በምሬ ወዳጆ የሚመራው የምስራቅ አማራ ፋኖ መግለጫ አወጣ “ሚሊሻ እንድንሆን እየተጠየቅን ነው”

በአርበኛ ምሬ ወዳጆ የሚመራው የምስራቅ አማራ ፋኖ ዛሬ ባወጣው መግለጫ፣ መንግስት ‘ስለ ወቅታዊው የሕወሓት ወራራ እንወያይ’ ብሎ ትናንት ሰኔ 28 ቀን 2014 ዓ.ም በወልዳያ ከተማ ስብሰባ ከጠራቸው በኋላ፣ አጀንዳውን ቀይሮ ሚሊሻ እንዲሆኑ የጠየቃቸው መሆኑን ይፋ አድርጓል። እንዲሁም፣ በማንኛቸውም መንገድ ፋኖ ከህዝብ ገንዘብ እንዳይሰበስብ አቅጣጫ አስቀምጧል።

የምስራቅ አማራ ፋኖ ፣ “በቆቦ ከተማ እና በራያ ቆቦ ወረዳ ፣በሁሉም ቀበሌዎች፣ መንግሥት በፋኖ ስም የሚሰበሰበው ገንዘብ የፋኖ አለመሆኑን ሁሉም ህዝባችን እንዲያውቀዉ” ሲልም አሳስቧል።

“የአባቶቻችንን የደም አርበኝነት እና የግብር ፋኖነት መቼም በምንም ሁኔታ አንተዉም” ያለው ፋኖ፣ አገዛዙ በአነሳቸው ጉዳዮች ላይ እንደሚከተለው አቋሙን አሳውቋል፦

፩. ፋኖነት ስማችን ብቻ ሳይሆን፣ ደምና አጥንት የተገበረለት የአባቶቻችን ዉርስ፣ ዛሬም ያለ ወደፊትም ከአማራ ህዝብ ጋር ህያው ሆኖ የሚኖር ስሪታችን ነው። አባቶቻችን በአድዋ፣ በማጨው፣ በጋራ ሙለታ፣ በመቅደላ መድፍና ታንክ ይዞ የመጣ የዉጭን ወራሪና ቅኝ ገዥ ኃይል በባህላዊ መሳሪያ በሆኑት ጦርና ጋሻ አንበርክከው የቀጡበትና ዋጋ የከፈሉበት “እምቢ ለአገሬ፣ ለነጻነቴ”ብለው በፋኖነት እንጂ፣ ሌላ ተቀጽላ ወይም የተዉሶ ስም አልነበራቸዉም። ስለሆነም፣ ከአባቶቻችን የወረስነዉን ፋኖነት፣ እኛ አልፈንበት ለልጆቻችን የምናወርሰው ቅርሳችን መሆኑን እናሳዉቃለን።

፪.ፋኖ ያለ ደመወዝ ለአማራ ህዝብ ብሎም ለሀገሩ ኢትዮጵያ አንድ ህይወቱን ለመስጠት የተዘጋጀ፣ እየሰጠም ያለ ስለሆነ፣ ህዝብ በትጥቅ እና ስንቅ እንዲደግፈን አጥብቀን እንሰራለን።

፫. የትግራይ ወራሪ ኃይል ለዳግም ወረራ በተዘጋጀበት እና የአማራን ህዝብ በጠላት ፈርጀው ከሚንቀሳቀሱና ዓላማቸው የአማራን ህዝብ እንደ ህዝብ ለማጥፋትና ሀገር-አልባ ለማድረግ በሚንቀሳቀሱበት በዚህ ግዜ፣ እንደዚህ ዓይነት አጀንዳ ማንሳቱ ወቅቱን ያላገናዘበ ድርጊት መሆኑን ለማሳወቅ እንወዳለን።

ተጨማሪ ያንብቡ:  በአርባ ጉጉ እና አካባቢው በዐማራው ህዝብ ላይ የተፈጸመውን የዘር ማጥፋት ወንጀል መካድ አይቻልም

#ኢትዮጵያ

ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ 

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share