730 ቀናት ለሃይማኖት ነፃነት (730 Days For Religious Freedom) ዘጋቢ ፊልም ይፋ ሆነ

የኢትዮጵያ ሙስሊሞች እንቅስቃሴ የተጀመረበትን ሁለተኛ ዓመት ለማሰብ ድምጻችን ይሰማ “730 ቀናት ለሃይማኖት ነፃነት (730 Days For Religious Freedom)” የሚል ዘጋቢ ፊልም አዘጋጀ። 56 ደቂቃ ከ34 ሰከንድ የሚፈጀው ይኸው ፊልም ለዘ-ሐበሻ አንባቢዎች ግንዛቤ ይረዳ ዘንድ አስተናግደነዋል – እነሆ፦

ተጨማሪ ያንብቡ:  በኢትዮጵያ አየር መንገድ ትሰራ የነበረች አንዲት ቻይናዊት ሆስተስ በፖሊስ ከአገር ተባረረች

2 Comments

  1. From GETACHEW REDA (Editor Ethiopian Semay)

    ጌታቸው ረዳ (ኢትዮጵያን ሰማይ ድረገጽ አዘጋጅ)

    ለኢሳት ዘጋቢ ፊልም ጥያቄ።

    የሚከተሉት ጥያቄዎች ለፊለሙ አዘጋጅ መለስ ይሻሉ። መልስ ካላገኙ፤ ፊለሙ መልዕክቱን ያበላሸዋል ማለት ነው። ምክንያቱም አነዚህ ውንጀላዎች እውነትነት ያላቸው መሆናቸው እና አለመሆናቸው በመረጃ ማቅረብ የጠበቅበታል።

    እንዲሁ በግርድፍ እንደ ወያኔዎቹ ተቀበሉን ካላላችሁን ወይንም መጠየቅ “አይቻልም፤ ሃጢያት ነው” ካላላችሁ፤ ጥያቄዬ ይኼው።

    1) “አሕባሽ የተባለ በጽዮናዊያን አይሁዶች የሚደገፍ” መረጃችሁ ምንድ ነው? ይህ አባባል ‘አንዳንዶቹ’ አፍቃሬ ግራኝ አህመዶች ከመታሰራቸው በፊት ከአንዳንዶቹ አንደበት ተመሳሳይ ውንጀላ አድመጫለሁ። ለመረጃ ጠይቄ- እስካሁን ድረስ መልስ አልተሰጠም። አሁንም በዚህ ፊልም ተደግሟል። እባካችሁ መረጃ። አይሁዶች አሕባሽ ወደ ኢትዮጵያ ያስገቡበት መረጃ እባካችሁ ስጡን።

    2) 17 አመት በትዕግስት ዘልቋል። ወያኔ ከመጣ 22 ዓመት ሊሆነው ነው። 5 ዓመት ተወካዮቻችሁ እቦታው ላይ ነበሩ መለት ነው? አልገባኝም፤ ማብራርያ!

    3) አወልያ ያክራሪ እስላም መፈልፈያ ማዕከል ነበር፤ ስለዚህ አፈራርሰነዋል። የአውልያ ተማሪዎች “መልስ” ብሎ ፊለሙ ያቀረበው ደግሞ “አንዲት ወጣት ሴት “መቸ ነው አወልያ የፈራረው……” የሚል ነው። ፊለሙ ሊያስሰማን ያልቻለው ግን “ የአሕባሽ መሪዎች እና ተከታዮቻቸው…ከኢትዮጵያ ለቀው ይውጡ” ነበር ያሉት። ለምን ቆርጣችሁ አወጣችሁት? ይህ ምን ማለት ነው። ካሁን በፊት አውድዮው አሰምቻችሁ ነበር።

