በምንጃር ሸንኮራ ወረዳ በተፈጸመ ጥቃት ቁጥራቸው በወል ያልታወቀ ሰዎች መገደላቸው ተነገረ

በኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ ወለጋ ዞን ኪራሙ ወረዳ ነሐሴ 12/2013 ዓ.ም ጀምሮ በታጣቂዎች በተፈፀመ ጥቃት እና ግጭት በርካታ ሰዎች መገደላቸውን ከጥቃቱ የተረፉ ነዋሪዎች እና የዞኑ አስተዳዳሪ ለቢቢሲ ተናገሩ።

ለደኅንነታቸው ሲባል ስማቸ እንዳይገለጽ የጠየቁ ነዋሪ ለቢቢሲ እንደገለጹት በአካባቢው መንግሥት ኦነግ ሸኔ እያለ የሚጠራቸው ታጣቂዎች ቀደም ብሎም እንደሚንቀሳቀሱ አስታውሰው፤ በነዋሪዎች ላይ ግድያውን የፈጸመው ይህ ታጣቂ ቡድን መሆኑን ይናገራሉ።

የአማራ ብሔር ተወላጅ የሆኑት ነዋሪው እንደሚሉት በስፍራው የነበረው የኦሮሚያ ልዩ ኃይል ከስፍራው መውጣቱን ተከትሎ ታጣቂዎች በነዋሪዎች ላይ ጥቃት ማድረሳቸውን ገልጸዋል።

“በነሐሴ 11 ልዩ ኃይሎቹ ከአካባቢው ወጥተው ኦነግ ሸኔ በ12 ወረራ ጀመረ። ከስፍራው የነበሩ በርካታ ሰዎች ተገድለዋል፤ ማንም የተረፈ የለም። ንጹሀን ተጨፍጭፈው ቀሩ። ንብረት ሁሉ ተቃጠሎ ወደመ” ይላሉ።

ነዋሪው በጥቃቱ የሞቱ ሰዎች በመቶዎች እንደሚቆጠሩ የተናገሩ ሲሆን በአሁኑ ጊዜ ከ8 ሺህ በላይ ሰው ተፈናቅሎ በወረዳው ከተማ እንደሚገኝ አመልክተው “ለተፈናቃዩ ሕዝብ የደረሰ እርዳታ የለም” የለም በማለት በችግር ላይ መሆናቸውን ተናግረዋል።

የምሥራቅ ወለጋ ዞን አስተዳዳሪ አቶ አለማየሁ ተስፋ ለቢቢሲ እንደገለጹት ከአምስት ቀናት በፊት በአካባቢው ግጭት እንደነበረ አረጋግጠው፤ ጉዳት የደረሰው “የጁንታው ተላላኪ በሆነው ሽፍታው ሸኔ እና በአማራ ታጣቂዎች” ምክንያት ነው ብለዋል።

ጨምረውም “ጥቃቱን በዋናነት የሸኔ ሽፍታዎችና የጁንታው ተላላኪዎች ናቸው በኦሮሞና በአማራ ሕዝብ ላይ ተኩስ በክፈት የፈጸሙት። ታጥቀው የሚንቀሳቀሱ የአማራ ታጣቂዎችም አሉ። አሁን ግጭቱ ቆሟል” ብለዋል።

የአካባቢው አስተዳዳሪ አቶ አለማሁ እንዳሉት “በአሁኑ ወቅት የፀጥታ አካላት ገብተው እርምጃ እየወሰዱና ሕዝቡን እያረጋጉ ነው። እስካሁን ድረስ በግጭቱ የሞተውና የተጎዳው ሰው ቁጥር እየተጣራ ነው። ውጤቱ ሲደርስ እናሳውቃለን” ሲሉ ተናግረዋል።

