በእብደት ላይ እብደት እየጨመሩ ያሉት የአድዋ ልሂቆች – ነጋሪት

የትግሬ ህዝብ መርገምቶቹ መሪዎቹ ናቸው ።የትግሬ ህዝብ በውስጣቸው ሰላምና ልማት እንዳያሠጡለት በተስፋ የላካቸው ግን በተቃራኒው ጦርነት፤ ስቃይና ስደትን ቤቱ ድረስ ጎትተው ያመጡለት መሪዎቹ ናቸው ። ነቅናቂ እያለ ማን ጥሩ ይጠጣል ሆኖበት ነቅናቂዎቹን በጉያው ታቅፎ ውሎ እንዲያድር ያስገደደው የመሪዎቹ ጭፍንነትና አቅመ-ቢስነት ነው። የትግሬ ህዝብ እየወረደበት ያለው ነገር የእርግማኑ መነሻ ከየትም አይደለም ከመሪዎቹ ነው ።

ራዕይ አልባና የህዝቡ እጣ ፈንታ ግድ የማይሰጣቸው ፤ በንፁሃን ዋጋ መነገድ የለመዱ ፤ ቀን ያዘነበለ ጊዜና መሬት ስትገዳው ቂጡን ቆልፎ የሚፈረጥጥ መሪ ስላሉት ነው ። የትግሬ ህዝብ ድህነት በፍፁም ከማንም አካል አልመነጨም ከመሪዎቹ ብቻና ብቻ ነው ።

ለሰይጣን ስልጣን አታሳየው እንዲል አበው ፤ ከተቃዋሚ ፓርቲዎች መሪ ውስጥ አንዱ የሆኑት አቶ ክፍለገብርኤል ገ/ዮሐንስ በማህበራዊ ሚዲያ ከፃፉት ሃሳብ ሲመዘዝ ስለ ትህነግ አመራር እንዲህ ሲል ገልጿቸው ነበር ፦

” … የትግሬ ህዝብ በጠላት ተከቦ እየሞተ ፥ እየተጠመና እየተሰቃየ ነው ።ቸውጩ አልበቃው ብሎት በውስጥም እየታሰረ ፤ እየተገረፈ፤ እየተገፈፈና እየተበዘበዘ ነው ።ይሁንና የትግሬ ህዝብ በውጭና በውስጥ ሰማይ የተደፋበት ህዝብ ሆኗል ። ይሄንን ልናስወግድ እና ልናስተካክል የምንችለው የጋራ መግባባት ፈጥረን ፖለቲካዊ ማስተካከያ ማድረግ ስንችል ብቻ ነው ። ኃያላችንን የሚያፈረጥም ስልት እንከተል ። ውስጣዊ ችግሮቻችን ጠልፎ እንዳይጥለን አቤት ወዴት ተባብለን በመደማመጥ እንሻገር ፤ስርዓትና ህግን እናክብር ። የውጭ ጠላቶቻችንን የምናንበረክክበትን አማራጭ በመሰብሰብ አቅማችንን አሟጠን መጠቀም ስንችል ብቻ ነው ? ይሄንን በመረዳት ነባራዊ ሁኔታው በሚመጥን ፖለቲካዊ ማስተካከያ እንዲደረግ ሁላችንም በጋራ እንታገል ።

ተጨማሪ ያንብቡ:  የደብረማርቆስ ከተማ አስተዳደር ኮምዩኒኬሽን በጎንደር ላይ እየተፈጸመ ያለውን ድርጊት እያየን ዝም አንልም አለ

የትግሬ ህዝብ- በውስጥና በውጭ የችግሩ ምንጭ ምን እንደሆነ ገብቶታል ። ከሰላሳ ዓመታት በላይ በችጋር እና በመከራ ሰረገላ ያሳፈሩት፤ በመቶ ሺህዎች የሚቆጠሩ ወጣቶች መስዋእትነትን ረስተው ፤ በኔትዎርክ በተመረኮዘ የሥልጤን መደላድል የግል ጥቅማቸውን እያሳደዱ መኖር የመረጡት መሪዎቹ ናቸው ።

የትግሬ ህዝብ ምን መዓት ነው የወረደበት?

