በግብፅ፣ በሱዳን እና በኢትዮጵያ መካከል ያለውን ትብብር ማስፋት የታላቁ ህዳሴ ጉዳይን ለመፍታት ያስችላል ሲሉ የግብፁ ፕሬዚዳንት አብዱል ፈታህ አልሲሲ ተናገሩ

አልሲሲ ይህንን የተናገሩት ትናንት በሰርቢያ የቤልግሬድ ዩኒቨርሲቲ የክብር ዶክትሬት ከተሰጣቸው በኋላ ባደረጉት ንግግር ነው።
በየሄዱበት ሀገር የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን ጉዳይ በማንሳት የሚታወቁት አልሲሲ በሳምንትቱ መጀመሪያ ጀምሮ ለሶስት ተከታታይ ቀናት በምስራቅ አውሮፓዊቷ ሀገር ሰርቢያ ባደረጉት ጉብኝትም ጉዳዩን አንስተዋል።
ኤል ሲሲ በትናንቱ ንግግራቸው በግብፅ፣ በሱዳን እና በኢትዮጵያ መካከል ያለውን ትብብር ማስፋት የታላቁ ህዳሴ ጉዳይን ለመፍታት ያስችላል ብለዋል።
ፕሬዝዳንቱ አክለውም በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ዙሪያ በሶስቱ ሀገራት መካከል ሚዛናዊ እና ፍትሃዊ የህግ ስምምነት መኖሩ የኢትዮጵያን የልማት እና የኤሌክትሪክ ኃይል የማመንጨት አቅም ከማሳደግ ጎን ለጎን የግብፅን እና የሱዳንን የውሃ መብት ለማስጠበቅ ያስችላል ብለዋል።
ግብፅ በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ጉዳይ ላይ የግብፅና የኢትዮጵያን ግንኙነት ለማሳደግ ያላትን እምነት መሰረት በማድረግ ለዓመታት የድርድር መንገድን ስትከተል መቆየቷን ገልፀው፤የውሃ አካላትን የጋራ አጠቃቀም የሚቆጣጠሩ ሁለንተናዊ መርሆች መከበር እንዳለባቸው ተናግረዋል።ይህም እንደ ፕሬዚዳንቱ የሀገሮችን ፍላጎት በሚዛናዊ በሆነ መንገድ ያሳካል።
ህጋዊ ስምምነት በሌለበት ሁኔታ ኢትዮጵያ የግድቡን የመጀመሪያ እና ሁለተኛ ሙሌት በማጠናቀቅ በያዝነው አመት መጀመሪያ በግድቡ ተርባይን ኤሌክትሪክ ማምንጨት መጀመሯ እና ሦስተኛውን ሙሌትም በመጭው ነሀሴ እና መስከረም ወር ለመጀመር ዕቅድ መያዟ እንዳሳሰባቸው መግለፃቸውን አልሃራም የተባለው የግብፅ ጋዜጣ ዘግቧል።
DW
ተጨማሪ ያንብቡ:  ኢትዮጵያ ውስጥ መንግስት የመቶ ብር ኖቶችን እንደጉድ እያተማቸው ነው * መቶ ብር በዛ ኢኮኖሚ ጠነዛ

2 Comments

  1. ግብጾችና ትግሬዎች መሰረታቸው አንድ ነው ማለት ነው? ነገራቸው ሁሉ የልጅ ነገር ይመስላል ልጅ የሰው ነገር የኔ ነው ብሎ እንደሚያለቅሰው ማለት ነው ትግሬዎችም አሁን ትላንትና ቀምተው አጽድቁልን ይላሉ፡፡ አሁንማ የግብጾች ነገር ውሃው ከግብጽ ወደ ኢትዮጵያ የሚፈስ አስመሰለባቸው፡፡ የምን የውሃ ድርሻ ነው የሚያወሩት? ዉሃ ወርቅ ሁኗል የምን አሳሪ ስምምነት ነው? ትንሺ ማፈርም ቀረ? ወደፊት ጠንካራ ፈስፋሻ ያልሆነ ትውልድ ሲመጣ እነሱ ለነዳጅ እንደሚያስከፍሉት ቢቻል እስከዛሬ ለተጠቀሙበት ባይቻል የወደፊቱን እኛ ባስቀመጥነው ዋጋ ይከፍላሉ፡፡ ታዲያ ከዛ በፊት ኢትዮጵያውያን ግብጾች ላይ ትኩረት ያስፈልጋል እነ አቡ ምናምን አህመዲን ጀበል ጁዋር መሃመድ . የመሳሰሉት ጥሎባቸው ከተከበረው ኢትዮጵያዊነት ይልቅ አረብ መሆን ህልማቸው ነው፡፡ ትንሽ የሚወረውሩላቸውን ሽርፍራፊ ወደ ፊት ኢትዮጵያም ልትሰጣቸው ትችል ነበር ቸኮሉ እንጅ ብርሃኑ ነጋም ጉዳይ አስፈጽማለሁ ብሎ ትንሽ ነገር ሳያገኝ አልቀረም አንድ ሰሞን የጭቅጭቅ አጀንዳ ሁኖ ነበር እሳቶች እድሚያቸው ስለገፋ ተናዝዘው ቢሞቱ ደህና ነበር፡፡

