ይህ በአል ከዚህ ቀደም በአዲስ አበባ ከተማ ህዝብ ተሳትፎ በከፍተኛ ድምቀት በምኒሊክ አደባባይ ይከበር ነበር። እኔም አንዱ የህዝብ አካል ሆኜ ተሳትፌበት አውቃለሁ። በዛሬው እለት ግን በምኒሊክና በመስቀል አደባባይ የከተማው ህዝብ ድርሽ እንዳይል ከልክለው፣ በበአሉ የታደሙት የብልጽግና ከፍተኛ ባላስልጣናት፣ ካድሬዎችና ብልጽግና ድህነታቸው የታማኝነት ማሰሪያ ሰንሰለት አድርጎ በጥቃቅን እና አነስተኛ ድርጅቶች ያደራጃቸው ምስኪኖች ብቻ ናቸው። ሌላው ህዝብ ወደ አደባባዮቹ እንዳይደርስ በወታደር፣ በፌደራል ፖሊስና በከተማው ፖሊስ እንደ ከብት ከመንገድ እየተነዳ እንዲወጣ ተድርጓል።
በአንዳንድ ቦታዎች በድብደባ ጉዳት የደረሰባቸው እንዳሉ መረጃው ደርሶኛል። ሁኔታውን ለተመለክተ ቀኑ የበአልና የደስታ ሳይሆን ከተማው በጠላት ተወሮ የሃዘን ጥላ ያጠላበት ቀን ይምስል ነበር። ይህ በወሬ ሳይሆን በአካል ወደ መስቀል አደባባይ ከጓደኞቼ ጋር ለመሄድ ሞክሬ ከደረሰብኝ ተነስቼ ነው የምጽፈው። እንኳን ለዚህ ቀን አበቃህ የምትሉ ምጸተኞች እንዳላችሁ አውቃለሁ። በምጸታችሁ አላዝንም። የማዝነው ከታሪክ መማር ለተሳናቸው እብሪተኛ የሃገሪቱኛ ገዥዎች ነው።
V Day turned into a day of ignominy. Residents of Addis were denied the right to celebrate the V of Adwa at any of the city’s public Squares.Only PP affiliates, officials and cadres were allowed to get into Meskel Square.Menelik Sq was also off the limit to revellers.I was there
Andargachew Tsige