በዛሬው ዕለት ግንቦት 22/2014 በፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ አራዳ ምድብ ችሎት ፍርድ ቤት የቀረበው ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ በሁለተኛ ቀን ቀጠሮው ፖሊስ ጋዜጠኛውን በምን ወንጀል እንደሚጠይቅ ስላማናውቅ ምርመራው ተጣርቶ ሲያልቅ የሚጠየቅበትን ለመወሰን የተጠየቀው ዋስትና ሳይፈቀድለት ለግንቦት 29/2014 ጠዋት 3:30 ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል::
ጠበቃ ሔኖክ አክሊሉ እንዳሉት በምንም ነገር ቢጠየቅ ጋዜጠኛ በመገናኛ ብዙሃን አዋጅ መሰረት ዋስትናው ትከብሮለት ነው የማጣራት ሂደቱ መታየት ያለበት ሲሉ ሙያዊ ማብራሪያ ሰጥተዋል።
ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ፣ ለ30 እስረኞች በተዘጋጀ ክፍል ውስጥ 400 እስረኞች በአንድ ላይ ታስረው በሚገኙበት ክፍል ውስጥ ታስሮ እንደሚገኝ ጠበቃው ለችሎቱ ተናግረዋል።
በሌላ በኩል በዛሬው ችሎት አዲስ ዳኛ የተለወጡ ሲሆን፤ ዳኛው የግራ ቀኝ ሀሳብ ከመስማት ይልቅ ቀጥታ ወደውሳኔ (የቀጠሮ ጊዜ) ሀሳብ መግባታቸው ብዙዎቹን የችሎቱ ታዛቢዎች ያስገረመ ጉዳይ ሆኗል።
የጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ እስራት በነፃ ጋዜጠኝነት ሙያ ላይ የተከፈተ ጦርነት ነው። የታሰረው አንድ የነፃው ፕሬስ መሪ ተዋናይ ብቻ ሳይሆን ኢትዮጵያዊነት ነው።
በኢትዮጵያ የነፃው ፕሬስ ታሪክ ውስጥ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ከ13 ዓመታት በላይ ስለፍትሕ፣ ነፃነትና እኩልነት ዘር ቀለም ኃይማኖት ሳይለይ የታገለ የግፉዓን ድምፅ ነው። የጋዜጠኛው እስር የኢትዮጵያ የሽግግር ዴሞክራሲ ለመጨናገፉ አንድ ማሳያ ሆኖ ይቀርባል።
የ Pen2Pen Freedom of Expression Award 2020 ተሸላሚው ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ የሙያ መርሆዎቹ ፦ ነጻነት፣ ፍትሕ፣ እና እኩልነት፣… ናቸው።
ቤተሰቦቹ እና የፍትሕ መጽሔት ባልደረቦች