ያ’ገሬና የኔ – አትክልት አሰፋ (ጋዜጠኛ) – ከቫንኩቨር

እናቴና አገሬ ሙግት ገጠሙና፣
ሚስቴና እናት አለም ተወዳደሩና፣
ልጄ እና እማምዬ ፉክክር ገቡና፣
አንዱን ምረጥ ብለው ድርቅ ሲሉብኝ፤
እናቴም ውዴ ናት፣
ሚስቴም የኔ ፍቅር፤
ልጄም ንጉሴ ነው፤
የሚጣፍጥ ከማር፤
የግሌ የራሴ የማ’ለውጣቸው፣
በሰላሳ ዲናር የማልቀይራቸው፤
እናት፣ ሚስት፣ ልጄ፤ ሁሉም የኔ ናቸው።
እኔ ግን ያገሬ፤
እኔስ የ ‘ማምዬ…
የግል ንብረት ነኝ ብዬ መለስኳቸው።
ዲሴምበር 15/2013- ቫንኩቨር (በርናቢ)

ተጨማሪ ያንብቡ:  የድምጻዊ ኢዮብ መኮንን ቃለ ምልልስ ቪድዮ - ለትውስታ
Share