ኢትዮጵያዊነት፣ HR6600ና ወቅታዊ ጉዳዮች – የመፍትሄ ሃሳቦች- ከአባዊርቱ

ይድረስ በቅርብና ርቀት የኢትዮጵያ ጉዳይ የሚከነክናችሁ፣ በአገራችን የውስጥ ትርምስ ስሜታችሁ እንደኔው ለተጎዳው ወገኖቼ – ይቺ አጭር ማሳሰቢያ ድንገት ካሸለባችሁበት እንድታነቃ ታስባ ነውና በፅሞና ተከታተሉኝ።
ባሁኑ ሰአት፣ ለምን አሜሪካ ይህን መሰሪ HR6600 የሚሉትን  ህግ ልትጥልብንና ልታፀድቅ ላይ ታች ትላለች? እንደው ስታስቡት አለ ፕላን የተደረገና በግርግር መሃል እንደተበየነብን ሆኖ እንደማታዩት እገምታለሁ። ከሆነ እሰየው፣ ካልሆነ እስቲ የኔን ግምት ላስቀድም።
፩) ባለፉት ወራት በተለይም ጁንታው የአማራውንና አፋሩን ግዛቶች ከወረረ በሁዋላ ኢትዮጵያዊነት በ ፬ቱም ማእዘናት እየፈነጠቀ  መውጣቱን ፅልመቶቹና ጌቶቻቸው ምቾት አልሰጣቸውም። ስለሆነም ይህን የመስበርያ እቅድ በማስፈለጉ
፪) በትዊተርና በተለይም በዛች ብርቅዬ ሄርሜላ የተጀመረው  የ #NoMore ዘመቻ ከወገን አልፎ በጥቁሩና ሌላው አለም እንደ ሰደድ እሳት በመሳለጡ ጠላቶቻችን እንቅልፍ በማጣታቸው ምክንያትና ኢትዮጵያ በዶር አቢይ አመራር ወደሁዋላ ፊቷን ላትመልስ መቁረጧን በመገንዘባቸው፣
ለ 30 አመታት ያህል ልክ እንደጁንታው ባህሪያችንን ያጠኑት እነ ሱዛን ራይስ የሆነ ስትራቴጂ መንደፍ አስፈለጋቸው። ይህም እንደምገምተው እያቆጠቆጠ ያለውን የኢትዮጵያዊነት ስሜት መግደያ ዋናው መሳርያ እኛን መአት ቦታ ከፋፍሎ ከአቢይ አመራር መነጠል ነው። ለዚህም ከባድ በጀት ለመመደባቸው በግልፅ የሚታይ ነው።
ወገኖቼ ንቁ! እንንቃ!!
ከመቼ ወዲህ ነው አሜሪካ ሆነች አውሮፓ የአማራው ህይወት የገደዳቸው? እነሱዛን በደንብ አጥንተውናል። በ”ደጉ” ጊዜ ጎዝጉዘው ከፅልመት ውላጆች ጋር እየተሳለቁ ፣ ምግባችንንም እየተቃመሱ፣ ሶልዲውንም እየተቀራመቱ አሳምረው የወገንን ባህሪ አጥንተዋል። ለምሳሌ፣ የጁንታው አፈቀላጤ ልቡ የተሰበረ አማራ ይሆንና በ ዖሮሚያ እራሳቸው የሚያስገድሉትን ምስኪን የአማራውና ባለማተብ የዖሮሞ ልጆቻችንን አንገት ያስቀሉና ፣ እሪ ” አቢይ ከሃዲው፣ እነሆ ህዝባችንን አስበላ” ይሉሃል። ያኔ የኔ ቢጤው ይነሳና ” አሁንስ በዛ፣ እውነትም ይህ ሰውዬ ምኑ ይታመናል? አንድ ቀን እንኳ ሃዘን አይደርስ፣ ደንታም የለው ለአማራው ነፍስ ፣ አፋር ባለውለታው ተከዳ” እንላለን ። በርግጥም ድሃው አማራው ሆነ በቅጡ የማይመሰከርለት ዖሮሞው መታረዱ ሃቅ ነው። ታድያ የሚደንቀው ገዳይና አስገዳይ የታወቀው ጁንታና ሎሌዎቹ  ሸኔዎች ሆነው ጎዝጉዘው አስለቃሾችም እነሱው መሆናቸው ነው። የኔ ቢጤው ወይ ሴራውን ለመገንዘብ ልቡ ተደፍኗል አልያም በቁጭትና