    4) ዘጋቢዎች፤- የሰላም አምበሳደሮች፡ የምትሏትን አባባል አልስማማበትም። ከመታሰራቸው በፊት ሲሰብኩዋቸው የነበሩ ፖለቲካዊ አስተምህሮዎች እና የጻፏቸው መጽሐፍት በሙሉ ከወያኔአዊ ውሸት አይለዩም። ግራኝን የነፃነት አርበኛ ይሉታል።፡ኢትዮጵያን 100 አመት ይሏታል። እኛ የምናውቀው ሌላ ተሪክ ነው። እነሱ ከታች ተነስተው ያጥለቀለቁትን ምድር አንኳ ከመቶ አመት በፊት አንደነበር ሰነዶች ማቅረብ ይቻላል።እነኚህ የሃይማኖት መሪዎች ሃይማኖት ሰባኪዎች ወይስ ፖለቲከኞች? እንዲህ ያሉ ሰዎች “የሰላም አምባሰዳር አንዴት ሊሆኑ ይችላሉ? ግራኝ ሰላማዊ እና የነፃነት አባት እያሉ የሚሰብኩ?
    ለነገሩ እንዚህ እስልምና ተደፈረ የሚሉን እስላም ወገኖች፤ ምነዋ ክርስትያኑ አንደጮኸላቸው ለክርስትያኑ አልጮኹም? ይህነን ይመልከቱ፤

    በኢትዮጵያ የአክራሪ እስልምናው የ፲፱፻፹ዎቹ እንቅስቃሴ ፖለቲካዊ ጥላውን የዘረጋ፤ ስውር ነበር ማለት ይቻላል። “ቀደም ባሉት ዘመናት የነበሩት የኢትዮጵያ ነገሥታት የእስልምና ሃይማኖትን ጨቁናዋል”፤ “እስላሞች የሚገባቸውን ቦታ አላገኙም”፤…የመሳሰሉትን ደጋግመው በማሰማት ለእስላሞች መብት የቆመ ይመስል ነበር። ይሁን እንጂ ዓላማውና እንቅስቃሴው እንደሚያሰማው ድምፅ ቦታዬን ላግኝ ብቻ አልነበረም “ዋሽንግተን ያለው ሰውየ ሚስቱ- ሸሪዓ/ኸሊፋ ይመጣል” አንዳለቺው ማለት ነው!) ይህን ለማየት ባሳለፍናቸው ዘመናት የተከናወኑ ድርጊቶች መቃኘት ያስፈልጋል። ይህ ክንውን ሲደረግ የእስላም ልሳኖች ነን የሚሉን አሁን በየሚዲያው ከተቃዋሚ ክርስትያን ሚዲያዎች ጋር እየጮኹ ያሉት ምንም ያወገዙት ወይንም ያጋለጡት ነገር አንድም የለም። ይባስ በሎ ‘በፓል ቶክ’ አክራሪዎች ሲጨኹ ምንም ያሉት ነገር የለም። እስኪ ይህን እንመልከት። ሃይማኖታዊ ብሔረተኞች እና ጐሰኛ ብሔረተኞች ከዚህ በታች ያለው ጉድ ሲፈጸም ምን አደረጋችጀሁ? ጩኾታችሁ ምን ነበር?

    ብዙዎቻችን ባልተረዳንበት ጊዜ አክራሪዎች በኦሮሚያ እና በደቡብ ባሉ አንዳንድ አካባቢዎች ክርስቲያኖቹን ለይተው “ነፍጠኞች” በማለት ነገራቸውን መደባዊ ፖለቲካ በማስመሰል ብዙ በደል አድርሰዋል።በተለይ በጅማ እና በኢሊባቡር አካባቢ ክረስትያን ሆኖ መገኘት “ነፍጠኛ” ለመባል ቀዳሚ ምስክር የሆነ እስኪመስል ድረስ ፍጹም ድሆች እንኳ ሳይቀሩ በክርስትናቸው ብቻ ተገፍተው ነበር። አክራሪዎች ይህ የማስመሰል ሒደታቸው እንዳልተነቃበት ሲያስተውሉ ነበር አካባቢውን ሙሉ በሙሉ የእስላማዊ ነፃ አካባቢውን ሙሉ በሙሉ የ እስላማዊ ነፃ መሬት ብቻ ለማድረግ በነበራቸው ጽኑ ፍላጐት ሰይፋቸውን ይዘው የወጡት።
    በሓረር ገለምሶ፤ በአርሲ የተለያዩ ቦታዎች ያየነው የ፲፱፻፹ዎቹ (የ1980ዎቹ) አሰቃቂ ግፍ ፖለቲካዊ ርእዮተ ዓለምን ተገን ያደረገ የአክራሪዎቹ ዘመቻ መሆኑን አሁን መገንዘብ ይቻላል። የአክራሪ እስልምናው አራማጆች ይህም ተገልጦ ሳይነገርባቸው ሲቀር እንደገና ቀስ እያሉ ወደ ባሱ የድፍረት ሥራዎች ተሸጋገሩ። በተለያዩ ቦታዎች አብያተ ክርሲያናትን ማቃጠል፤ካህናትን ማሠርና መደብደብ፤አልፎ አልፎም በስውር መግደል፤ክረስቲያን ሴቶችን አስገድዶ መድፈር፤ካህናትን ሻሽ እንዳይጠመጥሙ የክርስትና ምልክት እናዳይዙ መከልከል ዋና ዋናዎቹ መገለጫዎቻቸው እየሆኑ መጡ። እነዚህ ዘገምተኛ ጥቃቶች ሲያደርጉ የተለየ ትኩረት አልተደረገም።
    ደረጃ ሁለት፦————

