ትህነግ በሚስጥራዊ ስብሰባ ኢትዮጵያ ውስጥ ግጭት በማስነሳት ትግራይን እንደ ሀገር ለመመስረት – ጌታቸው ሽፈራው

ትህነግ በሚስጥራዊ ስብሰባ ኢትዮጵያ ውስጥ ግጭት በማስነሳት ትግራይን እንደ ሀገር ለመመስረት ያስችላሉ ብሎ ያስተላለፋቸው ዓለም አቀፋዊ፣ ቀጠናዊና ሀገራዊ “ስትራቴጅያዊ ውሳኔዎች”
………………………………
በተለያዩ ሀገሮች የተሰባሰቡ የትህነግ ተወካይ ብሔርተኞች ለ6 ቀናት በZoom ተሰብስበው ሰንብተዋል። ተሰብሳቢዎቹ ከውጭም ከሀገር ውስጥም የተካተቱ ሲሆን በረሃ ካሉት የኪዳነ አመነ እና የመሃሪ ዮሃንስ አስተያየት ተደምጧል።
የውይይቶቻቸው ዋና ዋና አላማዎች የሚከተሉት ናቸው:_
ሀ) ትግራይ ሀገር እንድትሆን ለማድረግ ሊሰራ የሚገባው ውስጣዊና ውጫዊ የፖለቲካ ስራዎች ለመረዳዳት የሚለው ዋነኛው የስብሰባው አላማ ነው።
ለ) ይሄንን ለማድረግ የተስማሙበት ቅድመ ሁኔታ ትግራይ የጀመረችው ወታደራዊ ጦርነት አሸንፋ እንድትወጣ አማራጭ የሌለው ጉዳይ መሆኑ ነው። ይህ ካልሆነ፣ ትግራይ ካለችበት የጦርነት አዙሪት ከተሸነፈች ትግራይ እንደ ሀገር ይቅርና መቀሌ የትግራይ ክልል አካል ሆና አትቀጥልም የሚል መደምደሚያ ወስደው ነው ውይይቱን የጀመሩት። በውይይታቸውም በሚከተሉት ነጥቦች የጋራ መግባባት ላይ በመድረስ ተለያይተዋል።
1) የትግራይ ሀገረ-መንግስትነትን ለመመስረት ኢትዮጵያ ውስጥ ሶስት ዓበይት አብዮቶችን መፈጠር አለባቸው
2) የኦሮሞ ብሄር ምንም የጋራ አገራዊ ማንነት ስሌለው፣ በሀገራዊ ስሜት ሊነሱ ስለማይችሉም ጭምር የአዲስ አበባን ጉዳይ ምክንያት በማድረግ “ፊንፊኔ ኬኛ” ብለው እንዲነሱ ለማድረግ ከኦነግ ጋር አስፈላጊ ትብብር እንዲፈጠርና ለዚህም ትግሬዎች አስፈላጊውን ዋጋ ከፍለው የፊንፊኔን ጉዳይ በማነሳሳት “የኦሮሚያ አካል ካልሆነች” በሚል ጥያቄ አዲስ አበባ ላይ እሳት መጫር
3) በአፋርና በሶማሌ መካከል የተፈጠረው ግጭት በማባባስ፣ የአፋር ብሔረሰብ ላይ በትግራይ በኩል ጦርነት እንደሚከፈት በማድረግ extensial threat እንዲሰማው ማድረግ። በሶማሊና በትግራይ መገደል የጀመረ አፋር ሳይወድ በግድ ኤርትራና ጅቡቲ ካሉት አፋሮች ጋር እንዲተባበር ማድረግ። ይሄን ስልት በማፍጠን ከአፋር ጋር የመሬት ጥያቄ በማንሳት ወደ ቀጣዩ ውግያ መግባት። በውግያው የሚያጋጥመው ኪሳራ ወደ ስነልቦና ውድቀት ስለሚመራቸው በኢትዮጵያ ተስፋ ይቆርጣሉ
4) አፋር ውስጥ የሚነሳ ጦርነት በproxy ወደ ሶማሊ እንዲልም በማድረግ ሶማሊ ክልል እሳት እንዲደፋበት መስራት። ከዚህ በኋላ በጁቡቲና በታላቋ ሶማሊያ ያለውን የሶማሊ ብሔረሰብ በማነሳሳት ኢትዮጵያ ውስጥ ወደ ጦርነት ገብቶ ያለውን የታላቋ ሶማሊያ ሀገር ብሔርተኝነት እንዲያነሳ ቅስቀሳ ማካሄድ
5) የትግራይ ሀገረ የመሆን መንገድ መራመድ ሲጀምር፣ የመሬት የወሰን ጥያቄ ከአማራና ከአፋር ጋር በማንሳት የትግራይ ህዝብ ከነዚህ አረመኔ/አህዛብ ጋር ላንዴና ለመጨረሻ የሚለያይበት የስሜት ግንብ መስራት
6) በኤርትራ ጉዳይ ባድሜን በኃይል እንደተወሰደች በማወጅ ጦርነቱ በመክፈት የትግራዋይ ብሔርተኞች ማንሳት። ይሄን የሚያደርጉ ከኤርትራውያን ዲያስፖራ መጠቀም።