ሃዘን ልቡ ስለተኮማተረ እነ ሱዛን ቀድመው ወደ አቀዱለት ወጥመድ ዘው ብሎ ይገባላቸዋል። ወደድንም ጠላንም የተፈለገው አለምአቀፉን የወገን ሬዚስታንስ ለማኮላሸት ነው – በትንሹም ትንሽ የተሳካ ይመስላል ። ልብ ብላችሁዋል የ ኖ-ሞሩ ሞቅሞቅ ቀዝቀዝ እንዳለ? ያልተጠበቁ አንቱ የተባሉ አገር ወዳዶች ሸርተት እንዳሉ? ይህ ነው የተፈለገው ወገኖቼ. እንንቃ!!!ለኢትዮጵያችን ስንል ።
አንዱ ወንድም በትዊተር ዛሬ አንድ ወቅታዊ ጥያቄ ስለ ብልፅግና ጠየቀ። በርግጥም ግራ ቀኝ ባየው ዛሬን ላይ ቆሜ፣ ስለእውነት አገሬን የምወድ ከሆነ ከብልፅግና የተሻለ ማን ሊመጣ እንደታሰበ ግራ ይገባል። እንደው የህዝቡ በምርጫ ብልፅግናን መምረጡ ገደል ይግባ ቢባል እንኳ አቢይ ላይ ሌባ ጣቱን የሚቀስር ሁላ ማንን ለኢትዮጵያ  አጭቶላት እንደሆነ ግራ ይገባል። የወያኔን ተለጣፊ ፌዴራሌውን ነው? ልቡ የተሰወረውን ልደቱን ነው? የሚሰራውን ያሳጣውን እስክንድርን ነው ወይስ ማንን ይሆን? ወይስ ስለ ፈጣሪ ሰዎቹ ይመለሱልን ነው?ብቻ የሚገርምና የሚያሳዝን ወቅት ነው።
ምን ይደረግ? መፍትሄዎች!
፩) የወታደሩን ለነ ፊ/ማ ብርሃኑና ጄ/ አበባው ልተውና ወደ ሌላ ጥቆማ እዘልቃለሁ። እነ አጅሬ ለምን እስካሁን እንዳደፈጡ እነሱ ያውቃሉና የቄሳርን ለቄሳር።
፪) ወገን የተባልክ በተለይም አሜሪካ የምንኖር እያንዳንዱን ሴንተር ወጥረን መያዝ የግድ ነው። አደገኛው ረቂቅ ፉርሽ ሆኖ እንዲጨናገፍ ጡንቻችንን የምናሳይበት ወሳኝ ወቅት ነው። አሜሪካኖቹ የውስጥ ችግሮቻችንን እኛን መለያያ ስትራቴጂ አድርገው የሸረቡትን በተባበረ ክንዳችን ፉርሽ ማድረጊያው አሁን ነው
፫) መጪው ሚደተርም ዴሞዎችን አይቀጡ ቅጣት የምናሳርፍባቸው ለመሆኑ ካሁኑ በየቢሮዎቻቸው ማስታወቅ። ስንተባበር የማንደረመስ ጉልበት ነን ወገኖች።
፬) የወያኔዎቹን የመሰናበቻ የመጨረሻውን ጦርነት በቸልታ አለ ማየት ። ህዝቡን ነው የምለው እንጅ መንግስት ምን እንደማሰላቸው መገመት አይከብድም። ካልሰማችሁ የጄ/አበባውን ቃለመጠይቅ አንዴ ሳይሆን ሶስቴ ስሙት። ያን የሰማ ኢትዮጵያዊ በስሜት እየጋለበ አፋርና አማራ ተከዳ አይልም ነበር። ደግሞ ካልተጠበቁ ወገኖች። የፅልመት ውላጆቹን አይደለም የምለው። እነሱማ እንደፈለጋቸው እያማረጡ፣ አንዴ የወለጋ ዖሮሞ፣ ያ አልሆን ሲል ደግሞ ቅልጥ ያሉ ወለዬዎች  ይሆናሉና ምን ችግር አለው። አልቅሰው ያላቅሱናል፣ አስገድለው በቁም ይቀብሩናል። ግን እንዴት አንነቃም? በአገርቤት ያሉትን ህፃናት ሆን ብለው ለ ሰላሳ አመት ስርአት ትምህርቱን ገድለው የልጆቻችንን ማሰቢያ ሰውረውብን ፣ እንዳይጠይቁና እንዳይመራመሩ ተብትበው ከ 14 