    አክራሪ እስልምናው ቀደም ብለን የገለጽነውን ሁሉ እያደረገ ዝም በተባለ ጊዜ ወደ ሁለተኛ ትንኰሳ ተሸጋገረ።ሁለተኛው ደረጃ “እዚያ ማዶ ጠብ አድርሰኝ” ዓይነት መርሕን ይዞ የተነሣ ነበር። የሕዝቡ በውል ያለመረዳት ያስተዋለው የአክራሪ እስልምና እንቅስቃሴ ምክንያት እየፈጠረ ግጭት ማስነሳቱን ጀመረ። እጅግ በሚያሳዝን ሁኔታ ከዩኒቨርሲቲ የተባረረው የሐዋሳውን የተማሪው ለዚህ አብነት መጥቀስ ይቻላል።
    በሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ ሲማሩ ከነበሩት አንዱን ባለ ዕድል ከኋላው በመከተል ቁርዓን ቀድዶ ለመጸዳጃነት ተጠቅሟል የሚል ዓመጽ አቀጣጠሉ። ይህን የአክራሪዎች ወጥመድ በጊዜው ማንም አልተገነዘበም ነበር።በቤቱ ወይንም በዶርሙ ምንም ዓይነት ዓረባዊ ጽሑፍ የማግኘት ዕድል የሌለውን አንድ ክርስቲያን መጸዳጃ ቤት ገብተው ሲጠቀምበት ያላዩትን፤በርግጥ የተባለው የተቀደደ የቁርዓን ብጣሽ ሲጠቀምበት ያላዩትን በእርግጥ የተባለው የተቀደደ የቁርዓን ብጣሽ ለዚያ አገልግሎት ውሎ ከሆነ እንኳ ከእርሱ በፊት የተጠቀሙ ሰዎች ይሁን የእርሱ ሳይጣራ ግፊቱን አጧጧፉት።

    ከውስጥና ከውጭ በሚዲያ ለማስተጋባት ተዘጋጅቶ የነበረው የአክራሪ እስልምና ሠራዊት ሁሉ “አሁንም እስላም ይገፋል/ተበድሏል” እያለ ይጮኽ ጀመረ። የአገራችን ሚዲያዎችም ነገሩ በውል ሳያጤኑና በበቂ ሳይረዱ በአክራሪ እስልምናው ወጥመድ ውስጥ ተዘፈቁ።በዚህም ለእነርሱ መብት የሚታገሉ ወይም ክብር የሚሰጡ መሆናቸውን ለመግለጽ ሲጣደፉ በሌሎቹ ፕሮፓጋንዳ ውስጥ ወድቀው የግፍ ተባባሪዎች ሆኑ።

