በጎንደር ሰማያዊ ፓርቲ ለድንበር መከበር፤ የቅማንት ማህበረሰብ የማንነት መብቱ እንዲከበር በተመሳሳይ ቀን ሰልፍ ሊወጡ ነው

“በጥይት ትመታላችሁ፣ መትረየስ ጠምደን እንፈጃችኋለን እያሉ እያስፈራሩን ነው”

– የቅማንት ማህበረሰብ የማንነት መብት ጥያቄ ሰልፍ አስተባባሪዎች

በዘሪሁን ሙሉጌታ (የሰንደቅ ጋዜጣ ሪፖርተር)

በመጪው እሁድ ጥር 25 ቀን 2006 ዓ.ም በጎንደር ከተማ ሰማያዊ ፓርቲ በኢትዮ-ሱዳን ድንበር መካከለል ጉዳይ ለሕዝብ ግልፅ አለመሆኑን በመቃወም ሰልፍ የጠራ ሲሆን፤ በተመሳሳይ ቀን በጎንደር ዙሪያ የሚኖሩ የቅማንት ብሔረሰብ አባላት ማንነታችን አልተከበረም በሚል ሕገ-መንግስታዊ ጥያቄአቸውን ለማቅረብ የሰላማዊ ሰልፍ ጥያቄ አቅርበዋል።

የጎንደር ከተማ (ፎቶ ፋይል)

ለጎንደር ከተማ አስተዳደር ሁለቱም ወገኖች የሰላማዊ ሰልፍ ጥያቄ ቢያቀርቡም፤ ለሁለቱም ወገኖች ለሰላማዊ ሰልፉ መካሄድ ማረጋገጫ አለማግኘታቸውን እየተናገሩ ነው። ሰማያዊ ፓርቲ ሰልፉን ለማስተባበር ወደስፍራው የላከውን የፓርቲውን አመራር ጨምሮ ሌሎች የፓርቲው አስተባባሪዎች ታስረው መፈታታቸውን ገልጿል። ሆኖም ሰልፉን ለማካሄድና የማሳወቂያ ደብዳቤ ለከተማው አስተዳደር ቢያቀርቡም አስተዳደሩ ደብዳቤውን ባለመቀበሉ ጠረጴዛ ላይ ትተው መውጣታቸውን የፓርቲው ሕዝብ ግንኙነት አስታውቋል። እስካሁን የከተማው አስተዳደር ምንም አይነት ምላሽ ያልሰጠ በመሆኑ ሰላማዊ ሰልፉ እንደተፈቀደ በመቁጠር ሰልፉን ለማካሄድ በዛሬው ዕለት 12 የአመራር አባላት ያሉት ቡድን ወደ ጎንደር እንደሚሄድ አስታውቋል።

በሌላ በኩል በበርካታ ጊዜያት የቅማንት ብሔረሰብ የቋንቋ፣ የባህልና የማንነት መብቱ አልተጠበቀም የሚሉ ወገኖች በተመሳሳይ ቀን (ጥር 25 ቀን 2006 ዓ.ም) ጥያቄአቸውን በሰላማዊ ሰልፍ ለመጠየቅ ሰልፍ መጥራታቸውን የቅማንት ብሔረሰብ የማንነት የራስ አስተዳደር ጥያቄ አስተባባሪ ኮሚቴ ሊቀመንበር አቶ አበራ አለማየሁ ለሰንደቅ ጋዜጣ አስታውቀዋል።

የኮሚቴው ሊቀመንበር የጎንደር ከተማ በጉዳዩ ላይ ለማነጋገር ጥረት ማድረጋቸውን ገልፀዋል። አስተዳደሩም የእነሱ ጥያቄ ሕገ-መንግስታዊ እንጂ የፖለቲካ አይደለም። ነገር ግን እናንተ ጥያቄ ካቀረባችሁ በኋላ ሰማያዊ ፓርቲ ሰላማዊ ሰልፍ ጠይቋል በማለት አጀንዳችሁ ተመሳሳይ ነው የሚል ጥያቄ ቀርቦላቸው አጀንዳችን የተለያየ መሆኑን ብንገልጽም፤ “በጥይት ትመታላችሁ፣ መትረየስ ጠምደን እንፈጃችኋለን” እያሉ እያስፈራሩን ነው ብለዋል።

ተጨማሪ ያንብቡ:  “በኢሕአዴግ መንግስት የሕግ የበላይነት ጭላንጭል በሐገራችን እየተዳፈነ ነው” – (ከሰማያዊ ፓርቲ የተሰጠ መግለጫ)