ክፍላተሃገራት ወደ 86 ንኡሳን ቡድኖች እንደ አሜባ አራብተውን አጨልመውብናል። እኔን የሚያሳዝነኝ በውጭ ያለው የትግራይ ልጅ ይሁን የሌላው እንዴት በእንዲህ አይነት ጥልቀት እነዚህ ሰዎች ጭንቅላታችንን ሊቆጣጠሩ ቻሉ ያስብላል። ለነገሩ በገዛ ገንዘባችን የሸመቷቸው አናሊስቶች፣ የአይምሮ ጠበብቶች ብዙ ስለሆኑ ምንስ ይገርማል ። ትግራዋይ ሆነ ሌላው ለቀን ጉርሱ ሲከንፍ ምንስ ጊዜ አግኝቶ ሊመራመርባቸው ኖሯል። ፈጣሪ ብቻ ይፍረደው።
ዛሬ  ስታሊን ስለተባለው አንጋች ዲ/ዳንኤል ክብረት ያጋለጡትን ሰምቼ አጃኢብ አስብሎኛል። በጤና አይደለም በአብያተ ክርስቲያናት ዙርያ የሱቅ በደረቴ ሱቆች እንደ አሸን የፈሉት። በኛ ዘመን እንኳንስ በተእምነት  ቤት ስር ሱቅ ሊከፈትና ሊገበያዩበት በአካባቢውም ለእይታ አይኖርም ነበር። ይህን ስሰማ የከንቲባዋ አበሳና ፍጥጫ ታየኝና ከልብ አዘንኩ። ለነገሩ ሰዎቹ ደስ የሚለው ከ አርባ አመታት በፊት ገና ጫካ እያሉ ኦርቶዶክስ ላይ ክንዳቸውን እንደሚያሳርፉ ነግረውን ነበርና ምንስ ይገርማል ።
፫) የእንገነጠላለን ቀረርቶ
አንድ የማልንቀው የነዚህን ሰዎች ጉዳይ፣ እያንዳንዱን የኢትዮጵያዊ ሃሳብ ያውቃሉ። ለዚህም ነው ከየኪሳቸው እያወለቁ አጀንዳ የሚያቀብሉን። እንደማይሆንላቸው ያውቁታል፣ ሆኖም በስሜት ክፉኛ የተወጣጠርን መሆኑን ስለሚያውቁት ለምሳሌ እንዲህ ይላሉ፣
ወልቃይትን እናስመልሳለን
አድዋ የኛ ነው
ሲሉ በዖሮሚያ የሚያስቀነጥሱትን የአማራውና ዖሮሞው ደም ደመከልብ ሆኖ እንዲቀር አጀንዳ ማስቀየሻና ህዝብና መንግስትን ለመለያየት የታለመች ታክቲክ መሆኗ ነው። እስቲ በምን ተአምር ወልቃይትን ያስመልሳሉ መቀሌ ተሸሽገው? ይቺ በየጉድጓዱ የደበቋት አስቤዛ እየተጣራች መሆኗን ስላወቁና መጪውን ክረምት እንደማታዛልቅ ስለተረዱ እንደ እብደትም እያረጋቸው ቢሆን እንጅ አድዋን ምናልባት በታሪክ አጋጣሚ በአካባቢው ከመወለድ ሌላ ለአድዋና ኢትዮጵያ የሞተው እንኳ የመሃል አገር ህዝቡ ነው። እኛም የኛ ነው አላልን የጀግኖቹና የሰመአታት ትውልድ። የአድዋን ስም ከሃዲ ሲጠራው ይወረኛልና ነው እንጅ ለሌላ አልነበረም።
ማጠቃለያ!
አገራችን ከምንጊዜውም የበለጠ የሁላችን ርብርብን ስለምትፈልግ በትጋት እንስራ። ከአቢይ ቁርሾ ያላችሁ፣ ወይም አካሄዱን ያልተረዳችሁ፣ ስለ እናት አገር ብላችሁ የሚሰራብንን ደባ ለመረዳት አይናችሁንና ልባችሁን ክፈቱ። ኢትዮጵያን ካስቀደማችሁ የግለሰቦች ሚና ኢምንት ይሆናልና። የችኮላ ሃሳብ ስለሆነ እያረማችሁ አንብቡት። ለራሴውም ይሆናል የፃፍኩት። አገራችንን ሰላም ያርግልን።
ተጨማሪ ያንብቡ:  መኢአድና አንድነት ውህደታቸውን ለማራዘም መገደዳቸውን ገለፁ

