እሌኒ ገ/መድህን ዜጎችን በማራቆት የህወሓት የኢኮኖሚ ጡንቻ (ነጋሪት)

እሌኒ ገ/መድህን
——————-
መግቢያ፦ ይህን ጽሑፍ ከዚህ በፊት ሶስቴ ለጥፌዋለሁ (18 March 2020፣ 20 May 2018 እና 17 November 2018)፤ ለውጥ መጥቷል፣ መንግስት ተቀይሯል ብዬ የሀገርቷ ኢኮኖሚ ላይ አሻጥር የፈጸሙ ሰዎች እንዲጠየቁ ጥቆማ መስጠቴ ነበር፤ መሪው አብይ አህመድ ሆነና ጩህቴ የቁራ ጩህት ሁኖ ቀረ፤ ይህቺ ሴት “የሌባ ዐይነ ደረቅ መልሶ ልብ አድርቅ” ሆነችና አብይን ልትወቅስ ወደ ሶሻል ሚዲያ ብቅ ብላ ህዝቡን ስታንጫጫ ለ3ተኛ ጊዜ ለመለጠፍ ወደድኩ፤ ዛሬ መንግስት ግልበጣ ማሴሯ ይፋ ሲሆን ለአራተኛ ጊዜ መለጠፌ ነው፣
ይህች ሴት ከምዕራቡ ሀገር ሰላዬችና ከወያኔው አምባሳደር ብርሀነ ገ/ክርስቶስ ጋር ስለ መፈንቅለ መንግስትና የሽግግም መንግስት ስትዶልት የሚያሳይ ቪዲዬ ዛሬ Twitter ላይ ተመለክትኩ፣ ከስር ተራ ቁጥር 5 ላይ የተሰጠውን ማስፈንጠሪያ ተከትለው የምትለውን ይስሙ፣ “ትግሬም ሆነ ኦሮሞ አይደለሁም፣ ለምን ቤቴ ተፈተሻ” ብላ መርዘኛ አስተያየት መስጠቷም ተሰምቷል፣
አብይ አህመድ ከአርቲስቶችና ከሰባኪ ወንጌላን ጋር በጥምረት፣ በናትናኤል፣ ሙክታሮቪች፣ ስዩም ተሾመ አይነት ሀባብ ራስ አሸብሻቢነት የሚመራውን መንግስት የምጠላው እንዲሁ አይደለም፣ basic sophistication የሌለው ይህ ቀትረ ቀላል መንግስት ሀገር እዳያሳጣን እሰጋለሁ፣
ስለ እሌኒ ገ/መድህንና ዘመዴነህ ንጋቱ ጥቆማ የሰጠሁት ወያኔ መራሹ መንግስት ሞት ዋዜማ ላይ ነበር፣ በአይነ ቁራኛ እንዲጠበቁ፣ ካልሆነም እንዲታፈኑ፣ ከፍ ካለም እንዲያሰናብቷቸው የፈለኩት ከወያኔ ጋር ሁነው ለፈፀሙት ወንጀል ብቻ ሳይሆን ሊፈጥሩት የሚችሉት የኢኮኖሚ አሻጥር (sabotage) ለውጡን በአፍጢሙ እንደሚደፋው ስለገባኝ ነው፣ ደግሞም አቅሙና መንገዱ አላቸው፣
ለማንኛውም ንባቡ የሚከተለው ነው
___________________________________________________
ዜጎችን በማራቆት የህወሓትን የኢኮኖሚ ጡንቻ ካፈረጠሙ ሰዎች መካከል ዘመዴነህ ንጋቱን እና እሌኒ ገ/መድህንን የሚስተካከል አይገኝም፤ የኢትዮጵያን ገጸ-ምድር እና ከርሰ-ምድር ዶላር መክፈል ለሚችል ለውጭ ዜጋ አሻሽጦ ሰለከበረው፣ የወያኔ ባለስልጣናትን የገንዘብ ባህር ውስጥ ስለነከረው፣ ዜጋውን የደም እንባ ስላስለቀሰው ዘመዴነህ ንጋቱ ከዚህ ቀደም የተወሰነ ብያለው፤ ዛሬ የእሌኒ ገ/መድህንን ሸፍጥ በጥቂቱ ልንገራችሁ::