ከዚህ ቀደም ጥር 4 ቀን 2006 ዓ.ም በጅልጋ ወረዳ አይከል ከተማ ላይ ከ70 ሺህ በላይ ሕዝብ የተገኘበት ሰላማዊ ሰልፍ ማድረጋቸውን ያስታወሱት አቶ አበራ፤ በዚያን ጊዜም “በመትረየስ እንፈጃችኋለን” ቢሉንም ሕዝቡ ነቅሎ መውጣቱን ተናግረዋል። አሁንም በጎንደር ከተማ ከሰማያዊ ፓርቲ ቀድመው ሰላማዊ ሰልፍ ለማካሄድ ቢዘጋጁም በየቀበሌው ሕዝቡን በስብሰባ በመጥራት ወደ ሰልፉ እንዳይወጡ ቅስቀሳ እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል። በመሆኑም ያለውን ጫና ተቀቁመው ሰልፉን ለማካሄድ ወደኋላ እንደማይመለሱ ተናግረዋል።
እንደ አቶ አበራ ገለፃ፤ እነሱ የሰላማዊ ሰልፍ ጥያቄ ተቀባይነት ያላገኘው በተመሳሳይ ቀን ሰማያዊ ፓርቲ በሌላ አጀንዳ ሰልፍ በመጥራቱ እኛም ከሰማያዊ ፓርቲ ጋር አብረን እንደምንሰራ ተደርጎ ታይቶብናል ብለዋል። ይሁን እንጂ የእኛ ጥያቄ ሕገ-መንግስታዊ እንጂ የፖለቲካ ወይም የድንበር አይደለም ብለዋል።

የቅማንት ብሔረሰብ በአማራ ክልል በጎንደር የተለያዩ ወረዳዎች የሚኖር ሕዝብ መሆኑን የጠቀሱት አቶ አበራ፤ የሕዝብ ብዛቱም አንድ ሚሊዮን እንደሚሆን፣ የቋንቋው ተናጋሪዎችም ከ20 ሺህ በላይ እንደሚሆኑ ገልፀው፤ ሕዝቡ እራሱን በቻለ ዞን ለመተዳደር ተደጋጋሚ ጥያቄዎችን ሲያቀርብ ቆይቷል ብለዋል። በያዝነው ዓመት መስከረም ወር ጥያቄውን ለፌዴሬሽን ም/ቤት አቅርቦ ውሳኔ አለማግኘቱንም ተናግረዋል። የጎንደር ከተማ ከንቲባ አቶ ጌትነት አማረን በስልክ አግኝተን በዚሁ ጉዳይ ላይ የአስተዳደራቸውን አቋም እንዲያብራሩልን ያደረግነው ተደጋጋሚ ጥረት አልተሳካም።

6 Comments

  1. It’s about time that they recognize the Qemant for who they are. Gonder zuria and Chilga should be their home. I bet you it is not going to be well received by some quarters.

  2. በጣም የሚገርመኝ አማራ ስለሚባሉ ልሂቃን ሳስብ ነው። በጎን አማራ ተጎዳ አማራ ተፈናቀለ ወዘተርፈ እያሉ ሲለፍፉ እናያለን እንሰማለን። ኢትዮጵያውያን አላሉም። አማርኛ ተናጋሪ አማራ ዘጎችን አሉ። ለመሆኑ አማርኛ ተናጋሪ አማራ ብቻ ነው? እድሜ ለአጤዎቹ። ቋንቋችንን አጥተን ይሀው አማራ ተባልን አይደል? ኧረ እንዲያውም ያማራ ድርጅት መስርተዋል። ብዓዴን የማን ድርጅት ነው? እነሞረሽ ወገኔ ያማራው ድርጅት የማን ነው? መአድ የማን ነው? የአማራ! ታዲያ ይህ ዘረኝነት አይደለም? በሌላ በኩል አማርኛ ብናገርም አማራ አይደለሁም። በቃ ተውን ስንል ዘረኛ ከፋፋይ ምናምን። አሁን ማን ይሙት መትረጌስን ምን አመጣው? አማራ አይደለንም ስላልን? በመትረጌስ አማራ ማድረግ ይቻላልን? 21st ክ/ዘመን ቁጭ ብሎ እንዴት በ15ኛው ክ/ዘመን ጭንቅላት ያስባል? በሎጂክ ማስረዳት በብሔር ከመከፋፈል ይልቅ አንድነት እንደሚሻል ውህደት እንደሚበጅ ማስረዳት መከራከር የብስል ሰው ወግ ነው። በመትረገስ ግን የሚገርም ነው። ዶማ ታዲያ ከእንደዚህ አይነት ዶማ ጋ ውህደት ከመፍጠር በመትረጌስ ማለቅ አይሻልም? መች ነው በሰለጠነ አስተሳሰብ ማሰብ የምንጀምረው? ይህ ጥያቄ በርግጥ የወያኔ ሴራ አይደለም። የህዝብ ጥያቄ እንጅ። የወያኔ ቢሆን ኖሮ 23 አመት ባልፈጀ። ወያኔ ውሳኔ ለመስጠት አማራን ከምንም እንደማይቆጥር ልትገነዘቡ ይገባል። በተለያዩ
    ውሳኔዎቹ የገባቹህ መስሎኝ ነበር። ከየክልሉ እየለቀመ ስያባርርር ባማራ ይሁንታ አይደለም። ልካችሁን እወቁ ይልቅ የህዝብን ፍላጎት አክብሩ የሃገሪቱ ባለቤቶች እናንተ ብቻ አይደላችሁም። የኛም አባቶች ሞተዋል። ቆስለዋል። ታግለዋል። ስለዚህ ኢትዮጵያ የኛም ነች የናንተም ነች። በጋር ልንኖርባት ስንኖርባት ደግሞ ተከብረን ተፋቅረን እንጂ እናንተ ነግሳችሁ እኛ ጭሰኞች ሆነን አይደለም። አማራዎች ነን ባዮች አጠገባችሁ ያለን ሌላ ብሔረሰብ ምን እንደምትሉ ስለሱምን እንደማታከናውኑ ልባችሁ ያውቀዋል። ለኢትዮጵያ መፈራረስ መንስኤ ሳትሆኑ ሰከን ብላችሁ አስቡበት። ለወያኔ እና ሻዕቢያ መፈጠር በስተመጨረሻም ኤርትራን እንድናጣት የተደረገው በሃይለስላሴ እና ደርግ ምክንያት ነው። አሁንም ሌላ አደጋ ያንዣብባል ገና። ሰከን ብላችሁ አስቡበት።

