ከጠላት ዋሻ ውስጥ ላደገ ወሮበላ ውሻ ፍርፋሪህን ካሳደግኸውና አጥርህን ከሚጠብቀው ውሻህ ጋር እንዲጋራ አትፍቀድ

ከጠላት ዋሻ ውስጥ የያደገ ወሮበላ ውሻ

በመጀመሪያ እንኳን ለ127ኛው የአድዋ የድል በዓል አደረሰን አደረሳችሁ ። አድዋን ስናከብር ጀግኖች መሪዎች ከሌሉ ጀግና ህዝብ ጀግነቱን የሚያሳይ ሥራ መሥራት ብዙ መሰዋእትነት እና ዘመን እንደሚወሰድ እያሰብን መሆን አለበት። ለዚህም ነው የአድዋ ድል እንዲጨበጥ ያደረጉ ንጉስ ነገስት ዳግማዊ አጤ ምኒልክን እና ንግስተ ነገስቻት እቴጌ ጣይቱ ብጡልን በየአመቱ መዘንጋት የለባቸውም የምንለው ።

ወደ እርሱ ስመለስ ግን ዛሬ የባንዳ ልጆችና ማደጎዎች የአብይ አህመድ ኦሮሙማ እና ወያኔ የነ አጤ ምኒልክን ሀውልት ማየት የሚጠሉት እና የሚያስበረግግ መስቀል የሆነባቸው ከቀደመው የባንዳነት ውርሳቸውና አስተዳደጋቸው የመነጨ ነው።

ከጠላት ዋሻ ውስጥ ላደገ ውሻ የትግል መሪነት ወንበር ብቻ ሳይሆን ፍርፋሪ ህን እንጓ ካሳደጋቸውና አጥርህን ከሚጠብቀው ውሻህ ጋር እንዲጋራ አትፍቀድ።

ሹምባሽ በአርበኛ ጓዳ ውስጥ ምን ይሰራል ?

ደሳለኝ ጫኔን ጨምሮ አብዛኛው የዚህ የአብን አጭበርባሪ ቡድን ታሪክ ለማታውቁ ከ2010 በፊት ወያኔን የሚቃወሙ ሰዎችን ይሰልል የነበረ ነው። በዐማራ እና/ወይም ኦርቶዶክስ ላይ ግፍ ሲገዝፍ የት ነበሩ ብሎ የሚጠይቅ የለም ሾርት ሚሞሪ ናቸው ብለው ያስባሉ ልክ እንደ ሿሚዎቻቸው እና ጌቶቻቸው ። ያኔ የብአዴን-ወያኔ ቀኝ እጅ የነበሩ ህዝባችን ማሸነፉን ሲረዱ ተስፈንጥረው ከህዝብ ተቀላቅለው ዐማራውን ለጭፍጨፋው አዘጋጁ ት።

ተስፈንጥረው ዐማራው ሊያቋቁማቸው የጀመራቸውን እንደ አስራት የመሳሰሉ የሚዲያና መሰል ተቋማት አፈራርሰው ወጀ አሳደጋቸው ጓዳ ገቡ።

በነገራችን ላይ እኔም እራሴ አባል የነበርኩበት በአቶ ተክሌ የሻው የሚመራው የዐማራ ህልውና ለኢትዮጵያ አንድነት ፖርቲ አብሮ ለመስራት እና የመጣብንን አደጋ ህዝባችንን አሰባስበን እንታገል በማለት አነጋግሮ የፖለቲካ ሰነዶችን ተቀበለው ከተመለከቱ በኋላ ሀሳቦችን ከዘረፉ በኋላ ብአዴን በዐማራ ህዝብ ላይ ከሚያደርገው ማጣጣል በላይ አጣጥለው ነው የመለሷቸው።

ተጨማሪ ያንብቡ:  ወቅቱ ግድ የሚለው በአመጽ ነጻ መውጣት ወይንም በአመጽ መፈራረስ (እውነቱ ቢሆን)

ይህ አሳፋሪ ስብስብ የሠራውን የዐህኢአ ወገኖቼ ሊናገሩት ያልፈቀዱት ለዐማራው ትግል ሲሉ ይሆናል ። እኔም የእነሱን ለትግሉ መቆርቆር ተመልቼ ዝም ብየ ነበረ።

አሁን በቃኝ። የዐማራ ትግል ልክ የአድዋው አይነት የአንድ ጀምበር ፍልሚያ ብቻ የሚጠይቅ እንጅ ለአመታት ህዝብ እየታረደ አንድ እርምጃ ወደፊት ሁለት ወደኋላ የሚጓዘው በነዚህ አይነት ከተፈለፈሉበት ቅርፊት ጋር እንዲያታግሉንና እንዲታገሉልን በጊዜያችንን እና ገንዘባችንን ስለምናባክን ነው።

ተራው የአብን እና የብአዴን አባላት እነዚህ ሁለቱን ታጥበው የማይጠሩ ሽንፍላዎች አሽቀንጥሮ በመጣል ከመሪዬ እስክንድር ነጋና ጀግኖች የዐማራ ፋኖዎች ጋር አንድ የትግል ተቋምእንዲኖረን እንዲሰሩ እና ይህንን እንዲያደርጉ ጥሪየን አቀርባለሁ ።

ዛሬ ህዝብ ልክ በፋሸሸት እንደተወረርንበት ዘመን አምርሮ መነሳት ሲጀመር ለምን መጡ የሚለው ጥያቄ ላይ ሰመጣ፥

ዛሬ በመሪዬ በአርበኛው እስክንድር ነጋ እና በዐማራ ወጣቶች መናበብ በገሃድ እና በተግባር ሲመለከቱ ዘልለው ሊሰፍሩብንና ትግላችንን ሊያቀጭጬ ተከስተዋል ።

አሁንም ሊያታልሉህ ይችሉ ይሆን?

አይመስለኝም ።

ኑርልኝ- የካቲት 23 2015 ዓ.ም

 

https://zehabesha.com/open-letter-to-the-norwegian-nobel-committee-3/

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share