መነሻውን ፈለገ ገነት ቅዱስ ጊዮርጊስ ካቴድራል ቤተ ክርስቲያን በማድረግ መድረሻውን ጽርሐ ጽዮን ቅድስት ማሪያም አንድነት ገዳም ያደረገው ሩጫ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ የባሕር ዳር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል ብፁዕ አቡነ አብርሃምን ጨምሮ ታላላቅ የአብያተ ክርስቲያኗ አባቶች፣ የመንግሥት የሥራ ኅላፊዎች እና ሕዝበ ክርስቲያኑ ተሳትፈውበታል።
በመርሐ ግብሩ ላይ አትሌት ሻለቃ ኀይሌ ገብረ ሥላሴ በክብር እንግድነት ተገኝቷል።
በሩጫው ከሴቶች ገንዘቤ ጋረድ ፤ ከወንዶች ያረጋል ቀሬ ፤
ከአካል ጉዳተኞች በወንዶች ሞገስ እስከዚያው እንዲሁም
በሴቶች እናትሁን ዓለም አሸናፊ መሆናቸውን አሚኮ የዘገበ ሲሆን ከአረጋውያን ደግሞ በወንዶች አደመ መንግሥቱ
በሴቶች ደግሞ ትነበብ ታደለ መንፈሳዊ ሩጫውን በአሸናፊነት አጠናቅቀዋል።
መንፈሳዊ ሩጫው ለጽርሐ ጽዮን ቅድስት ማርያም አንድነት ገዳም እና በውስጡ ለተካተቱ ዘርፈ ብዙ መንፈሳዊ ፕሮጀክቶች ገቢ የማሰባሰብ ዓላማ ያለው መሆኑም ታውቋል።
አዲስ አድማስ