❝የገጠመንን የህልውና አደጋ በመገንዘብ ሁሉም ሕዝብ ለህልውና ዘመቻው የራሱን አስተዋጽኦ ማድረግ ይገባዋል❞ አቶ የሱፍ ኢብራሂም

ጥቅምት 28/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ምክትል ሊቀ መንበር የሱፍ ኢብራሂም በተለያዩ ግንባሮች በመንቀሳቀስ ከማንኛውም የዕይታ ልዩነት በላይ የሆነውን ሀገራዊ የህልውና ስጋት ለመመከት የሚደረገውን ትግል እያስተባበሩ ነው።
የጣልያን ተረክ የወለደው አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ኀይል ከውስጥና ከውጪ የሽብር፣ የሴራ እና የወንጀል አባሪዎቹ ጋር በመሆን በአደባባይ የዛተበትን ሕዝብ አንገት የማስደፋት እና ሀገር የማፍረስ እንቅስቃሴ በተግባር እየፈጸመ ይገኛል፡፡
በአማራ ክልል ሰፊ ወረራ የፈጸመው አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ኀይል ንጹሐንን በጅምላ በመግደል፣ መነኩሴዎችን እና አዛውንቶችን ሳይለይ አስገድዶ በመድፈር፣ የአማራ ሕዝብን የኢኮኖሚ መሰረት ለማናጋት ልክ የሌለው ዝርፊያና ውድመት በመፈጸም፣ መሠረተ ልማቶችን በማፍረስ፣ የሕዝብ መገልገያ ተቋማትን በመዝረፍ እንዲሁም በማውደም የህልውና አደጋ ደቅኗል፡፡
አቶ የሱፍ እንዳሉት አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ኀይል በሕዝብ ላይ ጸያፍ ድርጊቶችን እየፈጸመ ይገኛል፡፡ አብያተ ክርስቲያናትን ያረከሰ፣ መስጂዶችንም ያወደመ እምነት አልባ ስብስብ ነው።
አቶ የሱፍ የገጠመንን የህልውና አደጋ በመገንዘብ ሁሉም ሕዝብ ለህልውና ዘመቻው የራሱን አስተዋጽኦ ማድረግ እንደሚገባው መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡ የአንድ ሰው አስተዋጽኦ የጦርነቱን አቅጣጫ ሊቀይር እንደሚችል በማስገንዘብ፡፡
አቶ የሱፍ አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ኃይል በመደበኛ ውጊያ ብቻ ሊመከት ሰለማይችል ሕዝባዊ ማዕበል በመፍጠር መላው ኢትዮጵያዊ እንዲፋለመው ማድረግና ማጥፋት እንደሚያስፈልግም ገልጸዋል፡፡
በሕዝብ ግንኙነት፣ በሀብት ማሰባሰብ፣ ማኅበረሰቡን በማደራጀት፣ በጦር መሪነትም ይሁን በተለያየ ዘርፎች መረባረብ እንደሚገባም አስታውቀዋል፡፡
አቶ የሱፍ በሁሉም የአማራ ክልል አካባቢዎች ለህልውና ትግሉ ሕዝቡን የማስተሳሰር ተግባር እየተከናወነ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡
ሕዝቡም ለመዝመት ዝግጁነቱን ገልጿል፤ ሀብቱንም ለመስጠት አይሳሳም ነው ያሉት፡፡
የህልውና ትግሉ በባንዳ እና በአርበኛ መካከል የሚካሄድ መሆኑን የጠቀሱት አቶ የሱፍ የተራቆተ መነሻ ያለው የሽብር ኃይሉ በአጭር ጊዜ የመሞቱ ጉዳይ አይቀሬ እንደሆነም አመላክተዋል፡፡
የሐሰት ፕሮፖጋንዳን የሚመክት በቂ የሰው ኀይል፣ ሀብት እና ዕውቀት እንዳለም ተናግረዋል። ይህንን የማቀናጀትና አመራር የመስጠት ጉዳይም በትኩረት ይሠራበታል ነው ያሉት አቶ የሱፍ።
በተለያየ አግባብ ጦርነቱ የሕዝብ አጀንዳ እንዳልሆነ በማስመሰል በማወቅም ይሁን ባለማወቅ በሐሳብም ይሁን በተግባር ለሽብር ቡድኑ ድጋፍ የሚያደርጉ አካላትን በአፋጣኝ አድኖ በቁጥጥር ሥር ማዋል እንደሚገባም ገልጸዋል፡፡
ዘጋቢ፡- ደጀኔ በቀለ
ተጨማሪ ያንብቡ:  አሳማ ቢን ላደን ማን ነው?

1 Comment

  1. አቶ የሱፍ ኢብራሂም እና አቶ ጋሻው የአማራ የቁርጥ ቀን ልጆች መሆናቺሁን በተግባር አሳይታችሗል። ብዙወችንሞ ለመጨረሻ ትግል አነቃቅታችሗል። የኛ ጀግኖች።

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share