November 9, 2022
1 min read

ጋዜጠኛ ዳዊት ከበደ ወየሳ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ

314414476 8179249182149630 7536147184994988946 n
አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ
ጥቅምት 30 ቀን 2015 ዓ.ም
314414476 8179249182149630 7536147184994988946 n
“ጋዜጠኛ ዳዊት ከአሜሪካ ወደ አዲስ አበባ የገባው ከአምስት ቀናት በፊት ባሳለፍነው አርብ ሲሆን፤ ከ3 ቀናት በፊት በማኅበራዊ ሚዲያው አዲስ አበባን እንዴት እንዳገኛት እያጋራን ነበር። ከሦስት ቀናት በኋላ ወደ ማተሚያ ቤት የሚገባውን አዲሱ መጽሐፉን አርትዖት ለማጠናቀቅ ደፋ ቀና በሚልበት ወቅት ነው ድንገተኛ እረፍቱ የተሰማው” ሲል ጋዜጠኛ ይድነቃቸው ከበደ አጋርቷል።
ጋዜጠኛ ዳዊት ከበደ ከሩህ መጽሄት እስከ ሞገድ ጋዜጣ፤ ከለገዳዲ እስከ ትንሳ’ኤና አድማስ ሬድዮ ያገለገለ ፤ በሙያው አንቱታን ያተረፈ፣ ላለፉት 30 አመታት ያለማቋረጥ በፕሬስ ህትመት እና በሬዲዮ ዝግጅት ክፍል ውስጥ ዋና አዘጋጅ ሆኖ አገልግሏል ።
እግዚአብሔር ነፍሱን በአብርሀም በይስሀቅ በያዕቆብ አጠገብ ያኑርልን።
ለጋዜጠኛ ዳዊት ከበደ ቤተሰቦች፣ወዳጅ እና አድናቂዎች ልባዊ መፅናናትን ፈጣሪ ይስጥልን !!
ምንጭ_ጋዜጠኛ ይድነቃቸው ከበደ

2 Comments

  1. ለምን ትሞታለህ እኔ ተቀምጨ ምንም የማልሰራ እጅ እና እግር ይዤ
    ማሰቡስ ይቅርብኝ ጭንቅላት የለኝም ሰው በድሎት ሂዶ ቀናን አያስብም
    አጥርቶ ለማየት አይኖቼም ከብደዋል ሰርክ ዓለም ሳለቅስ በግፍ ለተሸኙ
    ሟሙተው ጉድጉደው ጭቃ ብይ መስለዋል
    ኸረ ተይ ሃገሬ ይብቃሽ መርጦ መግደል ጀላፎው ተቀምጦ ምርጦችን ማስወገድ (ህዳር 1, 2015)

    የዳዊት መሞት እጅግ ልብ ይበላል። እኔ ዳዊትን በግሌ አላውቀውም። በሥራው ግን አውቀዋለሁ። እኔን የማይገባኝ በኢትዮጵያ ውስጥ በድንገት ሞተ የሚባለው ሰው መብዛቱ ነው። ከዚህም በላይ በጣም የሚያሳዝነኝ በሰላም ከተቀመጡበት ሃገር ወደ ምድራቸው ተመልሰው ለሃገሬ ለወገኔ በማለት ቀና ደፋ ሲሉ በዚያው የሚቀሩት ሰዎች ቁጥር የዕለት ዜና መሆኑ ነው። ማን ነው የሚገድላቸው? ወይም የሚያስገድላቸው? ምን አይነት የመከራ ዝናብ ነው በዚያች ምድር ላይ የሚፈሰው። እንደ ዳዊት ያሉት ሞታቸው በዜና የወጣላቸው ብቻ ሳይሆን እንዲሁ ስማቸው ሳይጠቀስ አፈር የለበሱም ብዙዎች ናቸው። ከከያኔዎች ዳዊት ነጋ፤ ማድንጎ አፈወርቅ ወዘተ ድንገት ሞቱ ተብለን ቀብረናል። የሞታቸው ሚስጢር የገባው ይኖር? መረጃ አለ? ወይስ ዝም ብሎ አልቃሽና አስለቃሽ ተሰባስቦ በመቅበር ጉዳያቸው ይረሳል።
    ሞት ለሁሉም የማይቀር ነው። ዛሬ ቆሞ አፈር በሟች ላይ የመለሰው እቤቱ ሳይገባ ሟች ሊሆን ይችላል። ለዚም ይመስለኛል ሽክስፔር ስለ ኪሊዪፓትራ በጻፈው ሥራ ላይ እንዲህ የሚለው “The stroke of death is as a lover’s pinch, which hurts, and is desired”. እኔ በፍቅረኛዬ ተቆንጥጨ አላውቅም። ግን ሊያስተላልፍ የፈለገው ጉዳይ ይገባኛል። ኸረ ተው ምቀኝነት፤ መገዳደል፤ መሸዋወድ ይብቃን።

  2. ነብሱ ይማረው ዳዊት ከበደ ወይሳ፣ እዚህ ኣትላንታ ነው የማውቀው በተለይ ከኣድማስ ሬድዮ እና በህዝባዊ ስብሰባዎች። የዓድዋ ድል ለመጀመርያ ሲከበር ሰምትሓል ወይ ብሎ ደወለልኝ፣ ተሳተፍኩኝ፣ ቆይተውም “ዓድዋ ጉዞ በኣትላንታ” መስርተው ቅዳሜ ቅዳሜ ስቶን ማውንቴን (Stone Mountain Park) በሚባለው ትልቅና የታወቀው ፓርክና ተራራ ወደ ከፍታው እየወጣን የዓድዋ ድልን እናከብራለን። በተጨማሪ ዳዊት ታሪካው ትንተና ስንነሳ፣ መሓል በእረፍት የመቀለ ድል፣ እላይ ጫፍም እንደዛው፣ ከዛም የኢትዮጵያ ባንዴራ ተውለብልቦ ይከበራል። ጣና ሱቅ በተለይ ባለቤቴ ስትገልጸው በጣም ትሁት፣ ኣድማጭ፣ ተጫዋች፣ እስከ መኪና እቃዎች የሚያደረስ፣ የሚወደድ ወንድም ብላ ታከብረዋለች። አትላንታ ትልቅ ሰው ዳዊት ከበደ ወይሳ ኣጣች። ደግነትህ አይረሳም። እግዚአብሔር በቀኝ እጁ ያኑርህ።

Leave a Reply

Your email address will not be published.

smyelesh
Previous Story

የሥም የለሽ ነፍስ ማን ያንሳሽ? (በላይነህ አባተ)

177706
Next Story

አንጋፋው ጋዜጠኛ ዳዊት ከበደ ወየሳ ድንገተኛ ሞት ትውስታ

Latest from Blog

አስቸኳይ ህዝባዊ ጥሪ

July 24, 2024 ዓለማቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያዊያን መብት Global alliance for the Rights of Ethiopians (GARE) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሳቻ ጎዝዲ ቀበሌ በደረሰው የመሬት መንሸራተት የብዙ ወገኖቻችንን ህይዎት ማለፉን
Go toTop