ስሟ በብዛት የሚነሳው የኢትዮጵያን ምርት ገበያ ድርጅት (ECX) ጋር ተያይዞ ነው፤ ሙሉ ስሟ እሌኔ ዘውዱ ገ/መድህን ይባላል፤ የተወለደችው አዲስ አበባ ሲሆን ዜግነት ከሲዊዘርላንድ ወስዳለች፤ በስታንፎርድ፣ በሚችጋን እና በኮርኔል ዩኒሸርስቲዎች ትምህርቷን ተከታትላለች፤ [don’t let her qualifications fool you; keep on reading]፤ ኢትዮጵያ ከመግባቷ በፊት ለአለም ባንክ ሰርታለች፤ ወደ ሀገር ቤት ያመጣትን ጉዳይ ስትገልጽ <<የኢትዮጵያን የንግድ ስርዓት መልክ እንዳሲዝ ከጠ/ሚ መለስ ዜናዊ ጥሪ ደረሰኝ>> ትላለች፤ ጥሪውን ተቀብላ ጨርቄን ማቄን ሳትል ወደ አዲስ አበባ አቀናች፤ ጠቅላይ ሚንስቴሩ ጽ/ቤት አንድ ቢሮ ተሰጥቷት ስራዋን ጀመረች፤ የኢትዮጵያን ምርት ገበያ ድርጅት (ECX) ተብሎ የሚጠራው ድርጅት በዚህ መልክ ተጸነሰ፤ እሌኒ እና መለስ ቢሮ ዘግተው የጸነሱት ይህ ድርጅት የዛሬ 12 ዓመት በአዋጅ ቁጥር 550/2000 ተወለደ፤
ይህ ድርጅት ምንም አይነት ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ (Macro Economic Significance) እንደሌለው በተለያዩ ምሁራን ተነግሯል፤ ጊዜ ያለው ከስር በተራ ቁጥር አንድ ላይ ያለውን ማስፈንጠሪያ ተከትሎ ፕሮፌሰር ሰይድ ሀሰን “The dangerous hype behind Ethiopian Commodity Exchange” በሚል ርዕስ ያተሙትን ጽሑፍ ያንብብ፤ በአጭሩ እሌኒ የገነባችሁ መጋዘንና የዘረፋ መዋቅር ነው፤ ይህን ገለጥለጥ አድርገን እንመልከት፤
የECX “የክርስትና” ተግባር በመላ ኢትዮጵያ የሚመረቱትን የቡና፣ ጥራጥሬ እና የቅባት እህሎችን ለውጭ ገበያ አቅራቢዎች ማጫረት ነው፤ በመጀመሪያ የቡና፣ ጥራጥሬ እና የቅባት እህሎች ተሰብስበው ECX መጋዘን ይገባሉ፤ በመቀጠልም የጥራት ደራጃ ይወጣላቸዋል፤ በመጨረሻም የመነሻ ዋጋ ይሰጣቸውና የድርጅቱ አባል የሆኑ ላኪዎች እንዲጫረቱ ይደረጋል፤ ከፍተኛ ዋጋ የሚሰጥ ላኪ አሸንፏል ተብሎ ጨረታው ይዘጋል፤ የዚህ ድርጅት አባል እና ተጫራቾች የህወሓት እና የህወሓት አጋፋሪዎች መሆናቸው የአደባባይ ሚስጥር ነው፤ በብሉንበርግ (bloomberg) ዘገባ መሰረት የኢትዮጵያን የብና እና የቅባት እህሎች በዋነኝነት ለውጭ ገበያ እያቀረበ ያለው የኢፈርቱ ጉና ትሬዲንግ ነው፤ በአጭሩ ECX የጉና መጋዘን ነው ብንል ከእውነታው አንርቅም፤ የሀገሪቱን ጠቅላላ የውጭ ንግድ በዚህ መልኩ በአንድ እዝ አስገብታ ስታበቃ ወያኔን እነሆ በረከት አለችው፤ ECX ምን ያህል በሙስና የነቀዘ መሆኑን ለመረዳት ከስር በተራ ቁጥር 2 ላይ የተሰጠውን ማስፈንጠሪያ ተከትለው ያንቡ::