4 Comments

 1. አሜሪካ የሚባል አገር በሰው አገር ገብቶ ባስቸኳይ ትግሉን ስልጣን ላይ መልሱ፣ስብሀት ነጋን ፍቱ አረ ግፉ በዛ አምላክ ፍርዱን ይስጠን እኛ አቅም አጥተናል።

 2. የአብይ እፈቀላጤና ባለሞል አባዊርቱ እፈረተቢስ ህሊናቢስ ነውርኝነትን ችላ ብለው እይናቸውን ጋርደው ጆሮእቸውን ደፍነው እእምሮእቸውን በፍርፋሪም ይሁን በኦሮሙማ የዘውግ ቅዥት ለዜውም ቢሆን ስክረው የምናየውን የምንስማውን የምናስተውለውን ንፁህ ኢትዮጵያውያንን እብይን እንድንደግፍላቸው እኛም እንድ እርሳቸው ልበስውራን እእምሮቢስ አለመሆናችን ያስተውላሉ ብሎ ማስብ የዋህነት ነው::
  እብይና ወያኔ በዘር ፕለቲካ እንድ የሆኑ ልዩነታቸው አገሪቱን ሃብት ለመዝረፍ የስልጣን ባለቤትነት ጉዳይ ብቻ ነው ::ህውሃት የመስረተው የዘር ፕለቲካ ከሌለ አብይ ወይም ኦሆድድ አይኖርም !ስለዚህም እብይ
  1; ከህውሃት ጋር የሚደረገው ጦርነት ህውሃት እንዲቆይ እንጅ ጨርስ እንዲጠፋ እይፈልግም
  2:ህውሃት አማራም ሆነ አፋር ኢትዮጵያው መንፈስና ጥንካሬ ያለው በመሆኑ በህውሃት እንዲጨፈጨፍ ትልቅ ሴራ ከህውሃት ጋር በመናበብ እየስሩ ጦርነቱን ከትግራይ ክልል አውጥተው አማራና አፋር ላይ እድርገው ክልሉን በኢኮኖሚና በስው ሃል በስነልቦና ቀውስ እንዲጋባ እያደረገ ነው
  3;በኦሮምያ ክልል የአማራን ዝር ከክልሉ ለማጥፋት በይፋ እራሳቸው ሽኔ ብለው ስም ስጥተው በይፋብጦር እያስለጠኑና ዘመናዊ መሳርያ እያስታጠቁ ነው!ልብ ይበል ትላብትና ከእስመራ ሆን ተብሎ ከን ትጥቁ ተፈቅዶለት የገባው የኦነግ ጦር ከ200 የማይበልጥ ነበር!ይህ ጦር በእደባባ ከልክይ ሳይኖረው ባንክ እየዘረፈ ራሱን እንዲያደራጅእስመሳዩ እብይ እገዛ ያደርጉ ነበር
  3;በኦሮምያ ክልል እማራን ከክልሉ ከንብረቱ እያፈናቀል ሲያሳርዱት ሲያሳድዱት የእብይመንግስት ይ ሁሉ የኦሮምያ ልዩ ሃይል ስራዊት ኦሮሞኦሮሞን እይገል ም በሚል ህሳቤ በጭራሽ እይነኩትም ነበር ይልቁንስ በመሳርያና በገንዘብ በተሽካርካሪ መኪና ጭምር ርዳታ ያስደርጉለት ነበር እንደ ቀይመስቀል የመስሉ መኪናዎችን በማዘረፍ
  4:በየትኛውም ግዜ ኦነግ እነደ እብይ መንግስት ዝመን እጅግ የተስፋፋበት በመሳርያበተሽከርካሪ በገንዘብ ጭምር በሚቆጣጠረውምእስከ ሽዋ ድረስ (እጣይከተማ ልብይሏል)የተቆጣጠረብት አማራ እንደ እንሰሳ ይታረደበት ዘመን ቢኖር የእብይ መንግስ ነብር
  4: አብይ በኦሮምያ ክልል በአማራላይ የሚደረገውን ዝር ማጥፋት እንድም ግዜ ይቅርታሆነ ማስተባበያ የስጠበት ህዜ የለም
  6:ኢትዮጵያ በታሪኩዋ እንደ እብይ መንግስት ዘመን ጨርሶ ሃይማኖት ባለበት ሀገር ጨርሶ በስውልጅ ላይ እጅግ ዘግናኝ ኢስብአዊ ጭካኔና ስቃይ በተለይም አማራ እዲሁም እፉር ህዝብ ላይ ደርሶ እያውቅም! እንዲዚህ እይነት ውሸታም እስመሳይ ደላላ ህሊና ቢስ መሪ ገጥሞአት እትውቅምን!ልብ ይበሉ የስላም ሚንስቴር ተብሎ በተሾመበት ባለበት ሀገር!ለ ምንእንዲስሩ እንደተቆቆሙ እይታወቅም
  ወንድሞቼና እህቶቼ የአብይ ባለሞል ካድሬ ያለእፍረት የእብይን ጥንካሬየልማትመሪ እድርገው ሊስብኩለት ይዳዳቸዋል!!የስውልጅ የመኖር መብትና ደህንነት በሌለበት ህግም የመንግስት ማፈኛተቋም በሆነበት ልማትና እባይግድብ ስለአዲስአበባ መናፈሻና ችግጭ ቢዋሩን ጥንቅር ብሎ ይቅር!ስላምበሌለበት በስከንድ ፈራሽ ሊሆንንየሚችል ነው
  አባዊርት ልነግርህ የምወደው መሽቶ እይቀርም ይነጌል!ሁሉም ታሪክ ሆኖ ለሚቀረውብትውልድ ምጥፎ አንገት እስደፊብታሪክ ሆኖይቀርል! ዝመን የቴክኖሎጅ ዘመን ነው ሁሉን ታሪክ በመረጃ ይዘግበዋል!እግዚእብሔርም ሁሉንን ያያልንይፈርዳልም!እናም ወንድሜ እባዊርቱ ዓይንህን እጥርተህ ጄሮህን ከፍተህ በማስተዋል በቅንልቡና በፍፁም ፍርህያ እግዚእብሔር ነገሮችን ብትመዝን መልካም ነው
  እናንተም የዘሃበሻ እምድእዘጋጅች እግዚእብሔር ረጅም ዕድሜና ጤና ስራችሁንምይባርክ!
  ለገላፍቶ ነኝ!

 3. ዮሀንስ ልክ ብለሀል አባዊርቱ ለዚህ መልስ ያላቸው አይመስለኝም ።ስላለው ሁኔታ ካንተ በላይ ያውቃሉ ነገር ግን ምክክር እያሉ አልፎ አልፎ እንዲህ ያለ መልእክት ይልካሉ። ጦጣ ፊቷን ስትሸፍን መላ አከላቷን የሸፈነች ይመስላታል የሚል ምሳሌ አለ። በወለጋ፣ባሩሲ፣በሻሸመኔ የሚታረደው የትላንት ወንድማቸው ለሳቸው ምንም አይደለም ለሳቸው ዋናው ኦሮሙማ በታሰበው ፕሮግራም መካሄዱ ነው። ቀደም ሲል ኢትዮጵያ ይሉ ነበር ዛሬ ላይ አብይ አብይ ነው። በኔ በኩል መልካም ጤና እና እድሜ እመኝላቸዋለሁ የኢትዮጵያን ትንሳኤ ዳግም እንዲያዩ ይሄ ጊዜ አልፎ እሳቸው ደግሞ ይሄ ጊዜ ከሚያልፍ እኔ ልለፍ ባይ መሰሉኝ።

