የኦሮሚያ ክልላዊ መስተዳዴር አሳሳቢ መግለጫ አወጣ!

“የዐማራ ፅንፈኞች” በኦሮሚያ ክልል ዘልቀው ጥቃት አድርሰዋል አለ!
የኦሮሚያ ክልላዊ መስተዳድር ባወጣው መግለጫ፣ በዐማራ ክልል አሉ ያላቸውን “ፅንፈኞች” በትዕግሥት አልመለከታቸውም ብሏል። በቅርቡ በሚንጃር አካባቢ የተከሰተውን ችግርም በዐማራ ክልል ያሉ ኃይሎች ላይ አላኳል።
መግለጫው በከፊል እንዲህ ይነበባል:-
እዚህም እዝያም የሚታየውን ጽንፈኝነት እያባባሰ ያለው አንዱ ምክንያት በባህሪው ላይ ተመሳሳይ እይታና አቋም አለመያዛችን ነው፡፡ በዚሁ መሰረት ጽንፈኝነት ከየትም ይምጣ ከየት እሳቤውና ተግባሩ ጸረ-ህዝብ መሆኑን ተገንዝቦ በጋራ መተጋል ሲገባን ጣት መቀሳሰር ጎልቶ ይታያል፡፡ የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስትም ጽንፈኝነት የትም ይብቀል የት ጸረ-ህዝብ መሆኑን በጽኑ አምኖ በመታገል ላይ ይገኛል፡፡ በዚሁ መሰረት ከአሸባሪው ሸኔ ጋር በሚደርገው ትግል ውድ መሰዋትነት እየከፈለ ይገኛል፡፡ በዚህ ደረጃ የሚከፈለው መሰዋትነት ጽንፈኝነት ሀገር-አፍራሽ መሆኑን በጽኑ አምነን ሀገርና ህዝብን ለመታደግ እንጂ በአማራ ስም ለሚንቀሳቀሱ ጽንፈኛ ሀይሎች እድል ለመከፈት አይደለም፡፡
ከዚህ አንጻር የአማራና የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦች ቀንደኛ ጠላት የሆኑት በአማራ ስም የሚንቀሳቀሱ ጽንፈኛ ሀይሎች በኦሮሚያ ክልል ውስጥ ዘልቀው በመግባት በሰላማዊ ዜጎችና ጸጥታ አካላት ላይ የፈጸሙት አጸያፊ ድርጊት የክልሉን ህዝብ ክፉኛ አስቆጥቷል፡፡ ይህ ጽንፈኛ ሀይል ስለፈጸመው አጸያፊ ድርጊት የክልሉን የመንግስት ሚዲያ ጨምሮ በተለያዩ የመገናኛ አውታሮች ሲያስተጋቡ፤ ጥላቻን ሲሰብኩና የግጭት ነጋሪት ሲጎስሙ በዝምታ ማያት ተጋቢ አለመሆኑን የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በጽኑ ያምናል፡፡
ዝርዝር ዘገባዎችን እየተከታተልን እናወጣለን።

ተጨማሪ ያንብቡ:  ብ/ጀኔራል ተፈራ ማሞ አዲስ የተመደቡበትን ስራ እንደማይቀበሉት ተገለፀ

1 Comment

  1. ሂድ እንግዲህ ፊሽካው ተነፋ ባላዋቂ ሀይሎች ኢትዮጵያም ኦሮሞም የሚቆስሉበት። ሽመልስ አብዲሳ እብሪት የውድቀት መጀመሪያ ነው ሰከን ማለት መልካም ነው ሲኒ ትሰብራለህ። ደመቀ መኮንን፣አገኘሁ ተሻገር ሌሎች ባለሟሎች መበያችሁ ደርሷል ፫አመት ማስተካከያ ጊዜ ተሰጥቷችሗል አልተጠቀማችሁበትም።

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share