ይነበብ «ወላሂ ሁለተኛ አማራ አልሆንም» የ 6 ዓመቷ ህፃን ከወለጋ

” ራሴን በተረፈረፉ ሬሳዎች ውስጥ አገኘሁት። ካንገቴ ቀና ስል አንዲት ህጻን (በግምት 6አመት) በ6ታጣቂዎች ተከባለች። እኔ እዛው አጠገባቸው ብሆንም ከተረፈረፈው ሬሳ እንደ አንዱ ስለቆጠሩኝ አላስተዋሉኝም።
ህጻኗን ባማርኛ ያናግሯታል፤ ከዛ ሁሉም ባንዴ ድምጻቸው የገደል ማሚቶ እስኪያስተጋባ ይስቃሉ። በመጨረሻ ህጻኗ ጮክ ብላ ይሄንን ስትል ሰማኋት
“ወላሂ ሁለተኛ አማራ አልሆንም”።
ቀጥሎ የሰማሁት ድምጽ የጥይት እሩምታ ነበር። ለማየት በሚያሣሣ ገላዋ ላይ እሽቅድምድም በሚመስል መልኩ ሁሉም የጥይት አረር አዘነቡባት። ሞታ እንኳን የሚረኩ አይመስሉም ነበር።
ነብሴን ለማትረፍ ከነ ሲቃየ ዝም አልኩ። ከሁሉም ነብሴ ትበልጥብኝ ነበር። ማክሰኞ ህጻኗ የሞተችበት ቦታ ተሰብስበን ሄደን ነበር፤ የለችም፣ ካሣደገኝ አጎቴ ሞት በላይ እስካሁን የምትጠዘጥዘኝ ህጻን!
አፈሩ ይቅለልሽ»
Melat Dawit
ተጨማሪ ያንብቡ:  እስክንድር ነጋ እመራዋለሁ የሚለው የአማራ ህዝባዊ ሰራዊት የሚባል አለ ወይ?

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share