የግብጹ ባንዲራና የጥላቻው መዝሙር (ከአሁንገና ዓለማየሁ)

የኦሮሞ ፖለቲከኞች የኦሮሞ ሕዝብ ዲሞክራሲ አላገኘም በሚለው ይስማማሉ። በዲሞክራሲያዊ መብት የመጠቀም እድል ካላገኘ ዛሬ የተጫነበትን የግብጽ ባንዲራም አልመረጠም ማለት ነው። የጥላቻውንም መዝሙር አልጻፈም፣ አላጻፈም፣ በዲሞክራሲያዊ አግባብ ተስማምቶ አላጸደቀውም ማለት ነው።

ራሱ የኦሮሞ ሕዝብ የኔ ነው ያላለውን ሰንደቅ ዓላማ እና የጥላቻ ድርሰት ሌሎች እንዲያውለበልቡ ማስገደድ ከኦሮሞም ከሌላውም ሕዝብ ፈቃድ ውጭ የሆነ የፋሺስቶች፣ የመልካም ራዕይ አልባዎች፣ የግጭት ነጋዴዎች ተግባር ነው። ይህንን መቃወም ደግሞ በተቃራኒው ለዲሞክራሲ መታገልና እጅግ ፍትሐዊ ተግባር ነው። ባንዲራው የግብጽ ነው። መዝሙሩም የጥላቻ ድርሰት ነው። ይህንን ባእድና አዋራጅ ጭነት መቃወም የአርበኝነት ሥራ ነው።  አጀንዳው ግን በዚህ ወቅት የተመዘዘው በግርግርና በሽፋኑ የክህደቱን ድርድር ለማስረሳት ይበልጥ ደግሞ የወለጋውን የንጹሐን ጭፍጨፋ ለማሳለጥ፣ የአማራን ጄኖሳይድ በክፍተኛ ደረጃ ከሕዝብ ትኩረት ውጭ ለማድረግ በመሆኑ የወንጀል ወንጀልና፣ ከከረፋ ቆማሪ ኅሊና የመነጨ አዳፋ ተግባር ነው።

እኔ በግሌ የኦሮሞ ሕዝብ ሰንደቅ ዓላማዬ ነው ያለውን በፈቃደኝነት ባውለበልብ ግድ የለኝም፣ መዝሙሬ ነው ያለውን ብዘምርም ደስ ይለኛል። ሀገር አፍራሽ፣ የአክራሪ እስልምና አጀንዳ አራማጆች በስውርና ዘመናትን በዘለቀ ማጭበርበርና ደባ የአክራሪ እስልምና አላባ፣ የግብጽ ባንዲራ የሆነውን ሰንደቅ ዓላማ በኦሮሞ ላይ እንደጫኑበት በእጅ አዙር እኔም ላይ ሊጭኑብኝ ቢሞክሩ ግን አልቀበለውም። መዝሙሩንም እህትና ወንድሜ አጥንትና ደሜ የሆኑ የኦሮሞ ልጆች በኢትዮጵያዊና አፍሪካዊ መንፈስ ተቃኝተው ለሕዝባቸው መልካም ራእይ ሰንቀው የደረሱትና ሕዝቡ የተቀበለው ከሆነ በደስታ አሁንም በፈቃደኝነት ብዘምረው ደስታዬ ነው። የአረብና የፈረንጅ ተላላኪዎች ሀገር ለማፍረስ፣ አፍሪካን ለሌላ ዙር ቀኝ ግዛት ለማመቻቸት የወጠኑትን የጥላቻና የበቀል ጥንስስ ድርሰት ልጆቼ እያጠኑ እንዲያድጉ ልፈልግ ቀርቶ ልሰማውም አልፈቅድም።

ተጨማሪ ያንብቡ:  ዳግማዊ ጫኔ { ሰይጣን ልማዱ ነው) dagemawi chanie seitan lemadu newu New Ethiopian Music 2023

የኦሮሞ ልጆች ከአብዲሳ እስከ ቀነኒሳ የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ ከፍ አድርገው ያውለበለቡ እንዲሁም የኢትዮጵያ ሕዝብ መዝሙር የሚዘምርለትን ነጻነት እውን ያደረጉ ናቸው፤ ዘላለማዊ ክብር ይገባቸዋል። ከዙፋን እስከ ጫካ ያሉት ባንዶች ደግሞ ኢትዮጵያን የሚያዋርዱ፣ መሠረቶቿን የሚንዱ፣ ከባእዳን ጋር የሚሞዳሞዱ ናቸውና እንደሌላው ብሔር ባንዳ ሁሉ ዘላለማዊ ተቃውሞ ይገባቸውል።

ይሁንና ተቃውሞው መጀመሪያ ባንዲራውና መዝሙሩ የኦሮሞ ሕዝብ ባንዲራ እና መዝሙር አለመሆኑን በማጋለጥ ቢጀምር። ሲቀጥል በስናይፐርና በገጀራ ለመፍጀት ዝግጅት ጨርሶ ለተቀመጠው የአቢይ አህመድ ጦር ሕፃናትና ወላጆችን ሲሳይ በማያደርግ መልኩ ቢካሄድ። ሦስተኛም ፍጅትና ግጭት፣ ግድያን ጠንስሶና ጠምቆ የሞቱን ድግስ ከርቀት ለመታዘብ ከሀገር ውጭ የሚጓዘው አቢይ አህመድ እሳትም ከተነሳ አብሮ እንዲበላው ጌቶቹ ጠርተውት ከሄደበት እስኪመለስ ቢጠበቅ።

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share