  2. አትጃጃሉ ግብጽ ለኢትዮጵያ መልካም አስባ አታውቅም። በናስር ዘመን፤ በሳዳት ከዚያም ሆስኒ ሙባረክና አሁን ደግሞ በአልሲሲ ከተንኮል በስተቀር ምንም የተገኘ ነገር የለም። በምንም ስም ይሰየም፤ ከየትም ይምጣ ኢትዮጵያን የሚያባላ ሃይል ከሆነ ግብጽ ደጋፊ ናት። ይህ በግልጽ በዘመናት መካከል የታዬ እውነታ ነው። አሁን እንሆ ወያኔ ባርነት ትግራይን በመደገፍ ላይ ይገኛሉ። ለአረቦች የእኛ መገዳደል ደስታቸው ነው። አዲሱ የሱማሊያ መሪ ኤርትራን፤ ጅቡቲን፤ ቱርክን አሁን ደግሞ ግብጽን የሚጎበኙት ሰላም ፍለጋ አይደለም። ይህም በተግባር አሁን አልሸባብ በምስራቁ የሃገራችን ክፍል የከፈተው ግጭት ምስክር ነው። ዳቦ ያረረበት የግብጽ ህዝብ ጦርነትን አይሻም። ግን የአፍሪቃ መሪዎች ይበልጦቹ የሚዘወሩት በውጭ ሃይል በመሆኑ በራስ አስቦ ለራስ መኖር የተለመደ ጉዳይ አይደለም። ግድቡን እናፈርሳለን ሲሉ አለማፈራቸው ምን ያህል ሰው በዚያ ጎርፍ ተጠራርጎ ወደ ሜዲትራኒያን ባህር እንደሚገባ ሳያውቁት ቀርተው ነው። ግን እኛ ግብጾች አፍሪቃዊ አይደለንም የሚሉን እነዚህ ጉዶች ራሳቸውን ከሌላው አፍሪቃ ከለዪ ቆይተዋል።
    ስለሆነም ከግብጽም ሆነ ከሱዳን ጋር የሚደረግ ስምምነት ሁሉ ውሎ የማያድር የማታለያ ብልሃት ነው። እኔ እጅግ የማዝነው በዚህም በዚያም በሱዳንና በግብጽ እንዲሁም ከህዋላ ሆነው በሚሾፍሯቸው ስመ ዲሞክራሲ ነጮች ተገፍተው ወገናቸውን፤ መሰላቸውን፤ አፍሪቃን የሚያፈራርሱ የእኛው በእኛው የሆኑት እንደ ወያኔ ባርነት ትግራይና ደጋፊዎቻቸው ያሉት እጅግ ያሳዝኑኛል። ለህዝብ የሚያስብ የህዝብን ልጅ አያስጨርስም። የብሄር ነጻነት በለው፤ የክልል ወሰን ይሁን ሰው እንደ እሳት ራት እየገባ ሲነድ ማየት ያሳዝናል። በአፍሪቃ ታሪክ ውስጥ የነጻነት ታጋይ፤ አርነት አውጭ ገለ መሌ የሚባሉት ሁሉ ለራሳቸው ጥቅማ ጥቅም የተሰለፉ በህዝብ ስም የሚነግድና ከበፊቱ የከፋ ባርነትን በህዝብ ላይ የሚጭኑ የፓለቲካ ስብስቦች ናቸው። ገና በአፍሪቃ ጉድ እናያለን። ምላስ የምታክለው ኢኮቶሪያል ጊኒ ላይ በሃገሪቱ መንግስት የሚፈጸመው በደልና በሃገሪቱ የተገኘውን የነዳጅ ሃብት ለሃገሪቱ እንደመጠቀም 16% ብቻ ከአሜሪካው ገፋፊ የነዳጅ ኩባኒያ ሸቭሮን በመቀበል ሌላው ነጭ የሚከፋፈለው መሆኑ የቱን ያህል እየተቀለደብን እንደሆነ አስረግጦ ያሳያል። የኢኮቶሪያል ጊኒ መሪና ቤተሰብ እንዲሁም በዙሪያው ያሉ ዘራፊዎች ግን የሚኖሩት ኑሮ ሰማይ የነካ ነው። ይህ ነው አፍሪቃዊው መልካችን። በህዝብ ስም መነገድ፤ ሃገርና የሃገር ንብረትን አሳልፎ ለነጭ ማስረከብ። ይገባኛል እምቢኝ ያሉ ይቀነጠሳሉ። ግን የህዝብና የሃገርን ልኡላዊነት ለማስከበር መሞት ክብር ነው ለጊዜአዊ ጥቅም ሃገርና ህዝብን ከመካድ። ስለሆነም የአልሲሲ ንግግር የማዘናጊያ እንጂ በሱዳን፤ በሱማሊያ በሌሎችም ሃገሮች እያስታጠቀና እያሰለጠነ የላካቸው አጥፊ ሃይሎች ብዙ ናቸው። ለኦሮሞ ህዝብ ቆሜአለሁ የሚለው ኦነግ ሸኔ እልፍ እየገደለና የመገናኛና የህዝብ መገልገያ ሃብትን እያወደመ ለኦሮሞ ህዝብ ነው የሚለውን የግብጽና የወያኔ ሥራ አስፈጻሚ ስለሆነ እንጂ ለኦሮሞ ህዝብ ገዶት አይደለም። አፍሪቃውያኖች መቼ ይሆን የምንነቃው? ቆዳው የነጣ ሁሉ የሰማይ መልአክ አስመስለን ከማየት መቼ ነው የምንላቀቀው? አረቡና ነጩ ዓለም ተንኮሉ ረቂቅ ነው። ከሳውዲ ምድር የኢትዮጵያዊያን መባረረ ከግብጽ ሴራ ጋር የቀጥታ ግንኙነት አለው። ግን ሰውን በመጋዝ ከሚሰነጥቅ መንግስት ምን አይነት ስብዕና ይጠበቃል? ምንም። የአል ሲሲም ሃሳብ ፍሬፈርስኪ ነው። ጉዳዪ ትብትብ ነው። ሚስጢሩ እንደ ሜዲትራኒያን ባህር የጠለቀ ነው። ቆይተን የሚሆነውን እንይ። በቃኝ!

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share