የዲሲው ተቃውሞ በቀጥታ ለታፈነ ሕዝብ ድምጽ ሆኑ አስተባባሪዎቹ ይናገራሉ | Hiber Radio With Wondessen Dec 13, 2022 | Ethiopia

 

^ አንቺን ተመርኩዘው ፤ ጊዜን ቢታደሉ
^ አለቃ ሆኑብኝ ፤ ዘመዶችሽ ሁሉ
^ አንቺ ግፍ አትፈሪም ፤ በኔ ቤት ሆነሽ
^ ዳንቴል ትሰፊያለሽ ፤ ለዛኛው ቤትሽ
^ እቴ ያንቺ ነገር ፤ ሳሥበው ይገርመኛል
^ የሰው ሚስት አግብቼ ፤ ምኖር የመስለኛል
..@….ጌቲሽ ማሞ ….#

 

 

ተጨማሪ ያንብቡ:  ጀግናው የአባገዳ ልጅ ታዬ ቦጋለ ስለ ጃዋር ያልተጠበቀ ጉድ አወጣ ጃዋር በአባቱ የመኒ በእናቱ አማራ ቢሆንም በአርሲ ኦሮሞ በጉዲፈቻ ያደገ ነው

1 Comment

 1. ሁለት ልጅ ያረደች
  ዳኛው ሞት ፈርዶባት በእስር እያበደች
  እያንጠባጠበ የንጹሐኑን ደም
  በኃያላን ማእድ ተጠርቶ ሊታደም
  አእላፍ ያረደ
  ዋሺንግተን ዲሲ ላይ ካውሮፕላን ወረደ

  ገሌ እየላከ
  “ኖ ሞር!” እያስባለ ሲያጃጅልህ ከርሞ
  ዲሲ መጣ ጌታህ
  ለእልቂት ተግባሩ ምንዳ ተሸልሞ
  ጌታውን እጅ ነስቶ ሊመለስ እግር ስሞ

  ለጌታህም ደግሞ አለውና ጌታ ጠቅሶ የሚጠራው አለንጋ ወንጭፎ
  አበሻ ተመልከት ሮጥ ብሎ ሲመጣ ጅራቱን ቆልፎ

  እሱ እያሻወከ
  ሽቦ በሌላት ስልክ እያንሾካሾከ
  አንተን አጃጅሎ
  ሲያስፎክርህ ነበር ሲልክህ ጃስ ብሎ
  በነጭናጫነትህ አንተ ስትጠላ
  እሱን ተመልከተው ከጌቶቹ ማእድ ቡሌውን ሲበላ።

  በሰላም እንዳትኖር ባስጠጋችህ አገር
  ኖ ሞር! ኖ ሞር! እያልክ እፉ ስትናገር
  የበሻሻው ጮሌ ከጀርባህ አላግጦ
  ገፍቶ ይጥልሃል ጭቃውን አዳልጦ

  ውስብስቡ ባንዳ
  መሬት ለኢንቨስተር ለሃብታም ሊያጸዳ
  ምስኪኑን ገበሬ ሲፈጅ በመደዳ
  የሕፃን አዛውንቱ
  ጎልማሳ ወጣቱ
  አካል ተከታትፎ
  ደማቸውም ጎርፎ
  ቤታቸው ተቃጥሎ
  አዝመራቸው ከስሎ
  የእልቂታቸው ዜና ጎልቶ እንዳይሰማ
  እንዳይከፍል ጉማ
  ገዳይ የሟቾችን ጩኸት እየቀማ
  እስከዛሬ ድረስ አጀንዳውን ማርኮ
  አዝለኸው እሽኮኮ
  ማስቀየሻ ሆነህ ስትጮህ በተልእኮ
  ላደረሰከው በደል ካይኖችህ አለቶች እስኪ ቅዳ ውሃ
  ካሳ ባይሆን እንኳን እንዲሆን ንሥሐ
  የጌታህን ክዳት ባይንህ ካየህ አሁን
  ይልቅ ለሚያርዳችው ንጹሐን ድምጽ ሁን

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share