻገር!

The photo says everything

 

 

 

ተጨማሪ ያንብቡ:  አሜሪካን እየወጋችን ነዉ! (መኮንን ብሩ)

5 Comments

  1. እግዚኦ ትንሽ እፍረት የለም እንዴ? ጎበዝ 1 ሚሊየን ወጣት እኮ ነው የረገፈው? ኧረ ምን እየተደረገ ነው? ዜጋ ነው እንስሳ ነው ያለን። እኛ ባንሞትም የሞቱት እኮ ወንድሞቻችን ናቸው ሞታቸውም ከላይ በሚተቃቀፉ ሰዎች ምክንያት ነው።

  2. ይልቃል እንዴት እንደሚቀልዱብህ ከዚህ ፎቶ መገንዘብ ትችላለህ ሆድህ ካልበለጠብህ።

  3. ሬድዋን ሁሴን አምበሳ የገደለ አይመስልም የቀድሞ ጌቶቹ ዘንድ ሲቀርብ ድረቱን ነፍቶ አይኑን አቁለጭልጮ? በጦርነቱ ጊዜ የህወአት ቁልፍ መረጃ አቀባይ ነበር ይሉታል። ኤርትራ በተሾመበት ዘመን ብቃት የሌለው ነው ተብሎ አፈወርቂ አልቀበለው ብሎ አዝነው ነው የመለሱት እሱ ረስቶታል እኛ ግን ስለሱ አዝነናል። በተመሳሳይ ሁኔታ ታየ ደንዳን ሚኒስቴር ያለ ፖርትፎሊዮ ሹሞት ይቀልድበታል የሚቀርቡት ሰዎች ጭንቅላቱ ተነክቷል ይላሉ ዛሬ ዛር የቆመላቸው ሽመልስ አብዲሳ፤ታከለ ኡማ፤አዳነች አቤቤ፤አዲሱ ቂጤሳ ሁለቱ ሌንጮዎች፤ ግሪሳ (ጁዋር መሃመድ) ናቸው እስቲ የነገውን ማን ያውቃል?

  4. አብይ አስገድዶት ነው ወይስ የይልቃል ምርጫ ነው ወደ መቀሌ መሄድ? ሰዎቹ ለስማቸውም አይጨነቁም ማለት ነው? የሽመልስና የአዳነች አቤቤ እንደዛ ፍንድቅድቅ ማለት ምንድነው ኦነግ እያለ መከራውን ሲያበላው የነበረው ትህነግ አልነበረም እንዴ ሽመልስ ባይታሰር ለታየ ደንዳ፤ለበቀለ ገርባ፤ ይፈታ ብለን በሃሩር በብርድ እየተንዘፈዘፍን ዋይት ሀውስ ቁመናል እኮ አማራ ኦነግ ሆንክ ብሎ እኮ አጠገብህ አልደረሰም ነገር ሁሉ የተምታታባችሁ ፍጥረቶች።

