የጠፋችን ‘ፅ’ናት

በኢትዮጵያ የሚደጋገሙ የዘመናት ጭቆና እና በደል እንደ አዙሪት ከቦ አንደ ዕንዝርት እየተሸከረከረ የሚፈራረቅባት  የመከራ ምድር ሆና ለዓመታት ዘልቃለች ፡፡

በየትኛዉም የአንድ አገር እና ህዝብ መገለጫዎች የሆኑት የባህል፣ ቆንቋ፣ ዕምነት ፣ ፖለቲካ ፣ ርዕዮተ ዓለም ፣ ኢኮኖሚ የመሳሰሉት በተለያየ መንገድ እንዲበረዝ እና እንዲከለስ ተደርጓል፡፡

እንዲያዉም ማንት ማሳያ የሆኑት የአንድ ህዝብ እና ማህበረሰብ ነፀብራቅ የሆኑት  የጥላቻ እና የበቀል ማራገቢያ ሆነዉ ቆይተዋል ፡፡

ለዓመታት አስቀድሞ ኢትዮጵያን የቆየ የአንድነት እና ታላቅነት ምሰሶ ለማናጋት በተለይም ኢትዮጵያዊነት እና ዓማራነት ጠላትነት ሆኖ በማንነት ላይ የተደረገ ብሄራዊ የማሳደድ ዘመቻ የተካሄደበት እንደነበር እና ይህም ቅርፅ እና መልክ ቀይሮ ካለበት ደርሷል፡፡

 

ለዚህ ሁሉ መጠነ ብዙ ማንት ተኮር የባህል ፣ የቋንቋ፣ የዕምነት እና የኢትዮጵያዊነት  የማጥላላት ፣ መግፋት ምክነያት የኢትዮጵያዉያን አንድነት እና ህብረት በቅርብ እና ሩቅ ዓላማ በፅናት አለመቆም እና አለመቀጠል ነዉ ፡፡

በነፃነት እና በህልዉና ጉዳይ በግል እና በተናጠል በችርቻሮ ማስተጋባት ለሆኑት እና ለሚሆኑት አገራዊ እና ህዝባዊ መከራዎች ዘመን መራዘም ምክነያት ሆኗል፡፡

አገር እና ህዝብ ሲሞት በዝምታ እና በምን ቸገረኝነት የሚያልፍ ነገር ግን የግል እና የቡድን ጥቅም ሲነካ ለምን እያሉ ብሄራዊ ችግርን እና መከራን መርሳት እና ማዘናጋት ከዓላማ አንድነት እና “ፅ”ናት አለመኖር ነዉ ፡፡

ለማናኛዉም አገራዊ እና ብሄራዊ ችግር  ምንጭ  ፅናት ብለን በጋራ መገንዘብ እና መናበብ ሲገባን እና ፅናት (Endurance and persistent  )እና ቁርጠኝነት ( courageous) ጠፍቶ የሰሞነኛ የግል ጫጫት ማስተጋባት ሰሚ ያጣ የቁራ ጩኸት  ከመሆን ሊያልፍ የሚችል ካለመሆኑ በላይ ጠብታ ዉጤት አያስገኘም ፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  አማራው በዘሩና በማንነቱ እየተገደለ ያለው በአብይ አህመድ እና በሽመለስ አብዲሳ ቀትተኛ ትዛዝ ነው

የዘመናችን ችግር ሁላችንም ኢትዮጵያ እንደ አገር እንትቀጥል ለምንፈልግ  የጠፋችዉን ፅ ማግኘት እና  ‘ፅ’ ናት እንዲኖረን አሁንም አሁንም   “ፅ” ን እናፈላልግ ፡፡ ፅ በፊደል ገበታ ላይ እንጂ በቃላት እና በስነ ቃላት የሚነበብ እንጂ በዕዉን የሌለ በመሆኑ በተግባር እንዲተረጎም  መተውጋት ያስፈልጋል ፡፡  ዕድገት (ብልፅግና) ዕዉንነት  መሠረቱ እና ምክነያቱ ‘ፅ’ ናት  እና በፅናት  በሠለጠነ አስተሳሰብ( ብል’ፅ’ግና) እና ፅናት (አይበገሬነት) ላይ “ፅ”ን ደጋግሞ ማሰብ እና ማንበር ያስፈልጋል ተሰዉራለች እና ነዉ ፡፡

ያለ ዓላማ አንድነት እና ፅናት  ነፃነት እና ህልዉና ህልም ነዉ ፡፡

“ኢትዮጵያን  ሲተባበር  ራሱን እና አገሩን ያስከብር  ፤ ኃይልም ከመተባበር  ነዉ ፡፡”

NEILLOSS –Amber

1 Comment

  1. ጎበዝ እረ አንድ እንበል ስብሃት ነጋን የመሰለ አገርና ዜጋ ገዳይን በእድሜ ምክያት ፈትቶ ለሃገር ተቆርቋሪን አቶ ታድዮስ ታንቱን በ80 አመታቸው ማሰቃየት ምን የሚሉት ነው? ይህ ህዝብ አቶ ታዲዮስ ታንቱን አሳስሮ ማን ሊታገልለት ይፈልጋል?

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share