February 19, 2014
2 mins read

ቴዲ አፍሮ በሱዳን ለመሐመድ ወርዲ በተዘጋጀ የመታሰቢያ ዝግጅት ላይ በአረቢኛ አቀነቀነ

(ዘ-ሐበሻ) “የፍቅር ጉዞ” በሚል በሙዚቃዎቹ ፍቅርን ይሰብካል በሚል የሚወደሰው ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) በሱዳን ካርቱም የፊታችን አርብ ፌብሩዋሪ 21 እና እሁድ ፌብሩዋሪ 23 ሁለት ታላላቅ የሙዚቃ ኮንሰርቶችን እንደሚያቀርብ ከዚህ ቀደም መዘገባችን አይዘነጋም። ቴዲ ለዚህ ኮንሰርት ሱዳን ከገባ በኋላ በካርቱም ለዝነኛው የሱዳን ድምጻዊ መሐመድ ወርዲ በተዘጋጀው የመታሰቢያ በዓል ላይ “ሰበርታ” የተባለውን ተወዳጅ የሱዳን የአረቢኛ ዘፈን በድንቅ ሁኔታ ተጫውቶታል።

ባለቤቱ አምለሰት ሙጬን ከፊት ለፊት አስቀምጦ ለሱዳናውያኑ ያቀነቀነው ቴዲ ከፍተኛ አድናቆትን አግኝቷል። የኢትዮጵያ ሙዚቃዎች በሱዳን በጣም የሚወደዱ ከመሆናቸውም በላይ በተለይ ከ8 ዓመት በፊት ሱዳን የነበረው የዘ-ሐበሻ ዋና አዘጋጅ ሱዳኖች ለቴዎድሮስ ካሳሁን እና ለሃይማኖት ግርማ ልዩ ፍቅር እንደነበራቸው በአይኑ ማየቱን ያስታውሳል። ድምፃዊት ሃይማኖት ግርማ “ዞል ቲቪ” በሚባል የቴሌቭዥን ጣቢያ የፕሮግራም አቅራቢ ሆና እንደነበርም ያስታውሳል።

በካርቱም ቴዲ የፊታችን አርብ እና እሁድ ሥራዎቹን የሚያቀርብ ሲሆን፤ በመሀመድ ወርዲ መታሰቢያ ላይ የተጫወተውን ሰበርታ ሙዚቃ እንጋብዛችሁ፦

Go toTop