May 30, 2022
2 mins read

ለጀነራል ተፈራ ማሞ ተጨማሪ የ10 ቀናት ቀጠሮ ተሰጠ

Tefera Mano
Tefera Manoየቀድሞው የአማራ ክልል ልዩ ኃይል አዛዥ ብርጋዴር ጀነራል ተፈራ ማሞ ዛሬ ለሁለተኛ ጊዜ ባህርዳር አማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ቀርበው ተጨማሪ የ10 ቀናት የጊዜ ቀጠሮ ተሰጣቸዉ፡፡ መርማሪ ፖሊስ ዛሬ ለፍርድ ቤቱ ጀነራል ተፈራ ማሞ ላይ የቀሩኝ የማሰባስባቸው ማስረጃዎች አሉኝ ሲል የ14 ቀናት ቀን ጠይቆ ነበር። የጀነራሉ ጠበቃ በበኩላቸው ቀሩ የተባሉ ማስረጃዎች ተጠርጣሪው በዋስ ቢወጣ ሊያጠፋቸውና ሊያገኛቸው የሚችሉ ባለመሆናቸው ደንበኛቸው ከፖሊስ ጣቢያ በዋስ ተለቅቀው እንዲከራከሩ ጠይቀዋል፡፡ ጠበቃ ሸጋው አለበልን ከችሎት በኋላ የዶይቼ ቬሌ ዓለምነዉ መኮንን አነጋግሯቸው ነበር፡፡
የሁለቱንም አካላት ክርክር ያዳመጠው የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ተጨማሪ የ10 ቀናት የምርመራ ጊዜ ፈቅዷል፡፡ ዛሬም ተጠርጣሪው ፍርድ ቤት በመጡበት ወቅት ቁጥሩ በዛ ያለ የፀጥታ ኃይል ከፍተኛ ጥበቃ ሲደርግ ነበር፡፡ ብርጋዴር ተፈራ ማሞ ህገ-መንግስታዊ ስርዓቱን የሚፃረር መልዕክቶችን በተለያዩ ሚዲያዎች ሲያስተላልፉ ነበር በሚል ተጠርጥረው በመንግስት ቁጥጥር ስር የዋሉት ግንቦት 8 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ውስጥ ነበር፡፡
ዘገባ ፤ዓለምነዉ መኮንን DW ከባህር ዳር/ DW

Leave a Reply

Your email address will not be published.

f4e8569bda61082637e051bd7072941e
Previous Story

የአማራ ሕዝብና የአጭቤ ዜናው አባት አማራጠሉ ቢቢሲ

military
Next Story

ባለሀብቶችን በማገት እና በማስፈራራት ብር በጠየቁ የሰራዊቱ አባላት ላይ ክስ ተመሠረተ

Latest from Blog

አስቸኳይ ህዝባዊ ጥሪ

July 24, 2024 ዓለማቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያዊያን መብት Global alliance for the Rights of Ethiopians (GARE) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሳቻ ጎዝዲ ቀበሌ በደረሰው የመሬት መንሸራተት የብዙ ወገኖቻችንን ህይዎት ማለፉን
Go toTop