ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ ሀገር የማፍረስ እንቅስቃሴውን በፕሮቴስታንት በኩል አውጇል፡፡ ኢትዮጵያዊያንን በሃይማኖት በኩል ለማጨፋጨፍ በሚሊነየም አዳራሽ በበጋሻው ደሳለኝ አማካኝነት የጥፋትን አዋጅ አሳውጇል፡፡ የዝግጅቱ አላማ ሙሉ በሙሉ ፖለቲካዊ ነው፡፡
በጋሻው ደሳለኝ የዝግጅቱን አላማ ሲገልጽ፡-
- ለብሔራዊ ንስሀ እና ለአማኞች አንድነት ጥርጊያውን ማዘጋጀት ነው (3x)፡፡
- ንጉሳችንን ክርስቶስን በአደባባይ ማክበር ነው (1x)፡፡
- ለሚመጣው ሀገራዊ ጉብኝት እና መነቃቃት ቤተ ክርስቲያንን መቀስቀስ እና ማንቃት ነው (3x)::
አብይ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤ/ክ እና ከፖለቲከኞች የሚደርስበትን ጫና ለመገታተር እና የፕሮቴስታንት ምዕመናንን ከጎኑ ለማሰለፍ አዋጅ አስነግሯል፡፡ የፕሮቴስታንት ሃይማኖት ተከታዮች ከጎኑ እንዲሰለፉ ግልጽ ጥሪ አቅርቧል ተግባራዊ እንቅስቃሴም ጀምሯል፡፡ እኔ በሃይማኖት ስም የኢትዮጵያዊያን ደም በከንቱ እንዳይፈስ ያሳስበኛል፡፡ ይህንን እንቅስቃሴ ልናጋልጠው እና ልናስቆመው ይገባል፡፡
ኃላፊነቱን መወጣት ሲያቅተው ሄዶ ከሃይማኖት ጋር መለጠፉን ማቆም ይኖርበታል፡፡ ይህ ሀገርን የሚያፈርስ እና በኢትዮጵያዊያን ላይ ጥፋት የሚያደርስ አደገኛ እንቅስቃሴ ነው፡፡ይበልጥ ኢትዮጵያን የሚያፈርስ እንቅስቃሴ ላይ እየተሳተፈ ነው፡፡ በቃህ ሊባል ይገባል፡፡ ቀድመን ልናስቆመው ይገባል፡፡
አብይ ዛሬውኑ ስልጣን ሊለቅ ይገባል!!!
ሙሉ በሙሉ ኃላፊነቱን የማይወጣ ሆኗል!! ይልቁንም ስልጣኑን አግባብ ባልሆነ መንገድ እየተጠቀመበት ነው!!