April 15, 2023
6 mins read

ʺበቂም፣ በበቀል፣ በጥላቻ ወድቀን ትንሳኤውን እናከብራለን ብንል ለምንም አይጠቅመንም” ብፁዕ አቡነ አብርሃም

Abune Abrham

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የመንበረ ፓትርያሪክ ጠቅላይ ቤተክህነት ሥራ አሥኪያጅ እና የባሕር ዳር ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ ብፁዕ አቡነ አብርሃም ብርሃነ ትንሳኤው የሰላም፣ የሕይወት፣ የጤና፣ የበረከትና የፍቅር ይሆን ዘንድ ተመኝተዋል፡፡
ሕያውን ከሙታን መካከል ስለምን ትፈልጋላችሁ፣ ተነስቷል እንጂ በዚህ የለም፣ የሰው ልጅ በሐጥያተኞች እጅ ተላልፎ ሊሰጥና ሊሰቀል፣ በሦስተኛውም ቀን ሊነሳ ግድ ነው እያለ እንደተናገረ አስቡ፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስን ሞት ይዞ የሚያስቀረው አይደለም ብለዋል፡፡ በሞት ላይ ስልጣን ያለው፣ በሞቱ ሞትን የገደለ፣ በሞቱ ነጻነትን የሰበከ፣ በሲኦል ያሉትን የፈታ ሲኦልን የገለባበጠ፣ ዲያቢሎስን ያሰረ ሕያው ነውም ብለዋል ብፁዕነታቸው፡፡
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ታላቁን ፆም በፆምና በስግደት ካሳለፈች በኋላ የተቀበለውን መከራ በማሰብ ትነሳኤውን እንደምታከብርም ተናግረዋል፡፡ የክርስቶስ ትንሳኤ የሁላችንም ትንሳኤ ነው ያሉት ብፁዕ አቡነ አብርሃም የክርስቶስ ትንሳኤ ሁላችንን ይገዛ የነበረው ሞት የተሸነፈበት ነውም ብለዋል፡፡
ክርስቶስ ለሰው ልጅ ቸርነቱን ያደረገበት፤ በንጹሕ ደሙ የዋጀበትና የራቀውን ሁሉ ያቀረበበት በመሆኑ ትንሳኤውን በልዩ ሁኔታ እናከብረዋለንም ነው ያሉት፡፡ ከእርሱ ጋር ሳለን ደስታና ሰላም አለን፣ በዓለም ግን መከራ አለ ብለዋል፡፡ የዓለምን ፍላጎትና ምኞት ለማሟላት በተሄደ ቁጥር መከራዎች መኖራቸውን ነው የተናገሩት፡፡
አምላክ ዓለምን ያሸነፈበት ጥበቡ እጅግ ድንቅ ነው ያሉት ብፁዕነታቸው የእርሱን ፈለግ የተከተ ሁሉ ዓለምን እና ፈተናዋን ያሸንፋልም ብለዋል፡፡
ክርስቶስ ጦርን በጦር ሳይሆን በፍቅር፣ በሰላም እና በትዕግስት ማሸነፉንም ተናግረዋል፡፡ ክርስቶስ ዓለምን በትዕግስት፣በሰላም በፍቅርና በአንድት እንዳሸነፈ ሁሉ እኛም ሰላም ይኑረን ከዚህ ውጭ ያለው ትርጉም የለውም ነው ያሉት፡፡
ዓለም በጥላቻ ተበክላለች ያሉት ብፁዕነታቸው ብዙዎች በሚያደርጉት አላስፈላጊ ፉክክር ዓለም እየተመሰቃቀለች ንጹሐን እየተገዶ መሆናቸውንም ገልጸዋል፡፡ ትንሳኤውን የምሥራች የምንባባል ሁሉ ለሰለም ቅድሚያ መስጠት ግድ ይላል ነው ያሉት፡፡ መከራ የበዛባትን ዓለም መሻገር የሚቻለው በመደማመጥ፣ በመቀራረብ እና በመነጋር መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ጦርና ጦርነት፣ መግደልና መሳደድ ትርጉም እንደሌላቸውም አስረድተዋል፡፡ አላስፈላጊ ውጣ ውረዶች፣ አላስፈላጊ አሸንፍ ባይነት፣ አላስፈላጊ ስምና ዝና ንጹሐንን እየጎዳ መሆኑንም አንስተዋል፡፡
በቂም፣ በበቀል፣ በጥላቻ ወድቀን ትንሳኤውን እናከብራለን ብንል ለምንም አይጠቅመንም ነው ያሉት፡፡ ከሙታነ ሕሊና መራቅ እንደሚገባ ያሳሰቡት ብፁዕ አቡነ አብርሃም ሙታነ ሕሊና ሰላም የጎደላቸው፤ ከጥላቻ ሌላ የማያውቁ መሆናቸውንም ተናግረዋል፡፡ መተዛዘን፣ በጋራ መብላት እና መጠጣት ግድ እንደሚልም ገልጸዋል፡፡
ከመከራው ለመዳን ማሸነፊያ መንገዱን ከእርሱ እንማርም ብለዋል፡፡ ጥላቻና መጥፎ ሃሳብ በምድር ላይ እንዳይነግሥ ፍቅርን ገንዘብ ማድረግ እንደሚገባም አሳስበዋል፡፡ መልካም ያደረጉት መልካም ትውልድና መልካም ሀገር ማቆየታቸውንም ገልጸዋል፡፡ በሀገሩ ስደተኛ፣ መጻተኛ፣ ተፈናቃይ፣ በስጋት የሚንከራተት እንዳይኖር እና ሰላም ይበዛ ዘንድ ሕያው የሆነውን አምላክ እንጠይቀው ነው ያሉት ብፁዕነታቸው፡፡
በዓለ ትንሳኤው ሲከበር የታመሙትን በመጎብኘት፣ የተራቡትን በማብላት፣ የተጠሙትን በማጠጣት፣ የተቸገሩትን በመርዳት፣ በሰላም እና በፍቅር ሊሆን እንደሚገባም አሳስበዋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

