ፌስቡክ የኦሮሞ ነጻነት ጦር (ሸኔ) የተባለውን አሸባሪ ቡድን ከገጹ ማገዱን አስታወቀ

በኢፌዲሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አሸባሪ ተብሎ የተፈረጀው የኦሮሞ ነጻነት ጦር (ሸኔ) ከፌስቡክ ያገድኩት ‘አደገኛ ድርጅቶች’ በሚለው መመሪያው መሠረት ነው ሲል ድርጅቱ አስታውቋል።

“የኦሮሞ ነጻነት ጦር ከፌስቡክ የታገደው ‘አደገኛ ድርጅቶች’ በተለይ ደግሞ ‘መንግሥታዊ ያልሆኑ ሁከት ፈጣሪ አካላት’ በሚለው ፖሊሲ ሥር ነው” ሲሉ የኩባንያው ቃል አቀባይ ለቢቢሲ አስታውቀዋል።
“ለዚህ ቡድን ድጋፍ የሚሰጥ ወይም ቡድኑ የሚፈጥረውን ሁከት የሚያወድስ” ይዘት ከፌስቡክ የማኅበራዊ ሚዲያ የትስስር መድረክ ላይ እንደሚጠፋ የፌስቡክ ቃል አቀባይ አስታውቀዋል።
የፌስቡክ ቃል አቀባይ ኩባንያው ድርጅቶችን በተለያየ ጎራ ከመፈረጁ በፊት ለጉዳዩ ቅርበት ካላቸው ባለሙያዎች ጋር ዝርዝር ሥርዓቶችን እንደሚከተል ጨምረው ገልጸዋል።
247335581 2117959768355360 6704301824426367674 n
(ኢ ፕ ድ)
ተጨማሪ ያንብቡ:  ከግርማ የሺጥላ ጋር የተሰዳደቡት ባለስልጣን ተባረሩ | በደሴ ተቃውሞ ሰልፍ ተደረገ

1 Comment

  1. ቄሱን ትቶ ዲያቆኑን? በመቶዎች የሚቆጠሩ የፌስቡክ አካውንት ከፍቶ ዓለምን እየበከለ ያለው ህወሓት አይደለም ወይ? ትግራይ ሚድያ ሃውስ፣ አንዴ በኦሮሞ አንዴ በአማራ ስም መግለጫ እና ፎቶሾፕ የሚያሠራጨው እያለ? አሁንማ ፍራንስስ ሃውገን የፌስቡክን ምሥጢር ዘክዝካለችና የቴክኖሎጂ እውቀት ያላቸው አገር ወዳዶች የህወሓት ካድሬዎችን ተግባር አጋልጠው ማሳገድ አለባቸው።

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share