 4. ለገላፍቶ ሆይ! ሲጀምር ንዴትና ስድብ የተሸናፊነት ምልክት ነው፣ ሆኖም እኔ እዚህ ለቅልቀው እንደሚጠፉት ሰዎች ሳልሆን ሃሳብዎትን ብቻ ለመሞገት እሞክራለሁ። እንግዲህ ድንገት የተቆጨና ሃቀኛ ወገን ከሆኑ እንጅ የፅልመት አንጋች ሊሆኑም ይችላሉ። ለምን? ከላይ ዮሃንስ ብሎ ከታች “ለገላፍቶን” የሚቀላቅሉ ያው እነሱው ይሆናሉ ከሚል እሳቤ ነው። ለማንኛውም፣

  1; ከህውሃት ጋር የሚደረገው ጦርነት ህውሃት እንዲቆይ እንጅ ጨርስ እንዲጠፋ እይፈልግም ላሉት

  አባዊርቱ
  አሳማኝ አይደለም። ለምን? ምን ይጠቅመዋል?ጦርነትና ልማት ሲደጋገፉ ሰምቼም አላውቅም ብዙም ኑሬአለሁ።ከልምድና ክህሎት የማቀውም ይህን የሚያስብ አይምሮ የታመመ ብቻ ነው እንጅ እንዴት ጦርነትና ልማት ይወራረሳል?

  2:ህውሃት አማራም ሆነ አፋር ኢትዮጵያው መንፈስና ጥንካሬ ያለው በመሆኑ በህውሃት እንዲጨፈጨፍ ትልቅ ሴራ ከህውሃት ጋር በመናበብ እየስሩ ጦርነቱን ከትግራይ ክልል አውጥተው አማራና አፋር ላይ እድርገው ክልሉን በኢኮኖሚና በስው ሃል በስነልቦና ቀውስ እንዲጋባ እያደረገ ነው

  አባዊርቱ

  አዎ ፣ ህውሃትማ ምኞቷና ተግባሩዋም ይህው ነው። አቢይን ማለትዎ ከሆነ ግን አሁንም አሳማኝ አይመስለኝም። ለምን? አፋርና አማራ እንዳሉትም የኢትይጵያዊነት ችካል ከሆኑ እንደምን አድርጎ ዶር አቢይ ይህን ከባድ ችካል ሊነቅል ይችላል? በርስዎ ፅልመታዊ አስተያይ እውነት እንዲህ አቅዶ ከሆነ እነሆ ታየ አይደለም እንዴ እንዴት አደርጎ የአማራው ገበሬ እርፉን አስቀምጦ በወኔ ቢቻ ምድረ የፅልመት ሰራዊትን እግሬ አውጭኝ አስብሎ ከክልሉ ጠራርጎ ያወጣው?/የምድር ለምድር ድሮን የተባሉት የአፋር አይበገሬዎች ይህው ከፊትና ጀርባ እየቆሉት አይደል እንዴ? እንግዲህ አቢይ አህመድ እነዚህን ሁለት የጀግኖች መፍለቂያ ለህውሃት ገብሮ ነው አባይን የሚያክል ተሃድሶና አገራዊ ልማት ለሚቀጥሉት ብዙ አመታት የሚያልመው ይበሉኛ? ይህ ማለት ከወገበ በታች በድን የሆነ አካልን ይዞ በእግር ሩጫ ለኦለምፒክ እንደመወዳደር ይሆንብኛል። ልብ ይበሉ የአካለስንኩላን ኦሎምፒክም አለ፣ ሆኖም አቢይ አህመድ በጋሪ ሳይሆን በእግር ወይም በፈረስ ጉግስ አይነት ኦሎምፒክ እያሳተፈን መሆኑን ለመግለፅ ያህል ነው!