7) ከኢሳያስ ውድቀት በኋላ ለሚፈጠር ኤርትራዊ ስነ ልቦና ውድቀት ብሄራዊ ንቃት እንዲኖረው፣ ስልጣን በትግራዋይ ብሄርተኛ እንዲያዝ ማድረግ። ኤርትራ ውስጥ ላለው ትግራዋይ የመጨረሻ እድል መስጠት።
8) ኤርትራ ውስጥ የሚኖረውን ከትግራዋይ ማንነቱ ሊያተሳስረው የሚችል የሽግግር ግዜ ስለሚያስፈልገው መጀመርያ የተለያዩ ማንነቶች ያሏቸውን የኤርትራ ሕዝቦች በማደራጀት በብሄር ፌደራሊዝም የምትተዳደር ኤርትራ እንድትፈጠር መስራት ከዛ በኋላ በተወሰነ ግዜ ውስጥ የትግሬ አንድነት ማረጋገጥ
9) ኤርትራ ውስጥ ያሉትን አፋሮች ኢትዮጵያና ጅቡቲ ካሉት አፋሮች ጋር አብረው የሚሰሩትን ሀገር ለመፍጠር መቀስቀስና መደገፍ
10) በኢትዮጵያ፣ ሶማሊያና ጅቡቲ ያሉ ሶማሊ ወደ ትልቋ ሶማሊያ እንዲጨመሩ ማረግ
11) በኤርትራና በኢትዮጵያ ያሉትን ትግርኛ ተናጋሪ ህዝቦች ታላቋን ትግራይ እንዲመሰርቱ ማድረግ
12) ይቺ አሁን ኢትዮጵያ የምትባለው ሀገር ደግሞ አማራዎች ብቻ ይዛ እንድትቀር ማድረግ
13) በአጠቃላይ ሀገረ ትግራይን ለመመስረት አሁን ያለው የኤርትራ፣ የኢትዮጵያ፣ የሶማሊያ፣ የጅቡቲ ቅርፅ መቀየር አለበት። እነዚ ሀገሮች መልካቸው ካልቀየሩ ግን ትግራይ ለብቻዋ ተነጥላ ሀገር ለመሆን የሚቻል አይደለም። ለትግራይ ሀገር መሆን ከ4 ሀገሮች ጋር ጥብቅ ዝምድና ያስፈልጋል። እነሱም ግብፅ፣እስራኤል፣እንግሊዝና አሜሪካ ናቸው።
14) ለግብፅ በአባይ ጉዳይ መወያየት። ሀገረ ትግራይ እንድትመሰረት የምትደግፍ ከሆነ አባይ በወታደራዊ ስሪት በትግሬዎች አቅም እንዲፈርስ መደረግ እንደሚቻል የውሳኔ ሐሳብ ማቅረብ።
15) ከእስራኤል ጋር በሚደረገው ውይይት የሀገሪቱን የኋላ ሁኔታን በማንሳት ትግራዋይ ተመሳሳይ መንገድ እያለፈ እንዳለ ማሳመን
16) ከእንግሊዝና አሜሪካ ሚደረገው ውይይት ትግራይ ለስነ-ሐሳብ ኒዮ-ሊበራሊዝም የምትቀበል ሀገር እንደሆነች በማሳመን ትግራይ ሀገር ስትሆን የሀገሪቱ መአድኖች በነሱ ሀገር ድርጅቶች እንደሚቆፈር መግባባትና የሁለቱ ሀገሮች NGO ትግራይን ማሳረፍያቸው ማድረግ እንደሚችሉ ማሳመን። በተጨማሪ እነዚህ ሀገሮች በአፍሪካ ቀንድ የሚያወጡትን ፖሊሲ ትግራይ መጀመርያ እንደምትተገብር መቀበል
17) የቻይና እና የሩስያ ጉዳይ ከአሜሪካና ከእንግሊዝ ጋር ሆኖ እንዲፈታ መስራት
18) አሜሪካና እንግሊዝ ላቀረቡት የውሳኔ ሐሳብ ሙሉ በሙሉ መቀበል። ያቺ ወንዝ ልትሻገር የማትችል ጉዳይ የprotestanism ሃይማኖት ተቀበሉ ከሚል ውጭ ያለውን መቀበል።
19) በኤርትራ እያደገ ያለውን የእስልምና መስፋፋትን እንደ ምክንያት በማቅረብ ያለንን ስጋት ማቅረብ፣ በክርስትና ላይ እየደረሰ ያለውን እንደ አጋጣሚ መጠቀም።
………………………………………
ማስታወሻ:_
1) ፅሁፉ ከትግርኛ ወደ አማርኛ የተተረጎመ ሲሆን የ Zoom ውይይቱ ጠቅለል ተደርጎ ሪፖርት የተደረገበት መሆኑ ተገልፆአል
2) ከትግራይ በርሃ የተሳተፉት ከኢትዮ ቴሌኮም ውጭ በሚሰሩ ዓለም አቀፍ ስልኮች ውይይት እንዳደረጉ ተጠቁሟል።
3) ውይይቱ በከፍተኛ ሚስጥር የተያዘ ነው ተብሏል።
4) ተሰብሳቢዎቹ መካከል ምሁራን፣ አክቲቪስቶች፣ ታጋዮችና ሌሎችም እንዳሉበት ተገልፆአል።