    ከላይ የጠቀስኩት ምሳሌ እውነቱን ለመናገር ሰውየው መጠቀሙን ቀርቶ ከሳሾቹ አክራሪዎቹ ወረቀቱን ከመጸዳጃ ቤት ማምጣታቸውን ለማረጋገጥ እንኳ የጣረ አልነበረም። ጤናማ ኣእምሮ ላለው ሰው መጸዳጃ ቤት ውስጥ ብዙ ሺሕ ተማሪዎች ባሉበት ዩቢቨርሲቲ ውስጥ ቀርቶ በሌላም ቦታ ቢሆን ላይንሳዊ በሆነ መንገድ የአሻራና ሌሎች ምርመራዎች እስካልተካሔዱ ድረስ ማን ምን እንደተጠቀመ ማወቅ አይቻልም። የተከሰሰው ሰው እንደወጣ ስለገባን ነው ቢሉ እንኳ ከእርሱ በፊት ያ ወረቀት ጥቅም ላይ ላለመዋሉ ማረጋገጫ የስፈልጋል። ነገር ግን ሁኔታው ሆነ ተብሎ የተቀነባበረ ስለነበረ በየቦታው አንድ ጊዜ አክራሪው ሁሉ ጮኸ። በዚህ ሚዲያዎችም ሰለባቸው ውስጥ ጣሉት። በእርግጥ ሚዲያው በእነሱ ሰለባ የወደቀው በዚህ ብቻ አልነበረም። ሁለት ነጥብ ሰባት ሚሊዮን ሕዘብ ይኖርባታል በተባለችው አዲስ አበባ ፲፭ በመቶው ፬፻፭ ሺሕ ብቻ የሚሆኑትን ግማሽ ሚሊዮን እንኳን የማይሆኑትን የእስልምና አማኞች ወገኖቻችን አንድ ጊዜ ከ1.5 ሚሊዮን በላይ በማለት በአራት እያባዛ ሌላ ጊዜ ደግሞ ከሁለት ሚሊዮን በላይ በማለት በአምስት እያባዛ ሲናገር እናዳምጣለን። ሚዲያውም ያንኑ በማስተጋባት ዘው ብሎ በመግባት በዚህ ጉዳይ እዚህ ለመዘርዘር የማያስፈልግ ብዙ ትዝብት ላይ የ የሚጥሉ ነገሮችን አሳይቶናል።

    የሐዋሳውን ተማሪ ጉዳይ እና የቁጥራቸውን ጉዳይ እንደ ምሳሌ አነሳነው እንጂ አክራሪዎቹ በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ያስነሧቸው ነውጦችና በአስተዳደርም ላይ የፈጠሯቸው ጫናዎች እጅግ ብዙዎች ናቸው። ሚዲያው ለዚህ ብዙ መጥፎ አስተዋጽኦ አድርጓል። በዚህ ጩሆታቸው እየተገፋፉ ያለ አግባብ ቦታ የሰጡ፤የክርስቲያኖቹን ያሠሩ ያፈናቀሉ ብዙ የወያኔ እስፈጻሚዎችም ነበሩ። ደመራ ሲደመር ወይንም የጥምቀት በዓል ሲከናወን ድንጋይ በመወርወር፤ሆ በማለት ጩኸት ሲያስነሳ፤ሚዲያው ተቀብሎ ወጣቱ አመጽ አስነሳ እያሉ የአክራሪ ሴራ መሆናቸወን ሳያጣሩ ወደ ፖለቲካ ይዘት በመለወጥ ይዘግባሉ። እረ ስንቱ።
    ሦስተኛው ደረጃ፤————–

    አክራሪዎቹ ትንኮሳቸው ግቡን እየመታ ዕቅዳቸው እያሳካ ሲመጣ ደረጃ በደረጃ ቀጠሉበት እንጂ አላቆሙም። በዚህ ጽሑፍ በሦስተኛ ደረጃ ያስቀመጥነው ትንኰሳቸው ገን እጅግ አብዝቶ መረን የለቀቀና የክርስቲያኑንም ትዕግስት በከፍተኛ ደረጃ እየተፈታተነ ያለ ነው።ለዚህ ማሳያ የሚሆን የቅርብ ጊዜ ትንኮሳዎች ጥቂቶቹን እናቅርብ። ይኸኛውን በደንብ ለመረዳት እንዲቻል በአምስት ከፍለን እንመለከተዋለን።