——

የትግሬ ህዝብ ከሌላው ኢትዮጵያዊ የሚለይበት አንዳች ነገር የለውም ። እንደ ማንኛውም በአካባቢው እንደሚኖሩ ህዝቦች የትግሬ ህዝብም የሚጥር ፤ በሰላም መኖር የሚፈልግ፤ ጨርቃቸውን ጥለው ባበዱ መሪዎቹ ምክንያት ከሃያ ዓመት በላይ በጦርነትና በስቃይ ሲኖር የነበረ ህዝብ ነው ።

የትግሬ ህዝብ ከመሪዎቹ በስተቀር ሌላ መርገምት የለበትም ። የትግሬ ህዝብ አረረም ጣፈጠም፤ እንደ ሌሎቹ አጎራባች ህዝቦች በላቡ ጥሮ ግሮ በልቶ ማደር የማይችል ህዝብ ነው ። ይሁንና በመሪዎች አልታደለም ። ይሄንን ህዝብ የሚታደግና ላከላከል የሚችል አመራር የለውም ።

ጥቅምት 24 በሀገር መከላከያ ሠራዊት ላይ ሠራዊቱ በተኛበት በመኖሪያ ካምፑ ላይ ባደረሱት ጥቃት ጦርነትን የለኮሱት የትህነግ አመራሮች ፤ በስልጣን ጥም በናወዘ አእምሮአቸው ወደ አማራ ክልል ክና ወደ አፋር ክልል ወረራን ለመፈጸም የላኩትን ወጣት ከ300000 ከሦስት መቶ ሺህ በላይ እንደቅጠል እንዲረግፍ አድርገውታል ። በዚህም አልበቃ ብሎ የልጆቹን ደህንነት አመት ሙሉ ሳይጠይቅ ፤ በፕሮፖጋንዳ አሳውረው ዘላቂ መቋጫ ለሌለው ጦርነት ዳግም የእሳት ራት ሊያደርጉት በመቀስቀስ ላይ ይገኛሉ ።

አንዷ በዚህ የፕሮፖጋንዳ ዘመቻ ታቅፈው ለትህነግ በሬ ወለደ ፕሮፖጋንዳ ስትነዛ የነቀረችው ጋዜጠኛ መድህን ገ/ስላሴም ሳትቀር የትህነግን የእውድ ድንብር አካሄድን ከዚህ በሚከተለው መልኩ ገልፃዋለች ።

ተጨማሪ ያንብቡ:  ዛሬ በዲላ ዩኒቨርሲቲ 3 ተማሪዎች በመጸዳጃ ቤት ውስጥ ተገድለው ተገኙ | ተማሪዎች ግቢውን ለቀው እየወጡ ነው

“እኔ የምደግፈውን ካልደገፍክ ፤ እኔ የምናገረውን ካልደገምክ ወየውልህ እያሉ ስር ስርህ እየተከተሉ የእያንዳንዱን ትግሬ ሲያስፈራሩ የሚውሉ አቅመ ቢስ ተላላኪዎች ሞልተዋል ።በአሁኑ ጊዜ ትግሬይ የራሱ ከፍ ሲልም የጌቶቹ ባለሥልጣናት ብቻ ርስት ሆና የምትታየው ሰው መመልከት ራሱ ያሳፍራል ፤ያሳቅቃልም። ወደዳችሁም ጠላችሁም ትገራይ የሁላችን ናት …”

እናስ- የትግሬ ህዝብ እስከመቼ ነው በእነዚህ በሥልጣን በታወሩ መሪዎቹ እየጠፋ እነሱን የሚያኖረው ?

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share