የይስሙላው ጨረታ ሳያያቸው የውሃ ሽታ የሚሆኑ ምርቶች ቁጥር ስፍር የላቸውም፤ የዛሬ 8 ዓመት ገደማ 10 ሺህ ቶን (10 ሚሊየን ኪሎ) ቡና ከECX መጋዘን ጠፋ ተባለ፤ ምጥ ይግባ ስምጥ አልታወቀም፤ ይህ ያበገናቸው ውስጥ አዋቂዎች ጉዳዩን ለግል ጋዜጦች ሹክ አሉ፤ በአለም አቀፍ ደረጃም መነጋገሪያ ሆነ፤ ይህን ጊዜ መለስ ዜናዊ በቴሌቪዥን ብቅ ብሎ <<ያለፈው አልፏል ከንግዲህ መደገም የለበትም>> ብሎ ፋይሉን ዘጋው፤ ከስር በተራ ቁጥር 3 ያለውን ማስፈንጠሪያ ተከትለው የመለስን መልስ ይመልከቱ::
የዛሬ አመት ደግሞ 19 ሺህ ቶን (19 ሚሊየን ኪሎ) ቡና ከእሌኒ መጋዘን እንደጉም ተኖ ጠፋ ተባለ፤ ይህን አስመልክቶ አዲስ ዘመን ጋዜጣ የሰራውን ሪፖርት ከስር በተራ ቁጥር 4 ያለውን ማስፈንጠሪያ ተከትለው ያንቡ፤ ከሁሉ የሚገርመው ለይስሙላ እንኳን ህግ ፊት የቀረበ ሰው አለመኖሩ ነው፤ እንግዲህ እነዚህ ለሚድያ የበቁ ዘረፋዋች ናቸው፤ የወያኔ መንግስት ሲገረሰስ የሚጋለጡ ብዙ ዘረፋዎ እና ምዝበራዎች መኖራቸው አይጠረጠርም::
ለማንኛውም የወያኔ መንግስት ወደ መቃብር ሲወርድ ካቴን ከሚጠልቅላቸው ውስጥ እሌኒ ገ/መድህን ከፊት መስመር ትገኛለች፤ ይህ እንደሚመጣ ስለሚያውቁ እሌኒም ሆነች ዘመዴነህ የውጭ ዜግነታቸውን ሳይመልሱ አድፍጠው እየጠበቁ ነው፤
——————————————————-
እሌኒ ዛሬ ምን እየሰራች ነው?
ለዚህ ጥያቄ አጭሩ መልስ “ዛሬም ደም እየመጠጠች ነው” የሚል ነው፤ ዛሬ ደግሞ “BlueMoon” ተብሎ የሚጠራ shady business ከፍታለች፤ ግብረ ሰናይ ድርጅት (civil organization) ይሁን የግል ኩባን የሚታወቅ ነገር የለም፤ የግብርና ንግድ (agribusiness) ላይ ነው የምሰራው ትላለች፤ በዚህ ዘርፍ የሚታይና የሚዳሰስ ነገር ግን አታሳይም፤ የድርጅቱ ድረ ገጽ ላይ የሚታየው የሚከራዩ የስብሰባ አዳራሾች ከነ ዋጋቸው ነው፤
ከስር ፎቶው ላይ እንደሚታየው አጋሮቼ የምትላቸው ግዙፍ የምግባረ ሰናይ ድርጅቶች ናቸው፤ ሌሎቹን እንተዋቸውና Save the Children የግብርና ገበያ ውስጥ ምን ይዶለዋል?? የከፈተችው የምግባረ ሰናይ ድርጅት ነው እንዳንል ህዝቡን ስትረዳ አይቻለው የሚል ተፈልጎ አልተገኝም፤ ቁጥጥር የሚያደርግ የመንግስት አካል የለምና እሌኒ እንዳሻት እየሆነች ነው፤ በዚህ ሁሉ ውስጥ አንድ ነገር በእርግጠኝነት መናገር እችላለሁ፤ ከአለም አቀፍ የእርዳታ ድርጅቶችና ኢንባሲዎች በኢትዮጵያ ህዝብ ስም በሚሊየን የሚቆጠር ዶላር እየሰበሰበች እንደሆነ በልበ ሙሉነት መናገር እችላለሁ፤
