August 15, 2022
4 mins read

ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ ባለፈው ሣምንት ከፕሬዝደንትነታቸው የለቀቁት አቶ እስክንድር ነጋ የት እንዳሉ እንደማያውቅ ገለጸ

299010213 5852190198147361 3434263022859082194 n
299010213 5852190198147361 3434263022859082194 nባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ ባለፈው ሣምንት ከፕሬዝደንትነታቸው የለቀቁት አቶ እስክንድር ነጋ አሁንም የት እንዳሉ እንደማያውቅ ገለጸ። የፓርቲው ኃላፊዎች ዛሬ ሰኞ በአዲስ አበባ በሰጡት መግለጫ ከሐምሌ 16 ቀን 2014 ጀምሮ አቶ እስክንድር ከባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ ጽህፈት ቤት እና ከሥራ አስፈጻሚው ጋር ያላቸው ግንኙነት ሙሉ በሙሉ መቋረጡን ገልጸዋል።
የፓርቲው ምክትል ፕሬዝደንት አቶ አምኃ ዳኘው በንባብ ባሰሙት መግለጫ አቶ እስክንድር “ምንም የነገረን ነገር ባለመኖሩ፤ የት እንደሔደ እና በምን ሁኔታ ላይ እንዳለ ባልታወቀበት ሁኔታ አድማጭን የሚያረካ መልስ መስጠት የሚቻልበት ሁኔታ አልነበረም” ብለዋል።
በአሜሪካ ሀገር የሚገኙት የአቶ እስክንድር ባለቤት እንዳልደነገጡ እና ከፓርቲውም ሆነ በውጭ አገር ከሚገኘው የድጋፍ ኮሚቴ ማብራሪያ እንዳልጠየቁ የጠቀሱት ምክትል ፕሬዝደንቱ በዚህ ምክንያት “የመታፈን አደጋ እንዳልደረሰበት ገመትን” ሲሉ ተናግረዋል። ፓርቲው አቶ እስክንድር ያሉበትን ሁኔታ ያሳውቁናል ብሎ በመጠባበቅ ላይ ሳለ በአሜሪካ ከሚገኘው የድጋፍ ኮሚቴ በኩል የመልቀቂያ ደብዳቤው ይፋ እንደሆነ አስረድተዋል።
አቶ እስክንድር የኢትዮጵያ መንግሥት “በባልደራስም ሆነ በሀገር አቀፍ ደረጃ በፈጠረው የለየለት አምባገነናዊ ጫና ሳቢያ በአባልነትም ሆነ በአመራርነት መሥራት የማልችልበት ደረጃ ላይ ደርሻለሁ” ሲሉ ሐምሌ 16 ቀን ተጽፎ ነሐሴ 5 ቀን 2014 በፓርቲው የተረጋገጠ የፌስቡክ ገጽ ላይ በተለጠፈ ደብዳቤ ገልጸው ነበር።
የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ አባል እና የጽህፈት ቤቱ ኃላፊ የሆኑት ወይዘሮ ቀለብ ሥዩም ከሐምሌ 16 ቀን 2014 ወዲህ አቶ እስክንድርን “በስልክም ይሁን በአካል አግኝተናቸው አናውቅም” ሲሉ ተደምጠዋል። መንግሥት አቶ እስክንድርን “እንዳላፈናቸው እና እንዳላሰራቸው” ፓርቲው እንደሚያምን የገለጹት ወይዘሮ ቀለብ ከቤተሰቦቻቸው “ደህና” መሆናቸው እንደተገለጸላቸው በዛሬው ዕለት በተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ አስረድተዋል። ይሁንና አቶ እስክንድር ከአሜሪካ ከተመለሱ በኋላ “የተለያዩ የደህንነት መኪናዎች እና የተለያዩ ሰዎች” ይከታተሏቸው እንደነበር የገለጹት ወይዘሮ ቀለብ “ውጥረት እና ከፍተኛ ጭንቀት” ውስጥ ለመሆናቸው “ምልክቶች እንደነበሩ እናውቃለን” ብለዋል።
DW

Leave a Reply

Your email address will not be published.

minster
Previous Story

አማራ፦ ህልውናህ ያለው በአንተው መዳፍ ውስጥ ነው (እውነቱ ቢሆን)

geletaw
Next Story

አቶ ገለታው ዘለቀ በኢትዮ 360 ላይ ተጋብዞ ስርዓታዊ ሽብር በሚለው አርዕስት ላይ በኤርምያስ ለገሰ ለቀረቡለት ጥያቄዎች ለሰጣቸው መልሶች ትችታዊ አስተያየት!

Latest from Blog

አስቸኳይ ህዝባዊ ጥሪ

July 24, 2024 ዓለማቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያዊያን መብት Global alliance for the Rights of Ethiopians (GARE) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሳቻ ጎዝዲ ቀበሌ በደረሰው የመሬት መንሸራተት የብዙ ወገኖቻችንን ህይዎት ማለፉን
Go toTop