  3;በኦሮምያ ክልል የአማራን ዝር ከክልሉ ለማጥፋት በይፋ እራሳቸው ሽኔ ብለው ስም ስጥተው በይፋብጦር እያስለጠኑና ዘመናዊ መሳርያ እያስታጠቁ ነው!ልብ ይበል ትላብትና ከእስመራ ሆን ተብሎ ከን ትጥቁ ተፈቅዶለት የገባው የኦነግ ጦር ከ200 የማይበልጥ ነበር!ይህ ጦር በእደባባ ከልክይ ሳይኖረው ባንክ እየዘረፈ ራሱን እንዲያደራጅእስመሳዩ እብይ እገዛ ያደርጉ ነበር፣
  አባዊርቱ
  በዖሮምያ ክልል የሚያልቁት አማራ ሆኑ ዖሮሞ ወገኖቻችን የሚያልቁበቱ ዋነኛው ምክንያት ሆዳም የዖሮሞ ልጆችና በዖሮሞ ምድር ለ አርባ አመታት እንደ አሜባ ሲራቡ የኖሩት የፅልመት ጡረተኞች ናቸው። እነዚህ ለሰው ልጅ ነፍስ ደንታቢሶች፣ ሀ ብትላቸው ለን የማይደግሙ አይምሯቸው አርቆ አገራዊ ራእይ የሌላቸው፣ በሶልዲ ሶላቸውን የሸጡ መሸጦዎች ናቸው። ትዝ ይለኛል ዖነግ ሲገባ ካልጠፋ ኬላ እንዴት ከነአቦይ ስብሃት ቡራኬ ተቀብሎ ያልፋል ብዬ እዚሁ ሳተናው ይሁን ዘሃበሻ ቤት ስቃጠልበት እንደነበረ። አንድ አባጫላ የሚሉት ዖሮሚፋን እየተቀኘ ልቤን ሲያማልል የነበረ ወያኔ (ሁዋላ እንደነቃሁበት) ሃሰት ነው ብሎ ሲከራከረኝ ነበር። ቁምነገሩ በዖሮሚያ እየሆነ ያለው ግፍ የ ሰላሳ አመታት የወያኔ ክፉ ስራ ውጤት ነው። የ፫ አመት በፊቱን ባንኮች ይሁኑ የዘንድሮው ንፁሃን ነፍስ ሲያወድሙ አገሪቱ ምንም ደጀን ኢትዮጵያን የሚሸት ፖሊስ ይሁን ጦር ሰራዊት እንደሌለን ስለምታውቁት ነው። የውስጥና የውጭውን ገበናችንን በደንብ ስለምታውቁት ከናንተ ጋር በንዋይ ፍቅር ከንፈው ወገናቸውን የካዱ የነ ኦቦ ዳውድና ጀሌዎቻቸው አይነቶቹ ስለተባበሯችሁ አዎ መአት ነፍሰገዳይ እንደ ደህና ምርት አድርሳችሁዋል። በሰራዊቱ ሆነ በልዩ ሃይሉ ለሆድ ያደሩ ብዙ ስላሉም የአቢይ፣ ታዬና ሌሎች ፍፁም ኢትዮጵያዊ የዖሮሞ ልጆችን ከህዝቡ ለመነጠል ስትሉና ህዝቡን ለማሸፈት የማታደርጉት የለም – ሆኖም ከሸፈባችሁ። ይህን የሰይጣን ስራ ስትሰሩ አቢይማ ምስጢሩ ገብቶት ኢትዮጵያን የሚሸት አርሚና መከላከያውን ሀ ብሎ ምስረታ ጀመረ። ፈጣሪም አሳካለትና እነሆ በዚሁ መከላከያ አመራርና ፈጣሪ ቸርነት፣ የህዝባችንም ቆራጥነት ኢትዮጵያ ከሞት እየተነሳች ነው።

  3;በኦሮምያ ክልል እማራን ከክልሉ ከንብረቱ እያፈናቀል ሲያሳርዱት ሲያሳድዱት የእብይመንግስት ይ ሁሉ የኦሮምያ ልዩ ሃይል ስራዊት ኦሮሞኦሮሞን እይገል ም በሚል ህሳቤ በጭራሽ እይነኩትም ነበር ይልቁንስ በመሳርያና በገንዘብ በተሽካርካሪ መኪና ጭምር ርዳታ ያስደርጉለት ነበር እንደ ቀይመስቀል የመስሉ መኪናዎችን በማዘረፍ

  አባዊርቱ
  ዖሮሞ ዖሮሞን አይገልም ያሉበት እሳቤ የዖሮሞን ህዝብ በተለያየ ፅንፍ የወጣጠሩትን ግለሰቦች፣ ወይም ድርጅቶች ወደ አንድ ማእድ ለማቅረብና ለመደመር ከተመኙት እሳቤ (ትዝ ይለኛል ኦቦ ዳውድ በቪኦኤ ድረስ ቀርበው መንግስትን ሲያስፈራሩ)እንጅ እርስዎ በመጥፎ መንፈስ እንደተመኙት አማራውን ሆነ ዖሮሞውን ወገን አንገቱ በሸኔ እንዲቀላ ተመኝተው አልነበረም። ይህንን በደንብ ታውቁታላችሁ፣ ሆኖም ብዙ ከላይ ላይ ሲያዩት የሚመስል ነገር ሲከፍቱት ግን እንደ ወያኔ ክህሎትና ትምህርት እጅግ የወረደ አተያይ ነው። አንዳንዴ ሳስበው የአቢይን ዝምታ ፣ ከዝምታው በላይ ምን ቢሉስ በአይን ግድያው እየታየ ምንስ ብለው ዲፌንድ ያደርጉታል?ለዲፌንስ እንዳይመች እኮ ነው በቁም የቀበራችሁን። ሊተራሪም በቁም ቀብራችሁን መች አበቃ? ኤኔትሬም በላያችን ነዳችሁም እኮ። እናንተ ወያኔዎች ትምህርት ሳይሆን ወይም ክህሎት ሳይሆን ለ 30 አመታት ያዳበራችሁት እንዴት አድርገን እንደምስጥ ህዝብ ውስጥ ገብተን በተለይም እንዴት አድርገን ሁለቱን አማራና ዖሮሞውን – እንዳላችሁትም – እሳትና ጭድ እናደርጋለን በሚል እሳቤ እንደ ብቅል ያሰጣችሁትን 86 ብሄርብሄረሰቦች አስጥታችሁ ስታጠኑን ነበር። ለብዙ ጊዜ ትምህርቱ ሰምሮላችሁ እርስ በርስ አጨራርሳችሁን ነበር ዛሬ እንደዚህ ጎማችሁ ሊፈነዳ። የተጋመድንበቱ ገመድ ግን እጅግ ጥብቅ በመሆኑ እንደሩዋንዳው ምን ብትመኙ አልሰመረላችሁም የማይተናነስ ግን ቀንቷችሁዋል።