3 Comments

 1. ደንቆሮ የሰማ እለት ያብዳል ይባላል።
  አሁን ይሄ ምን ምሥጢራዊ ስብሰባ ያስፈልገዋል? ምን ምሥጢር ወይም አዲስ ነገርስ አለው? ያረጀ ያፈጀው የእንግሊዝ የምሥራቅ አፍሪካ ፕሮጄክት አይደለምን? የሕገመንግሥቱና የኦህዴድስ መንገድ ከዚህ የተለየ ሌላ ምን መዳረሻ አለው?

  • ደንቆሮ የሰማ እለት ያብዳል ይባላል። old sayings of amhara elites like this lack respect to people who lost their sight and suffer from hearing dificulties ! That is why we said amhara elites lack dignity and do disrespcet others
   አሁን ይሄ ምን ምሥጢራዊ ስብሰባ ያስፈልገዋል? ምን ምሥጢር ወይም አዲስ ነገር

 2. There hardly is anything “novel’ in this report. It is mostly details of the same old British project for East Africa. Dismember Eritrea and annex the lowlands to the Sudan, dismember Ethiopia and annex western territories into Sudan (North/South Sudan). annex the Ogaden into Somalia…..etc. Essentially break up Ethiopia and annex its parts into mostly the surrounding British Colony (Sudan, Kenya, Somalia) and let France etc pick the leftover. The core of this strategy is a barren, land-locked territory for the Orhtodox Tigres (Tigray-Tigrign, highlander Eritreans and Tigrayans). How any human being with any intelligence would fight to create such a country is beyond my imagination. Land-locked because the Afar would “go” with both Massawa and Asseb.
  It is strange to see the British still supporting this old Colonial era mayhem, when they can just digitally colonize the whole Ethiopia as they are about to do with their “Global Partnership on Ethiopia” a thinly guised British take-over of Ethiopian Telecom.

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.