ዶ/ር እሌኒ ገብረመድህን ከገለልተኛ የኢኮኖሚ አማካሪነት መነሳታቸውን የፕላንና ልማት ሚኒስቴር አስታወቀ

የፕላንና ልማት ሚኒስቴር መግለጫ ያወጣ ሲሆን ሙሉ መግለጫው እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡

ሀገራችን ኢትዮጵያን ለ27 ዓመታት በመራው በሕወሓት መራሹ መንግሥት ሀገሪቱ ያፈራቻቸው ምሁራን በየትኛውም የሀገራቸው ጉዳይ ተሳትፎ ማድረግ የሚችሉበት እድል ካለመኖሩም በላይ በሀገራቸው ጉዳይ ሐሳብ ባነሱ ጊዜ ሲሳደዱና ሲንገላቱ ቆይተዋል፡፡

2010 .. የመጣውን የመንግስት ለውጥ ተከትሎ በለውጡ አመራር ከተደረጉ ዘርፈ ብዙ ማሻሻያዎች ውስጥ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ምሁራን በሀገራችን የኢኮኖሚ ፖሊሲዎችና የልማት አቅጣጫዎች ላይ ገለልተኛ ምክር መስጠትና ግምገማ ማድረግ ይችሉ ዘንድ ዕድሎች ተመቻችቷል፡፡

በዚሁ መሠረት ሀገር እና ሕዝብ የሚሻገረው በሁሉም ኢትዮጵያዊና የኢትዮጵያ ወዳጅ ትብብር እንደሆነ የሚያምነው የለውጡ መንግስት፣ ምሁራን ሀገራቸውንና ወገናቸውን ከድህነት ወደ ተሻለ ሕይወት በፍጥነት እንዲሻገሩ የሚረዱ የኢኮኖሚ ፖሊሲዎች ላይ ምክር እንዲሰጡ ምቹ ምህዳር ከፍቷል፡፡

ይህ በተሻለ አደረጃጀት እና ቅንጅት ይፈጸም ዘንድ ታህሳስ 52013 .ም በክቡር የኢፌድሪ ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ አማካይነት አስራ ስድስት አባላት ያሉት ገለልተኛ የኢኮኖሚ አማካሪዎች ምክር ቤት እንደተሰየመ ይታወሳል፡፡ ከነዚህ አማካሪዎች መካከል ዶ/ር እሌኒ ገብረመድህን አንዷ ናቸው፡፡

ሆኖም የምክር ቤቱ አባል የሆኑት ዶክተር እሌኒ፣ በቅርቡ በዓለም አቀፍ ሰላምና ልማት ማዕከል በተዘጋጀ በድብቅ በተካሄደ የበይነ መረብ ስብስባ ላይ በሕጋዊ ምርጫ ቅቡልነት ያገኘውን የኢፌዴሪ መንግስት የመለወጥና የሽግግር መንግስት የማቋቋም አጀንዳ ላይ በመሳተፍ ሐሳቦችን ሲሰነዝሩ ተስተውለዋል፡፡ የምክር ቤት አባሏ በድብቅ በተካሄደው ስብሰባ ላይ ያነሷቸው ሐሳቦች በሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት በሽብርተኝነት የተፈረጀን ቡድን በግልጽ የሚደግፍ ሆኖ ተገኝቷል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  አጭጭር ዜናዎች

ምንም እንኳን የገለልተኛ ኢኮኖሚ አማካሪዎቹ በግል የራሳቸው የፖለቲካ አመለካከት ሊኖራቸው ቢችልም፣ አማካሪዎቹ ያቋቋሙት ም/ቤት ህገ ደንብ ግን የምክር ቤቱን አባላት የአማካሪነት ኃላፊነታቸውን ሲወጡ ከየትኛውም ፓርቲም ሆነ የፖለቲካ ድርጅት ነጻ መሆን እንደሚገባቸዉ በግልጽ ያስቀምጣል፡፡

በመሆኑም የአማካሪ ምክር ቤቱ ኅዳር 182014 .ም ባደረገው አስቸኳይ ስብሰባ ዶ/ር እሌኒ ገብረመድህን በምርጫ ስልጣን የያዘን መንግስት የመለወጥና የሽግግር መንግስት የማቋቋም አላማ ባለው ስብሰባ ላይ ባራመዱት ጠንካራ አቋም በጣም ማዘኑን በመግለጽ፣ ግለሰቧ በገለልተኛ የኢኮኖሚ አማካሪ ም/ቤት አባል ሆነው መቀጠል እንደማይችሉ ውሳኔውን በጽሑፍ አሳውቆናል፡፡

በመሆኑም የገለልተኛ የኢኮኖሚ አማካሪ ም/ቤቱን ውሳኔ መነሻ በማድረግና ዶ/ር እሌኒ ገብረመድህን በመንግስትና በህዝብ ታምነው የተጣለባቸውን ከፍተኛ ኃላፊነት ወደ ጎን በመተው፣ የኢትዮጵያ ሕዝብ በድምጹ ይሁንታ የሰጠውን መንግስት ቀይሮ የሽግግር መንግስት ስለማቋቋም በግልጽ ምክክር ሲያደርጉ በመገኘታቸው ከዛሬ ኅዳር 192014 ጀምሮ ከገለልተኛ የኢኮኖሚ አማካሪነት መነሳታቸውን እናሳውቃለን፡፡

የኢፌዴሪ ፕላንና ልማት ሚኒስቴር

አዲስ አበባ

(ኢ ፕ ድ)

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share