ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝን በተመለከተ

የሁለተኛ ቀን መረጃ
***
ከረፋድ እስከ ምሳ ሰዓት ድረስ
➖
ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ በዛሬው ዕለት ግንቦት 19/2014 ረፋድ 4:30 ከአዲስ አበባ ፖሊስ በተለምዶ ሦስተኛ ፖሊስ ጣቢያ አግንተነዋል።
ፖሊስ ‘ተጨማሪ ፍተሻ ማድረግ አለብኝ’ በሚል የፍትሕ መጽሔት ቢሮ ወደሚገኝበት ወደአድዋ ድልድይ፣ በቀይ ዶልፌን ኮድ 3 መኪና፣ ጋዜጠኛ ተመስገንን ይዘው በመምጣት ለ1 ሠዓት ከ40 ደቂቃ በቢሮው ውስጥ ፍተሻ አድርገዋል።
በፍተሻቸው ትላንት በመኖሪያ ቤቱ እንዳደረጉት በቢሮው ውስጥ የሚገኙ የታተሙ የፍትሕ መፅሔት ህትመቶችን እና ተጨማሪም ቢሮ ውስጥ የተገኙ፦
???? አንድ የ”ጊዮን” መፅሔት ዕትም፣
???? አንድ “አዲስ ምንጭ” የተሰኘ ሌላ መፅሔት
ዕትም፣
???? አንድ ሀርድ ዲስክ፣
???? ሦስት ሲዲ እንዲሁም፣
???? በእጅ የተፃፉና በኮምፒውተር የተፃፉ ወረቀቶችን ይዘው ወደ ሦስተኛ ፖሊስ ጣቢያ ይዘው ተመልሰዋል።
ሁሉም መፅሔቶች ከዚህ ቀደም ለአንባቢያን የደረሱ ዕትሞች ሲሆኑ፤ ዛሬ በተጨማሪነት የተወሰዱ ሦስት ሲዲዎችና አንድ ሀርድ ዲስክ የፍትሕ መፅሔት ዕትሞች በሶፍት ኮፒ የተከማቹባቸው ፋይሎች ናቸው።
ከሠዓት በኋላ (8:00)
➖
ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ፣ ዛሬ ከቀኑ 8:00 ሠዓት አካባቢ በፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ አራዳ ምድብ ችሎት ፍርድ ቤት የቀረበ ሲሆን፤ ፖሊስ “ሁከትና ብጥብጥ ለማስነሳት በመስራት ጠርጥሬዋለሁ” ብሏል።
ለዚህ ጥርጣሬው በዩት ዩቦች የተለያዩ ቃለ-መጠይቆችን ሰጥቷል፣
ሕዝብ በመከላከያ ሰራዊቱ ላይ እምነት እንዳይኖረው ሰርቷል በማለት ጥርጣሬውን አቅርቧል-ፖሊስ።
የጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ጠበቃ ሔኖክ አክሊሉ ደንበኛቸው በዩት ዩብ ኢንተርቪው መስጠት ካቆሙ አራት ዓመት እንደሚሆን ለፍርድ ቤቱ ያስረዱ ሲሆን፤ ደንበኛቸው በኢትዮጵያ ነፃ ፕሬስ ታሪክ ውስጥ ጉልህ አበርክቶ ያላቸው ነባር ጋዜጠኛ እንደመሆናቸው መጠን፣ ተቋማዊ ችግሮችን ነቅሶ በማውጣት ለሀገር በሚበጅ መልኩ የመፍትሔ ሀሳብ በማቅረብ እንደሚታወቁ በመግለፅ፣ መከላከያ እንደተቋም ‘ስሜ ጠፋ’ ባላለበት ሁኔታ፣ ፖሊስ በጥርጣሬ ጉዳዮን ለማቅረብ መሞከሩ እንደማያስኬድ ለፍርድ ቤቱ አስረድተዋል።
ፖሊስ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝን ለመጠየቅ ማስረጃ አለኝ ብሎ ካመነ በፕሬስ አዋጁ 1238/2013 መሰረት መጠየቅ ሲገባው በወንጀል ሥነ-ሥርዓቱ አግባብ ማቅረቡ ለዚህም የጊዜ ቀጠሮ መጠየቁ ተቀባይነት እንደሌለው ጠበቃ ሔኖክ አክሊሉ ለፍርድ ቤቱ አስረድተዋል።
ፍርድ ቤቱ የግራ ቀኝ ሀሳብ አድምጦ ለሰኞ ግንቦት 22/2014 ጠዋት 3:30 ቀጠሮ ሰጥቷል።
➖
ከጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ጋር ስለእስሩ ሁኔታ ለመነጋገር ዕድሉን ባናገኝም፣ ቢሮው እየተፈተሸ በነበረበት ወቅት እና በችሎት ሰዓት በሙሉ የራስ መተማመን ስሜት ተመልክተነዋል።
ቤተሰቦቹ እና የፍትሕ መፅሔት ባልደረቦች

Tariku Desalegn Miki

ተጨማሪ ያንብቡ:  በመላው አለም ከሚኖሩ የአርማጭሆ ተወላጆች የተሰጠ መግለጫ

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share