የድሮ መሪዎች ያላደረጉትን ምሁር ጳጳሳቱ ያላስተዋሉትን ከፈረሰች ጎጆ ከባልቴት ቤት ገብቶ ክብሩን ዝቅ አድርጎ ውሀዋን ጠጥቶ ምግቧንም ተጋርቶ ያላለቀሰ ሰው ያንን ትይንት አይቶ ማን ይኖራል ከቶ? በዉሸት ፈገግታ ፊቱን አስመስሎ ፀሀይ የበራበት

ሰው በሰውነቱ – ከ ይቆየኝ ስሜ

የአማራ ፋኖ በጎጃም ምክትል የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ የነበረው እና አሁን ላይ በአማራ ፋኖ በጎጃም የሁለተኛ (ተፈራ ) ክፍለጦር ሰብሳቢ የነበረው ፋኖ ዮሐንስ አለማየሁ በክብር ተሰዋ። የአማራ ህዝብ የተጋረጠበትን የህሎና አደጋ ለመቀልበስ ያለ

ከአማራ ፋኖ በጎጃም የተሰጠ የሐዘን መግለጫ ታጋይ ይሰዋል ትግል ይቀጥላል !

January 22, 2025
ዳግማዊ ጉዱ ካሣ “ይድረስ ለእገሌ” ማለቱ ሰለቸኝና ተውኩት እንጂ ዛሬም መጻፍ የፈለግሁት የአማራን ዕልቂት ለመታደግና የኢትዮጵያን ትንሣኤ ለማብሰር እየተዋደቁ ላሉት ወገኖቼ ነው – በፋኖም ይሁን በሌላ ስም፡፡ ኢትዮጵያን ወደቀደመ ክብሯ ለመመለስ የነገድና

ጀልባዋ አትሰምጥም፤ የሚሰምጥ ግን አለ!

[ማስታወሻ ከፍል አንድ፣ በዘሐበሻ ድረ ገጽ ላይ ኦፍ ጃዋር አንድ ኢትዮጵያ ተብሎ በእንግልዝኛ ወጥቷል] (https://zehabesha.com/of-jawar-and-ethiopia/) ባለፈው ሰሞን፣ ጃዋር መሐመድ ከደረጀ ኃይሌ ጋር  በነገራችን ላይ ክፍል ሁለት ባደረገው ቃለ ምልልስ ላይ ተመስርቼ ገንቢ አስተያየት ጽፌ በኢንግሊዝኛው ዘሐበሻ ድረ ገጽ ላይ አሳትሜ ነበር። አስተያየቴ በዚህ ቃለ ምልልስ

ስለ ጃዋርና ኢትዮጵያ (ክፍል ሁለት)

January 20, 2025 ጠገናው ጎሹ የአቤ ጎበኛው አልወለድም ለወገኖቹ መብት መከበር ሲል ባደረገው ጥረት ምክንያት እንደ ወንጀለኛ ተቆጥሮ ይሙት በቃ በፈረዱበት ጊዜ በምላሳቸው መልካም  አድርጎ ስለ መገኘት እያወሩ በድርጊት ግን ተቃራኔውን የሚያደርጉ ሁሉ

ወዮ ለመከረኛው የአገሬ ህዝብ እንጅ  ታየማ ታየ ነው

መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ “ ሰው የሰነፎችን ዜማ ከሚሰማ ይልቅ የጠቢባንን ተግሣጽ መስማት ይሻለዋል። ”   — መክብብ 7፥5 እስቲ ቆም ብለን በማሰብ  ራሳችንን እንፈትሽ ።  እንደ ሰው ፣ የምንጓዝበት መንገድ ትክክል ነውን ? ከቶስ ሰው መሆናችንን እናምናለንን ? እያንዳንዳችን ሰው መሆናችንን እስካላመንን ጊዜ ድረስ ጥላቻችን እየገዘፈ

 ለሀገር ክብርና ብልፅግና ብለን ፤ ቆም ብለን በማሰብ ፤ ህሊናችንን ከጥላቻ እናፅዳ

Go toTop