    ፩. የመስጊድ መሥሪያ ቦታዎች፦

    ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ እጅግ ባልተለመደና በሚገርም ሁኔታ የአክራሪዎች ጤናማ ያልሆነ የመስጊድ ግንባታ እንቅስቃሴ ይታያል።”ጤናማ ያልሆነ” የምንለውም ቦታው አምልኮን ለመፈጸም ከመጠቀም ባለፈ ሁኔታ ነገር መፈለግ ስለሚታይበት ነው።ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ አክራሪዎች ለመስጊድ መሥሪያነት የሚጠይቋቸው ቦታዎች ሆነ ብለው ክርስቲያኑን የሚያነሳሣሱ እየሆኑ ነው። አንደኛ የመስቀል ደመራ ቦታዎችን የጥምቀት ባሕር ቦታዎችን፤ከዚያም አልፎ ቤተክርስቲያን ተጠግተው ወይም በዋናው መግቢያ ፊት ለመሥራት ከፍተኛ ጥረት ያደርጋሉ። በደሴ ሀገረ ስብከት ፊት ለፊት ለመሥራት የጠየቁት፤ በጎን ዳር በኣታ ለማርያም ቤተ ክርስትያን ጥምቀተ ባሕር ፊት ለፊት እየሰሩት ያለው በአፋር ዱብቲ በተ ክርስትያኒቱ ፊት ለፊት ለመሥራት የሚደረውን ጥረት እንደ ምሳሌ ለመጥቀስ ይቻላል።

    በአዲስ አበባ የአየር ጤና ኪዳነ ምሕረት ጥምቀተ ባሕርን ክፍሎ ወስዶ የተሠራ ወይንም መስጊድ እና ያደረሰውን ግጭት እዚህ ላይ ይታወሳል።

    ኢሳት የተባለው የግንቦት 7 ማሰራጫ ምነዋ በዚህ ታሪክ መዘገቡ ፈራ እሳ? ይህንንስ ፊልም መስራት አላስፈለጋችሁም?

    ለትንኮሳ ሳሆን ብሎ የሚደረግ መሆኑን የምናውቀው ደግሞ አንዳንዶቹን ለመኖሪያ ወይም ለንግድ ቤትነት ከተቀበሉና ቤቱንም ከሠሩ በኋላ ቀስ ብለው የመስጊድ ምልክት የሆነውን ሾጣጣ ነገር ምልክት ያወጣሉ የጨረቃውንም ምልክት ይሰቅላሉ። ይህን ካደረጉ በኋላ ቦታውን ለጠየቃችሀት አገልግሎት አውሉ ተብለው ሲጠየቁ በተለመደ የነቅተህ ጠብቅ እና የተባብሮ መጮኽ ዘዴ “እስልምና ተደፈረ…” በማለት ባንድ ጊዜ ይጮኻሉ። ሚዲያወም አብሮ ይጨፍራል፤ ጩኸታቸወን በገነነ መልኩ ያስተጋባዋል።

    የህንን በምሳሌ ጠቀስናቸው እንጂ ባለፉት ሃያ ዓመታት የተፈጸሙ (በእስላሙም በወያኔም) የተከናወኑ ትንኮሳዎች እና የአስፈጻሚዎቻቸው ትብብር በርካታዎች ናቸው።

    ሰላማዊ የእስልምና ተከታይ ወንድሞቻችንማ እስካሁን ድረስ መስጊድ ሲሠሩ ኖሮዋል። አገራቸው ነውና ለወደፊትም ይሠራሉ። ይሁን እንጂ “እስላም ተበደለ” የማስደንገጫ እና የማስፈራሪያ ደወል እየደወሉ ጩኾታቸውንም እንደ ገደል ማሚቶ የሚያስተጋቡላቸው ሚዲያዎች እና በዓለም ዓቀፍ ትስስራቸው (ፍንዳሜንታል ኔት ዎርክ)ስልት ሰለባ እየሆኑ ያልተገባ ሥራ መሥራት ግን ሊገታ ይገባል። የአንዱ ውድመት ላንዱ መሆኑን አና ሀገሪቱም የጋራችን መሆኗን መዘንጋት አይገባም።”)
    እነዚህ ሰዎች እስር ይገባቸዋል ወይ? አልወጣኝም፤፡ ነገር ግን እስላማዊ ብሔረተኞች መሆናቸው ግን በኔ ዘንድ ተቀባይነት የላቸውም። አራት ነጥብ!!!!

    ከወስጥ ያሉ የግራይ አህመድ ተከታዮቻቸው እና ኢትዮጵያ 100 አመት ዕድሜ ያላት አገር ናት ባዮች ግን ጀረባቸው የፖለቲካ ገመድ የያዙ መሆናቸው መጠራጥር አልችልም!!!!!
    ጌታቸው ረዳ

Comments are closed.

Share