እግሬ አውጪኝ ብሎ ከግንባር እየፈረጠጠ የነበረውን የመከላከያ ሠራዊት – ዘመድኩን_በቀለ

251557678 408202490861265 5558407747122995058 n
እግሬ አውጪኝ ብሎ ከግንባር እየፈረጠጠ የነበረውን የመከላከያ ሠራዊት መካነ ሰላም ከተማ ላይ መንገድ ዘግተው ከሸሸህ ሽሽ፣ መሸሽ መብትህ ነው። ነገርግን የሃገር ሃብት የሆነውን መሳሪያህን አውልቀህ ስጠን ያሉትን የመካነ ሰላም ወጣቶች ረሽኖ የተዘጋውን መንገድ አስከፍቶ በዐባይ አቋርጦ ጎጃም ጥንታዊቷ መርጡለ ማርያም ከተማ የገባው የሃገር መከላከያ ሠራዊት እንደ መካነ ሰላሙ ገድለኸን አታልፋትም በማለት የበላይ ዘለቀ ልጆች በዚህ መልክ መንገድ ዘግተው ከፈርጣጩ መከላከያ ጋር ሙግት ገጥመው ይተጋተጉ ይዘዋል።
… ታያላችሁ ቱ ምንአለ በሉኝ አሁን ብአዴን ይደውልና የአካባቢዊን ካድሬ አዝዞ መንገድ የዘጋውን ረፍርፈኸው እለፍ ይለውና ያሳልፋቸዋል። ከምር ዐማራ እኮ ነው። መካነ ሰላም ላይ ወንድሙን ገድሎበት መጥቶ መርጦ ለማርያም ላይ በሬ አርዶ ያበላዋል። ብትገድለው፣ ብታርደው፣ ብትቀጠቅጠው ሁሉን የመቻል ትከሻ የታደለ። አይ ዐማራ ታድሎ። ብቻ መጨረሻውን ተከታትዬ አሳውቃችኋለሁ። የበላይ ዘለቀ ልጆች እንደ ትግሬ ልጆች ትንሽ ደፈር ያሉ ይመስላል። ለማንኛውም እኔ አያገባኝም። የጥርስ ህመሜ እኮ ነው እንዲህ የሚያስለፈልፈኝ።
ዘመድኩን_በቀለ

1 Comment

  1. አዬ ዘመድኩን በቀለ ዛሬ ደግሞ ለማደሪያ የኪራይ ቤት ለመለመን በዚህ መጣህን? ዘመድኩን በቀለ አሉህን? ጠላትነው በቀለ ብትባል አይከፋም ነበር።አጋሰሥ ጌኛ ቆረንጮ

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.