የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በወቅታዊ ጉዳይ መግለጫ ሰጥቷል።

የመግለጫው ሙሉ መልዕክት ቀጥሎ ቀርቧል:-
እጅግ የተከበርከው የአማራ ክልል ሕዝብ ሆይ! በአሸባሪው የትግራይ ወራሪ ኃይል ሀገርን ማፍረስ ዋነኛ ቀዳሚ ዓላማ አድርጎ ይህንኑ ፍላጎቱን ለማስጠበቅ በአይነቱ የተለየ፣ በተሳሳተ ትርክትና የጥላቻ ፕሮፖጋንዳ የተጠለፈ ሕዝባዊ አሰላለፍ በመፍጠር መጠነ ሰፊ ወረራ መፈፀሙና እየፈፀመ መሆኑ ይታወቃል።
እድሜያቸው ከ12 እስከ 65 ዓመት የሚደርሱ ወንድና ሴቶች፣ አካል ጉዳተኞችና ነፍሰ ጡሮች፣ ካህናትና ሸኮች ሳይቀር እያስገደደ በማሰማራት ወደ አማራና አጎራባች የአፋር ክልሎች አዝምቷል።
በዚህ ወረራ ወደር የሌለው ጭካኔ በመላበስ አማራን እስከወዲያኛው አንገት ለማስደፋት በየደረሰበት አካባቢ ሴቶችን በመድፈር፣ ንጹሐንን በመረሸን፣ መሰረተ ልማቶችን በማውደም፣ የመንግሥትና የግለሰብ ሀብቶችን በመዝረፍ፣ የቤት እንሰሳትን በጥይት በመግደል ሕዝብን እያሸበረ ከቀየው እንዲሰደድ በማድረግ ላይ ይገኛል።
የትግራይ ወራሪ ኃይል ሀገርን የማፍረስና አማራን እንደ ሕዝብ የማጥፋት ዘመቻው ከመደበኛ ወታደራዊ አደረጃጀት በተጨማሪ በሕዝባዊ ማዕበል መቀልበስና መደምሰስ እንዳለበት ግድ የሚል ሁኔታ ስለተፈጠረ ሀገራዊ የመንግሥት ጥሪ መተላለፉ ይታወቃል።
ይህ ሀገራዊ የመንግሥት ጥሪ እንደተጠበቀ ኾኖ በአማራ ክልል ደረጃ ፈጣንና የተደራጀ ሁሉ አቀፍ ሕዝባዊ ዘመቻ ማካሄድ ጊዜ የማይሰጠው እጅግ አጣዳፊ ጉዳይ ሆኗል። ስለሆነም እድሜውና አካላዊ ብቃቱ የፈቀደለት የክልላችን ሀገር ወዳድ ዜጋ ኹሉ ከዛሬ ጀምሮ እስከ ጥቅምት 23/2014 ዓ.ም ድረስ ማንኛውንም መሳርያና ስንቅ በመያዝ ወደ ወረዳ ማዕከላት የክተት ጥሪውን ተቀብሎ እንዲገባ የክልሉ መንግሥት ታላቅ የሕልውና ዘመቻ ጥሪ አቅርቦልሃል።
ሁሉ አቀፍ የሕልውና ዘመቻውን የተደራጀ አመራር፣ በሕዝባዊ ማዕበል ተመስርቶ በእልህና በወኔ ለማከናወን የሚያስችል ዝርዝር ማስፈፀሚያ መመርያ በየአካባቢው ይደርስሃል።
የዚህ ክተት ዘመቻ ዋነኛ ኃይላችን ለመስዋእትነት የተዘጋጀ ሕዝባችን መሆኑን የክልላችን መንግሥት ያምናል። በመሆኑም አሸባሪውን የትግራይ ወራሪ ኃይል የከፋ ምኞች ማምከን ብሎም የገባበት ገብቶ ለመደምሰስ የቀረበውን የጀግንነት ጥሪ በመቀበል ኢትዮጵያን ለማዳን እንዲሁም የአማራ ክልልን ሕዝብ ከውርደት ለመታደግ እንድንዘምት የክልሉ መንግሥት ጥሪውን በድጋሜ ያስተላልፋል።
ህልውናችንን በትግላችን እናረጋግጣለን! እናሸንፋለን!
የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት
ጥቅምት 20/2014 ዓ.ም
ባሕርዳር፣ ኢትዮጵያ
ተጨማሪ ያንብቡ:  አብይ አህመድ ስልጣን የያዘው በኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ ተጋድሎ ነው....።"ግርማ ካሳ

1 Comment

  1. እነ አገኘሁ ተሻገር ነገር አበላሽተው ሂደዋል እነ አንዳርጋቸው ጽጌ ወቅት እየጠበቁ አንጉቱን ይሉታል እነ ብርሀኑ ነጋም መጤ ይሉታል ለአማራው ክፉ ሁኖ ለነሱ መልካም ሲሆን ይታያል። ትግሬ አማራን የጠላበት ኢትዮጵያዊነቱን ጠንቅቆ ስላወቀ ነው ኢትዮጵያ ፍርስራሽ ላይ ሊቆም የሚችል ሀይል የለም እነ አማራ ጠሎች ቀጥሉበት።

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share