  4:በየትኛውም ግዜ ኦነግ እነደ እብይ መንግስት ዝመን እጅግ የተስፋፋበት በመሳርያበተሽከርካሪ በገንዘብ ጭምር በሚቆጣጠረውምእስከ ሽዋ ድረስ (እጣይከተማ ልብይሏል)የተቆጣጠረብት አማራ እንደ እንሰሳ ይታረደበት ዘመን ቢኖር የእብይ መንግስ ነብር

  አባዊርቱ
  ይህን የምንሰማው ከናንተው ሲሆን ያማል እንጅ ትክክል ነው ይህ። እናንተ ስል ወያኔዎችና ኮተቶችን ማለቴ ነው። አማራው እንደ እንሰሳ የታረደው እናንተው ለ 50 አመታት በፈረደበት አማራው ወገናችን ላይ ስትዶልቱ፣ በቀጥታም፣ በአዋጅም በቤተእመነቶችና ትቤቶች ጥላቻው ዘልቆ እንዲገባ በማድረጋችሁ ነው። ለዚህም ነው ወጣት፣ አገናዛቢ አይምሮ ይኖራቸዋል በውጭም ሰለጠነው እየኖሩ ይህ አይጠፋቸውም ያልናቸው ሁሉ በጥላቻ ተሰውረው ዛር እንዳለበት የኢትዮጵያ ስም ሲነሳ የሚያደርጋቸው። በተለይም በእርግጥም የአማራው ወገናችን ላይ እጅግ ያስጓራችሁዋል። በልጅነት እድሜዬ የአማራውን ግዛትና የህዝቡን ፍቅርነት አይቼዋለሁ። ህዝባችን ሁሉም ጎሳ ፍቅር ነው። ፍቅሩን ያጠፋው የወያኔን ትምህርት ቁምነገር አድርጎ ተማርኩ ባዩ እራቀቃለሁ ብሎ የኢትዮጵያችንን ባለ ፫ ጥለት ሸማ አሽቀንጥሮ ጥሎ የየጎሳውን ጥብቆ ያጠለቀ ለታ ነው። የሞተውም ያኔ ነው። ለማንኛውም ዖነግ አይደለም የተስፋፋው። ከሸኔ ጋር አያማቱብኝ። ዖነግማ ዳይት አድርጎ ፣ ሸንቅጦ ፣ እነ ኦቦ ዳውድን አሽቀንጥሮና እነ ኦቦ ኢብሣ ነገዎና ቀጄላ መርዳሣን ወደ መደመር ማእድ አቅርቦ ተስተካክሎ የለም እንዴ? በከንቱ አይድከሙ። በበኩሌ ከልጅነት እስከ እውቀት ሰውን ከሚበልት ወገን አልወጣሁም። የናንተውና የቅጥረኞቻችሁ ሸኔዎች የስራ ውጤት ናት። ሸኔን የማየው ልክ እንደነ ቦኮሃራም ወይም ለአላማ ሳይሆን ለ ንዋይ እንዳደሩ ቅጥረኞች ነው። በነገራችን ላይ በ 30 አመታት ውስጥ በርግጥ ኦነግን እንደሌሎች ተቃዋሚዎች በክብር ተፈቅዶላቸው አጋጣሚውን ለወገን ግንባታ እንዲያውሉት መመቻቸቱ እርግጥ ነው። አቢይ ይህን ሲያደርግ በራሱ ላይ ተንኮልና በህዝባችን ላይ መከራን ያመጣሉ ብሎ ነው ብለው እባክዎ አያሳቅቁኝ።

  4: አብይ በኦሮምያ ክልል በአማራላይ የሚደረገውን ዝር ማጥፋት እንድም ግዜ ይቅርታሆነ ማስተባበያ የስጠበት ህዜ የለም

  አባዊርቱ
  ምን ጊዜስ አገኘና ፣ በምንስ አንጀቱ? የናንተው ሆምዎርክ ብዛቱ። የምታቀጣጥሉት የእሳት አይነት ድምቀቱ። ሰውዬው ትንፋሹን ለመሰብሰብም መች በለስ ቀንቶት እንኳንስ የአማራውን እዝን ሊደርስ። እናንተም ይቺን በደንብ ስለምታውቁና ህዝባችንም በዚህ መከራ ጊዜ ልቡ ስለተሰባበረ ቢያምናችሁ ምን ይገርማል? አሁንማ ይፋ ወጥቷልና ልናገረው። ህዝባችን እስካሁንም በደንብ የተረዳ አይመስለኝም የ 45ቱን ሺህ ሰራዊት። በየመንግስት መስራቤት ይሁን ግል ድርጅቶች ፣ ከቀበሌ እስከ ክከተማና ክፍለሃገር፣ ጠቅላላውን የአገሪቱን ደም ስር ወጣጥራችሁ ምን ጊዜ ደልቶት እዝን ይድረስ? እሳት እየለኮሳችሁ ቢዚ አድርጋችሁት። እድሜውና ወኔው እንዲሁም ውትድርናው ረድቶት ነው እንጅ ይህ ሰው ቆሞ መሄዱ እራሱ አጃኢብ ያሰኛል። ከተሸከመው ሸክም አንፃር። ደግሞስ የክልሉ አስተዳዳሪ እያለ ለምንስ አቢይ በዚህ ይጠይቅ ለፈጣሪ ፍርድ? ሺመልስም የአቢይ አይነት ችግር ካለባቸው ካልሆነ በርግጥም እኔም ቅር ብሎኛል። ለዚህም ነው ከንቲባ አዳነችን ያጨሁት። ሴቶቻችን ከጥንትም ብልሆችና ቆራጦች ናቸው።