(update:- “BlueMoon” የሚሰኝው የእሌኒ ድርጅት የሲአይኤ ድብቅ ፅህፈት ቤት መሆኑ አያጠራጥርም፣ ወትሮም ግራ የሚያጋባ አወቃቀርና ሽርክና የያዘ ድርጅት ነው)
በመጨረሻም:-
እሌኒ አብይን ጎሸም ማድረጓ ሊገርመን አይገባም፤ ወደ ፊት በአይጋ ፎረም ወይም በሌላ ሚዲያ ስራዓቱን የሚያጠለሽ ጽሑፍ ማውጣቷ አይቀርም፤ ይህ ደግሞ የአብይ መንግስት ወደ ቀልቡ ተመልሶ የበላሽውን ትፊ፣ በወንጀልሽ ተቀጭበት ያለ ጊዜ የታሰርኩት ሀሳቤን በመግለጼ ነው ለማለት ይጠቅማታል፤ [በነገራችን ላይ በወያኔ ዘመን በተለይ ዲያስፖራውን የሚወቅጥ ጽሑፍ አይጋ ፎረም ላይ ታወጣ ነበር]
ተጨማሪ ያንብቡ:  የሕወሓት አስተዳደር ሙስሊሞችን ከየአካባቢው እያደነ ማሰሩን ቀጥሏል

2 Comments

  1. ጥሩ ብለሀል አለቃ። አብይ አህመድ ደም መጣጮችን ከሚያስቀይም የኢትዮጵያን ህዝብ ማስቀየም ይቀለዋል አባዱላ ከሚነካበት አለም ቢያልፍ ይቀለዋል። ወርቅነህ ገበየሁ፣ተወልደ ገ ማርያም፣አርከበ እቁባይ፣ሌንጮ ባቲ ለታ፣ ሱሌማን ደደፎ፣ ታከለ ኡማ፣ አዳነች አቤቤ፣ሙሉ ነጋ፣አብረሀም በላይ የመሳሰሉ ነቀዞች መንግስት መዋቅር ውስጥ ምን ይሰራሉ? ትልቁን ጦር እዚህ ትቶ ቀለል ያለውን ጦር መውጋት ምን ይባላል? ስዩም ተሾመን በመሱለ ሰውስ መከበብ ምን ሞገስ ያሰጣል?

  2. ጥሩ ብለሀል አለቃ። አብይ አህመድ ደም መጣጮችን ከሚያስቀይም የኢትዮጵያን ህዝብ ማስቀየም ይቀለዋል አባዱላ ከሚነካበት አለም ቢያልፍ ይቀለዋል። ወርቅነህ ገበየሁ፣ተወልደ ገ ማርያም፣አርከበ እቁባይ፣ሌንጮ ባቲ ለታ፣ ሱሌማን ደደፎ፣ ታከለ ኡማ፣ አዳነች አቤቤ፣ሙሉ ነጋ፣አብረሀም በላይ የመሳሰሉ ነቀዞች መንግስት መዋቅር ውስጥ ምን ይሰራሉ? ትልቁን ጦር እዚህ ትቶ ቀለል ያለውን ጦር መውጋት ምን ይባላል? ስዩም ተሾመን በመሰለ ሰውስ መከበብ ምን ሞገስ ያሰጣል? ዛሬ ስዩም ተሾመ አቶ ታዲዎስን ከውጭ ቅጥረኞች አያይዞ ለማስመታት የሚንቀሳቀስ ሞራል የሌለው አውሬ ነው። አቶ ታዲዮስ ታንቱ ባላቸው ጉስቁልና 25000 ብር አገር ወዳድ ዜጋ ቢያስገባላቸው ክፋቱ ምንድነው?ስዩምስ የግለሰብ አካውንት ለማየት እንዴት access አገኘ? እሱ አካውንት ውስጥ በሚሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ እያለ ስዩም ማን የሞራል ገምጋሚ አደረገው? እንዲህ አይነት መናኛ ግለሰቦች ወደ ላይ መጠጋታቸው ነገሮችን ይበልጥ ያበላሻቸዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share