የአማራ ወጣት ቅድምያ መከላከያን ተቀላቀል!! = ቹቹ አለባቸው

Chuchu 1የአማራ ህዝብ በደረሰበት ዉጫዊና ዉስጣዊ(በራሳችን ችግር) ምክንያት በመከላከያ ዉስጥ ያለዉ ተሳትፎ በሚገባዉ ልክ መሆኑ ቀርቶ ጭራ ሆኖ ቆይቷል። የዚህን ዉጤት ምን እንደሆነ ደግሞ በተለይም ይህ ጦርነት ቁልጭ አድርጎ አሳይቶናል።
መደማመጡ ይሻለናል!መደማመጥ ባለመቻላችን እስከዛሬ ብዙ ዋጋ ከፍለናል። መቸም በአማራ ፖለቲካ ዉስጥ መደማመጥ አለመቻላችን ብዙ ዋጋ እንዳስከፈለን ቢያንስ ልብ ያለዉ ልብ ይለዋል። የአማራ ፖለቲካ መደማመጥ ቢዋጀዉ ኖሮ አይደለም የአማራን ችግር መፍታት ለሀገር ብሎም ለምስራቅ አፍሪካ በተረፈ ነበር፤ነገር ግን ምን ያደርጋል መደማመጥ የለ!
መደማመጥና መከባበር አይደለም በቀዉስ ወቅት በአዘቦት ጊዜም ጥቅም እንጅ ጉዳት የለዉም። መደማመጥና በጋራ መትመም ሲኖር ምን አይነት ጣፋጭ ድል ሊገኝ እንደሚችል የሰሞኑ ድሎቻችን ጥሩ ማሳያወቻችን ናቸዉ።
ይሁን እንጅ አሁንም ቢሆን በግልፅም ሆነ ዉስጥ ለዉስጥ የሚሰሩና የአማራን መከራ ሊያራዝሙ የሚችሉ ሀሳቦች አለ። ለምሳሌ የተጀመረዉ የመከላከያ ምልመላ እንዳይሳካ ዉስጥ ለዉስጥ የሚሰሩ ወገኖች አሉ(በዉስጥ መስመር የላኩልኝ አሉ)። እነዚህ ወገኖች አማራ በመከላከያ ዉስጥ ተገቢዉን ዉክልና እንዳይኖረዉ የማድረግ ፍላጎት አላቸዉ። አንዳንድ የዋሆች ደግሞ አማራ መከላከያ ሳይሆን ልዩ ሀይሉን ብቻ ይቀላቀል ይላሉ። ለነዚህ ወገኖች ሊታዘንላቸዉ ካልሆነ በስተቀር ሊታዘንባቸዉ አይገባም፣ምክንያቱም ግራና ቀኙን ማገናዘብ የመቻል አቅም ገና አላዳበሩምና።
ሌላዉና አሳዛኙ ነገር አማራ ራሱን ማደራጀት ያለበት በህዝባዊ ሰራዊት (ፋኖ መሆኑ ነዉ) እንጅ በመከላከያ መሆን የለበትም የሚሉ እስስቶችም አሉ። አሁን እነዚህን ወገኖች ምን ማለት ይቻላል? አይጣል ነዉ።
በአጠቃላይ አንዳንድ ወገኖች/ቡድኖች እነዚህንና መሰል እንቅፋቶችን እያነሱ የአማራ ወጣት በገፍ ወደ መከላከያ እንዳይገባ ጥረት የሚያደርጉ አሸክቶች እንዳሉ መገንዘብ ያስፈልጋል። እነዚህ ወገኖች ዛሬም ላይ አማራን በመከላከያ ዉስጥ በቁመናዉ ልክ እንዳይወከል እየሰሩ እንደሆነ መታወቅ አለበት። በነገራችን ላይ የመከላከያ መኖር ምን ያክል አስፈላጊ እንደሆነ በተለይም ከአማራና አፋር ህዝቦች በላይ ምስክር ይኖራል ብየ አላምንም።
እስኪ በሞቴ መከላከያ ባይኖር ኢትዮጵያን ተዋትና የአማራን እጣ ፋንታ ዛሬ ላይ ምን ይሆን እንደነበር አስቡት? አማራም ሆነ ኢትዮጵያ በዚህ ቁመናቸዉ እንዲገኙ በማድረግ በኩል፣የልዩ ሀይላችን፣ሚሊሻና ፋኖ ተጋድሎ እንዳለ ሁኖ፣ ትልቁን ዋጋ የከፈለዉ መከላከያ አይደለም እንዴ? ታድያ የአማራ ወጣት ይሄንን ተቋም እንዳይቀላቀል መስራት ጥቅሙ ለማን ነዉ?
አንዳንድ የዋህ ወንድሞቸ ደግሞ የግዳጅ ብሄራዊ አገልግሎት መጀመር አለበት ይላሉ። በእኔ እምነት ይህ አባባል ከአማራጭ ዉጭ አይደለም። ሁኖም አሁን ጊዜዉ አይመስለኝም። በማሳመን ሊሰለፍ የሚችለዉን የአማራ ወጣት ገና የደረስነዉ አይመስለኝም። ስለዚህ ቅድምያ አሳምኖ ለማሰለፍ እንስጥ።
በአጠቃላይ የአማራ ህዝብ ለመከላከያ፣ለልዩ ሀይል፣ለፋኖም ሆነ ለሚሊሻ የሚሆን በቂ የወጣት ቁጥር ያለዉ ህዝብ ነዉ። ስለዚህ በነዚህ አደረጃጀቶች ሁሉ በበቂ ቁጥር መደራጀትና የአማራ ብሎም የኢትዮጵያ መከታ መሆን ይቻላል። ይሁን እንጅ የልዩ ሀይል፣ፋኖ ሆነ ሚሊሻ አደረጃጀቶች የአማራን ህዝብ በመከላከያ ዉስጥ የሚኖረዉን ተሳትፎ በአንዲት ቁጥርም ቢሆን ማጉደል የለበትም። ይሄም ማለት የአማራ ወጣት ከሁሉ በፊት ወደ መከላከያ ይቀላቀል፣አማራ ኮታህን ሞልተሀል በቃህ ሲባል ወጣቶቻችን ልዩ ሀይልን ተቀላቀሉ። ከዝያ ህዝባዊ አደረጃጀቶችም አሉ(ሚሊሻና ፋኖ)።
የአማራ ወጣት ቅድምያ መከላከያን ተቀላቀል!
Chu Chu
ተጨማሪ ያንብቡ:  በባህር ዳር፣ ወሎና ጎንደር የመምህራን እጥረት ተከሰተ | ተማሪዎች በአስተማሪ እጦት ፈተና ሳይፈተኑ ቀሩ

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.