ተጨማሪ ያንብቡ:  ‹‹ ዳግም ሞት ›› የመተከል ተፈናቃዮችን ሰቆቃ የሚያሳይ ሙሉ ዶክመንታሪ

በስፍራው ይንቀሳቀሳሉ ያሏቸው “ሽፍታው ሸኔ እና የአማራ ታጣቂዎች” የተኩስ ልውውጥ ማድረጋቸውን ተናግረው፤ “እነዚህ ሁለት ቡድኖች እርስ በእርሳቸው ተታኩሰዋል። ሕዝብም ላይ ተኩሰዋል” ብለዋል አስተዳዳሪው።

የሁለቱ ቡድን ዓላማ “ለብዙ ዓመታት አብሮ በሰላም የኖረን ብሔር ማጋጨት ነው” ያሉት አቶ አለማየሁ፤ በግጭቱ የሰዎች ሕይወት ማለፉን እና በርካታ ሰዎች ከቀያቸው መፈናቀላቸውን አረጋግጠዋል።

በአሁኑ ወቅት በአካባቢው መረጋጋት መኖሩን እና ከቀያቸው የተፈናቀሉትን መልሶ ለማቋቋም የሚመለከታቸው ባለሥልጣናት ርብርብ እያደረጉ እንድሚገኙ አክለዋል።

ሌላኛው ያነጋገርናቸው ነዋሪ ደግሞ በአካባቢው በኦሮሞና በአማራ ተወላጆች መካከል ግጭት እንደነበር ተናግረው ጉዳት የደረሰውም በዚሁ ምክንያት ነው ብለዋል።

“በአማራ እና በኦሮሞ ማኅበረሰብ መካከል ግጭት ነበር። ከድሮ ጀምሮ የሚኖሩ የአማራ ማኅበረሰቦች ነበሩ። ከዚህ ቀደም በተፈጠረ ግጭት ምክንያት ወደ ክልላቸው ከሄዱ በኋላ ሴቶች እና ሕጻናትን ትተው ወደ አካባቢው ተመልሰው በመምጣት እዚያ ከሚኖር የኦሮሞ ማኅበረሰብ ጋር ተጋጭተዋል” ይላሉ የኦሮሞ ብሔር ተወላጁ።

ነዋሪው ይህን ይበሉ እንጂ የዞኑ አስተዳዳሪ ለቢቢሲ እንደተናገሩት ከአማራ ክልል ወደ አካባቢው የገባ ታጣቂ የለም።

“በማኅበራዊ ሚዲዎችያ ላይ ብዙ ነገር ይወራል። በተለያየ መንገድ ብሔሮች አንዲጣሉ ይደረጋል። ነገር ግን ከሌላ አካባቢ ገቡ ስለተባሉት ታጣቂዎች ምንም ማስረጃ የለም። ካለም ወደፊት እንናጣራለን” ብለዋል የዞኑ አስተዳዳሪ አቶ አለማየሁ ተስፋ።

ቢቢሲ በጥቃቱ የደረሰውን ጉዳት ለማወቅ ባደረገው ሙከራ ከተለያዩ ወገኖች መጠኑ የተለያየ አሃዝ ያገኘ ሲሆን ነገር ግን በርካታ ቁጥር ያላቸው ሰዎች መገደላቸው ተገልጿል።

በንብረትም በኩል ቤቶች መቃጠላቸው የተነገረ ሲሆን በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ደግሞ ከጥቃቱ ሽሽት ቤት ንብረታቸውን ትተው ወደ አቅራቢያ አካባቢዎች መሄዳቸው ተነግሯል።

ተጨማሪ ያንብቡ:  ኢትዮጵያ የ'ስዊድን 'ሳይሆን የራሱዋ 'ጠቅላይ ሚኒስትር' ያስፈልጋታል

መንግሥት ሸኔ የሚለውና በሽብርተኛነት የተፈረጀው እንዲሁም በቅርቡ ከህወሓት ጋር ጥምረት መፍጠሩን ያሳወቀው እራሱን የኦሮሞ ነጻነት ጦር አሁን ጥቃቱ በተፈጸመበት አካባቢ ታጣቂዎቹ ከዚህ በፊት ጥቃት መፈጸማቸው አይዘነጋም።

 


 

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share