  3. I think the Tigre invaders has always see the people of Gondar as their enemy No 1. Now they are organizing the so called Kimant issue which is none existence. They have completely asimiliated and they have no language other than Amharic. Now the tplf want to divide the people and conquare . They want the precieved enemy amara to be weaken in various forms. south wollo as Oromo and in gojam and north shewa that some areas are called as Oromo. The only solusion is to depose the tplf by a concerted armed struggle.

    • South wollo as oromo-where did you bring this nonsense? yes-there are oromo settlers in south wollo-just in awarded areas as oromia zone by the tplf opdo faction-not the whole wollo as oromo- dickheads like you does not know what the hell going on-in fact the true Amaras homeland is south wollo-read the book-“Rethinking Amhara through Heritage in Ethiopia”! wusha like you mixes things up! As far as kimnate is concerned, i do not think the Gonder Amharas are on their way, it is up to them to agree with each other first rather than blaming Amharas!

  4. how come two entirely different agendas come together?? blue party is running for national issue and the others are still tribal mentality … 20,000 people spoke the language … what kind of self administration you are claiming with the language 99% of you can not speak??? … that language, as far as I know is a dead one. The great people of Qemant, … please dont follow those power needy scums … you dont have any identity which is different from the rest people around Gondar.

  5. @Gondariew, you need two seven of holly water!, feel ashamed my broder! you can’t say this way! Do you think we are not concerned of National security? come on man!, It is Quaras and Metemas people who used to secure the border between sudan and Ethiopia, and you know those people who they are, right? if you’re really gondarie, you know the mentality of our people. I won’t say any thing dirty as you did say bcoz it is not the culture and tradition of my people. You know who pushed themselves to tribal mentality first. when you are attacked by tribals, you start looking for your own group. this group is definately is your own tribe. for language you are talking about, Please don’t worry, this is not your business. It is not the language which is dead it is your mind. በጣም ስላበሳጬኸኝ የሆነ ነገር ጣል ላደርግልህ ነበር። ግን ይቅር ለእግዜሩ ብያለሁ። 20,000 ህዝብ ይናገራል ትላለህ እንደገና ሞቷል ትላለህ። አትቀባጥር please!, እናም የፈለገ ቢፈጠር እንዳያቶችህ ሳይሆን አሁን በ21ኛው ክ/ዘመን እንደሚኖር ዜጋ በሰለጠነ አስተሳሰብ ሰው በሰውነቱ ብቻ አምነህ ከተቀበልክ ኢትዮጵያውያንን በኢትዮጵያዊነት ካንተ ጋ እኩል እንደሆኑ ካመንክ ምንም ነገር አትፍራ ውህደት እንጂ መለያየት የለም።
    @Belachew, አንተንስ መጀመሪያ ስምህን ሲያወጡ ነው ያበላሹት አቦ። በላቸው! ቤተሰቦችህ ነገረኞች እንደሆኑ ያስታውቃሉ። በላቸው ብሎ ስም! በማታውቀው ነገር አትዘባርቅ! ለነገረኛ ሰው ከዚህ በላይ መልስ የለኝም። በቃ አትዘባርቅ!

Comments are closed.

Share