July 23, 2022
2 mins read

4ኛ ቀኑን የያዘው የለንደኑ የርሃብ አድማ ቀጥሎ መዋሉን ለመመልከት ተችሏል

294451499 417464833731979 2580410661870413925 n
ይህ የርሃብ አድማ በውስን አማራዎች እና ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያን የተደረገ ሲሆን አላማውም በኢትዮጵያ በአማራ ህዝብ ላይ እየተፈጸመ ያለውን የዘር ፍጅት ማውገዝ፣ እንዲቆም መጠየቅ ነው።
ከዚህም በተጨማሪ መንግስታዊ መዋቅር ጭምር ተሳትፎ እያደረገበት ያለው የዘር ፍጅት መሆኑን የዩኬ መንግስት ተገንዝቦ ከንጹሃን ጎን እንዲሰለፍ ለማሳሰብም ነው።
294451499 417464833731979 2580410661870413925 n
በተለያዩ ጊዜያቶች ለኢትዮጵያ መንግስት የሚደረጉ ድጋፎች በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ በአማራ ላይ ለሚፈጸሙ የጅምላ ፍጅት እንደሚውሉ ግንዛቤ ተወስዶ ጫና ማድረግ እንዲችሉም ተጠይቋል።
4ተኛ ቀኑን በያዘው የርሃብ አድማ ከሚሳተፉት መካከል በተለይም ሮማን ተስፋዬ ተዳክማ ድንገተኛ የህክምና አገልግሎት በሚሰጡ የጤና ባለሙያዎች ስትደገፍ ታይታለች።
፤ የድንገተኛ ህክምና አገልግሎት የሚሰጡ የጤና ባለሙያዎችም ድጋፍ ሲሰጡ ተስተውሏል።
ከሲዊትዘርላንድ የርሃብ አድማ ለማድረግ ወደ እንግሊዝ ለንደን ያቀናችው የስቶፕ አምሃራ ጄኖሳይድ ዳይሬክተር ዮዲት ጌዲዮን በማህበራዊ ትስስር ገጿ እንዳጋራችው የአማራን የዘር ፍጅት በመቃዎም በሎንዶን፤ እንግሊዝ እየተደረገ ያለው የርሀብ አድማ ለአራተኛ ቀን ቀጥሎ ውሏል።
“አለን ሰላም ነን።እኔ ውሀ ዛሬ ትንሽ ጠጥቻለሁ። ያየሽይራድ ግን እምቢ አለች። ትንሽ እየደከመች ነው። ግን እየተከታተልናት ነው።” የሚል መልዕክቷን አጋርታለች።
መንግስታዊ የአማራው የዘር ፍጅት ይቁም!፣
በአማራው ላይ እየተፈጸመ ያለው የዘር ፍጅት በገለልተኛ ወገን ይጣራ!፣
ፍትህ ለዘር ፍጅት ሰለባ ለሆኑ አማራዎች የሚሉና የመሳሰሉ መልዕክቶችም እየተላለፉ ነው።
አዲስ ሚዲያ

1 Comment

  1. Igziabher Yibarkachihu. Ye nitsuhan Amlak yiTebiqachihu. History will remember you with Gandi and Dr. King (when history puts Abiy and collaborators in their rightful place with Mussolini, Hitler, Gobbles etc).

Leave a Reply

Your email address will not be published.

8757638140156407629
Previous Story

የአገርና የመንግሥት ሦስቱ ሥላሴዎች (National trinity) – አገሬ አዲስ   

294687064 10229016690345401 4248275892395723478 n
Next Story

የመወደድ ርሃብ የመወደድ ጥማት

Latest from Blog

አስቸኳይ ህዝባዊ ጥሪ

July 24, 2024 ዓለማቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያዊያን መብት Global alliance for the Rights of Ethiopians (GARE) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሳቻ ጎዝዲ ቀበሌ በደረሰው የመሬት መንሸራተት የብዙ ወገኖቻችንን ህይዎት ማለፉን
Go toTop