  5. ትላንት ዛሬ አይደለም ዛሬም ነገ አይሆንም
    ህልም አለን ብላችሁ ቅዥትን አታውሩ
    እውን የሚሆነው ራእይና ህልሙ
    ለገባቸው ብቻ ነው ተኝተው ለነቁ
    ኣይናቸው ተከፍቶ ዙሪያቸውን ላዪ፡፡
    ዝንተ ኣለም የመወነጃጀልና የመገዳደል ፓለቲካ ይኸው ያኔም አሁንም ይንጠናል፡፡ ችግሩ ገዳዪና የተገዳዪ ወገኖች አብረው መላቀሳቸው ነው፡፡ ሰውን ጠፍረው ይዘው እየደበደቡ ኡኡታ በማሰማት ኑና ገላግሉኝ የሚሉ ተልካሻ ፓለቲከኞች የፈሉባት ምድር ናት፡፡ በሌላው ላይ በይፋ ጀኖሳይድ ያደረሰው ሃይል ጀኖሳይድ ደረሰብኝ እያለ ማቆሚያ የሌለውን ጩኸት ያሰማል፡፡ በአዲስ አበባና በሌሎች የኦሮሞ ክልሎች ዙሪያ የደረሰው በደልና ግፍ አፍንጫቸው ላይ እያለ የኦሮሞ መርጦ አልቃሽ ፓለቲከኞች መቀሌ ላይ ሂደው ሲቀባጥሩ መስማት ምን ያህል ፓለቲካው ከሰውነት የወጣ እንደሆነ ቁልጭ አድርጎ ያሳያል፡፡ የትግራይ ህዝብ ችግር ወያኔ ነው፡፡ ወያኔ ከጀርባው ላይ ከወረደ የትግራይ ህዝብ በራሱ አስቦና ሰርቶ የሚኖር ለሌላው ወገኑ ደራሽ ህዝብ ነበር አሁንም ነው፡፡ የመቀሌው ድራማ ከእውነት የራቀ የፓለቲካ ትወና ነው፡፡ አቶ ጌታቸው ረዳን ቆንጮ ያደረገው የወያኔ ስብስብ በአፋርና በአማራ ክልል ላደረሰው በደልና ዝርፊያ ማንም ሳይጠይቀው አሁን በጠ/ሚሩ አመራርና በአሜሪካ መሪነት ሁሉም ነገር ወደ ትግራይ መባሉ የፓለቲካውን የማያባራ የመከራ ዝናብ ያሳየናል፡፡ በዚህ ሁሉ ግርግር የግርማ የሺጥላም መገደል ዝም ብሎ በነሲብና በገጠመኝ የሆነ ሳይሆን በተሰላ መንገድ የተከናወነ ነው፡፡ ሲጀመር ፓለቲካችን ሸፋፋ ነው፡፡ ገድሎ በሟች ስም መንገድ ይሰይማል፤ ሃውልት ያቆማል፤ ት/ቤት ያሰራል፡፡ እንዲህ ያለ የእቃ እቃ ጫወታ ቆይቶ መፈራረሱ አይቀሬ ነው፡፡
    ትላንት በወያኔና በድህነት ፓርቲ መካከል የነበረውን የሰው እልቂት እያገዘፉና ያለ የሌለውን ሁሉ በየሶሻል ሚዲያው እየለጣጠፉ በሰው ደም ሽርፍራፊ ሳንቲም ሲለቅሙ የነበሩ የቁም ሙቶች አሁንም በዚህም በዚያም መላ በመምታት ሰው ከሰው ጋር ለማላተም ምንም እውነትነት የሌለውን ነገር ሁሉ በማሰራጨት የወሬ ንግዳቸውን አጧጡፈውታል፡፡ የህዝብ ደህንነት፤ የሃገር አንድነትና ሰላም ለእነርሱ ግድ አይሰጣቸውም፡፡ የሚተነፍሱትና የሚያስቡት በዘርና በቋንቋ በተገጠመላቸው ሳንባና ጭንቅላት በመሆኑ ጀርመን ላይ ተቀምጦ የሚያቅራራ፤ የራሱን ቤተሰብና ዘርማንዘር እጎኑ ሰብስቦ በለው የሚል የሰው ባህሪ የሌላቸው ተናካሽ ውሾች በውጭና በሃገር ውስጥ እንደ ጉንዳን ፈልተዋል፡፡ ቆም ብሎ ማሰብ፤ ነገርን ማመዛዘን የለም፡፡ ያው የሃገሬ ሰው እንደሚተርተው “በየወገንህ ቢሉት የመቶ አመት ቆዳ ገቢያ ወቶ ቆመ” እንዲሉ በመሆኑ ጊዜው የብሄር ፓለቲካ ልክ ያጣበት፤ ሰው መርጦ የተወለደ ይመስል አንድ ሌላውን የሚኮንንበት የወረፋ ፓለቲካ በጦዘ መልኩ ሃገሪቱን እያመሳት ይታያል፡፡ ለውጥ እናመጣለን ብለው ሃገራቸውን ያፈረሱ እንደ ሊቢያ፤ ሶማሊያ፤ የመን፤ ሶሪያ፤ ወዘተ ምን እንማር የሚለውን ማሰብ የሚሻ ሰው የለም፡፡ ሁሉም እኔ ተጎዳሁ፤ እኔ ተጨቆንኩ፤ እኔ እኔ ብቻ! የእኔ ትውልድና የእኔ ፓለቲካ እኔነትን የሚያሳጣ ሁሉ እውርና ጉንድሽ የሚያደርግ አስተሳሰብ ነው፡፡ ከላይ በስንኝ ለማመላከት እንደሞከርኩት ሰው መከራው እራሱ በር ላይ ደርሶ የቤቱን በር እስካላንኳኳ ድረስ በሌላው ላይ የሚሆነው ሰቆቃና መከራ ምንም አይመስለውም፡፡ ደንዝዟል፡፡ ዋ ነግሬአለሁ በህዋላ የሱዳን እጣ ይደርሰንና መግቢያ እናጣለን፡፡ ሰው በሰውነቱ ይመዘን፡፡ የአፓርታይድ ፓለቲካ ይቁም፡፡ ሰው ብሄራዊ መግባቢያ ቋንቋ ይኑረው፡፡ እባካችሁ ወደ ድንጋይ ዘመን ህዝባችን አትመልሱት፡፡
    በመጨረሻም ግድያው፤ የፓለቲካ መናቆሩ፤ ኡኡታው ይቀጥላል፡፡ እጎኑ 10 ሺህ የሚሆኑ ሰዎች ቤታቸው እላያቸው ላይ ፈርሶና ማንም ሰው ቤት እንዳያከራያቸው በኦሮሞ አክራሪዎች ተባረው ማእድ ማካፈል ገለ መሌ የሚሉት የሽንፍላ ፓለቲካ ሊቀር ይገባል፡፡ በአንድ በኩል እያፈረሱ በሌላ በኩል ገነባን መባሉ የፓለቲካ የገበጣ ጫወታ እንጂ ሌላ ትርጉም የለውም፡፡ የአቶ የሺጥላም ገዳዪች ልክ እንደ እንጂኒየር ስመኘሁ፤ እንደ ጀኔራሎቹ ግዲያን እንደ ቀሩት ሁሉ ከጊዜ ጋር ይረሳል፡፡ ተያዙም ከተባለ በደል ያደረጉትን ሳይሆን ለማጣጫ ፓለቲካ የሚሆኑ የድሃ ልጆች ተፈልገው ዘብጥያ ይወርዳሉ፡፡ ግፍ ሰማይ የነካበት እንደ ሃበሻ ምድር የትም የለም፡፡ ወላሂ ከአሁን በኋላ አማራ አልሆንም እያለች የታረደችው ልጅ ትውስ ትለኛለች፡፡ አይ ፓለቲካ፤ አይ መደመር ድንቄም ትደመር፡፡ መርጦ መደመር፡ መርጦ መቀነስ፡፡ በቃኝ!

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share