  6:ኢትዮጵያ በታሪኩዋ እንደ እብይ መንግስት ዘመን ጨርሶ ሃይማኖት ባለበት ሀገር ጨርሶ በስውልጅ ላይ እጅግ ዘግናኝ ኢስብአዊ ጭካኔና ስቃይ በተለይም አማራ እዲሁም እፉር ህዝብ ላይ ደርሶ እያውቅም! እንዲዚህ እይነት ውሸታም እስመሳይ ደላላ ህሊና ቢስ መሪ ገጥሞአት እትውቅምን!ልብ ይበሉ የስላም ሚንስቴር ተብሎ በተሾመበት ባለበት ሀገር!ለ ምንእንዲስሩ እንደተቆቆሙ እይታወቅም

  አባዊርቱ
  ድንቄም ሃይማኖት አስብሎኛል እባክዎ ስታሊን የጠቅላይ ኦርቶዶክስ ወጣቶች መሪ ሆኖ ጃፓን ስብሰባ ሄዶ ነበር ማለትን ሰምቼ። የዬትኛውን እንዲህ የሚያኮራ በሁለቱም ቤተ እምነቶች ጓዳ የ 30 አመታት የስራ ፍሬ አይተን ነው? በየበተስካኑ ዙርያ ባስፋፋችሁት ንግድ ወይስ በመሪዎቹ የተንደላቀቀ ኑሮ? ወይስ በውጭው አለም የሚቸበቸቡትን ቅርሶቻችን? ባያናግሩኝ ይሻላል በዚህ ሴንሲቲቭ ጉዳይ። ሃይማኖቶቻችን የተረፉት በምእመኑ ፍፁም አማኒነት እንጅ በመዋቅሩ ጥንካሬ ከመሰሎት ተሳስተዋል። በተረፈ ዘግናኙና ኢሰባዊ ጭካኔውማ በወያኔና አጋፋሪዎቻቸው እንጅ አቢይማ ጦር አውድማ ውሎ ድራሻቸውን ማጥፋቱን ነው የማውቀው። ምንድነው የሚያወሩት? ሰላም ሰላምን ለሚሹ ይሉ ነበር አንድ ጥንት የብእር ሰው። እናም የሰላም ሚኒስቴር ስራው ያልታወቀው ሰላም ስለሌለ ይመስለኛል። የሰላም ሚኒስቴር መ/ቤት በመፈጠሩ ብቻ ሰላም አይመጣም ፣ ሰላምን የሚሹ ዜጎች ሲበራከቱ ነው። ይህው ነው!

  ወንድሞቼና እህቶቼ የአብይ ባለሞል ካድሬ ያለእፍረት የእብይን ጥንካሬየልማትመሪ እድርገው ሊስብኩለት ይዳዳቸዋል!!የስውልጅ የመኖር መብትና ደህንነት በሌለበት ህግም የመንግስት ማፈኛተቋም በሆነበት ልማትና እባይግድብ ስለአዲስአበባ መናፈሻና ችግጭ ቢዋሩን ጥንቅር ብሎ ይቅር!ስላምበሌለበት በስከንድ ፈራሽ ሊሆንንየሚችል ነው

  አባዊርቱ ፣ (የማልመለስበት የመጨረሻ)
  ወንድሜ፣ እንኳንስ ካድሬ ልሆን የካድሬ ቃል አልነበረም ከአገሬ ስለይ። ባይሆን የኢትዮጵያ ባለሙሉ ስልጣን እንደራሴ ቢሉኝ ወይም በጥንቱ አዋጊ ስሜ፣ ያየርባየር ተምዘግዛጊ ኤታማዦር ቢሉኝ ደስ ይለኛል ። ይህን ሁሉ ሀተታ ጊዜ ወስጄ የምመልስሎት አፃፃፍዎ ደረጃውን የጠበቀ ሆኖ አግኝቼው እንዳልሆነ ቢረዳኝም ድንገት ስሜታቸው የተጎዳ ቅን ዜጋ ግን በጣም የተናደዱ ሰው ስለመሰሉኝና በከንቱ ስለከሰሱኝም ጭምር ነው። የለየለት ሸኔ/ወያኔም ከሆኑ ሁላችንም በስሜት የማንነዳ፣ የናንተን የባረቀበት ክህሎት ከሩቁ ማሽተት የምንችል ሰዎችም እንዳለንና እንድንማማርበትም ጭምር ነው። በጣም ከርስዎ የምስማማው ግን በኒህ ዘሃበሻ ቤት የሚያስተናግዱንን ድንቅ ኢትዮጵያውያን አለማድነቅ ውለታቢስነት ነው።
  በተረፈ እኔ ለጥፌ የምሸሽ ሳልሆን ተመላልሼ የማስተነፍስ መሆኑን ነው። በዚህ አጀንዳ ስር ግን በቃኝ ለጊዜው። ገለቶማ!

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share