በፈረስ ጒግሥ ጨዋታ መሃል ፈረስ አይለወጥም (ተክሌ መኮነን)

  • በኦሮሚያ ክልል ኦሮሞ ባልሆኑ የሌሎች ነገዶች አባላትና በክርስቲያኖች ላይ የተፈጸመው ዐረመኔአዊ ግድያና ንብረት ውድመት ኦሮሚያን «ንፁኅ ኦሮሞዎች» ብቻ የሚኖሩባትና ኢትዮጵያን «ኦሮሙማ» የማድረግ ዓላማ የመጀመሪያው መጨረሻ ዕቅድ ነው!
  • በመንግሥት ከልክ ያለፈ ትዕግሥት፣ በትሕነግ/ኦነግ ጣምራ እንቅስቃሴ፣ ኢትዮጵያን ለመበተን የሚደረገውን ዕኩይ ተግባር እናወግዛለን!
  • መንግሥት ኢትዮጵያን ለማዳን ዜጎችንና ለሀገር ልዕልና የሚያስቡ የፖለቲካ ድርጅቶችን የማስተባበርና አስፈላጊውን መንግሥታዊ ግዴታውን የመወጣት ታሪካዊ ኃላፊነት አለበት!
  • መንግሥት ሥራውን የሚያከናውነው በሕግ እንጂ ተደጋግሞ ተሞክሮ ውጤታማ ባልሆነ ሽምግልና ሊሆን አይገባም። ወንጀል የፈጸመ ለፍርድ መቅረብና በሕግ አግባብ ሊዳኝ ይገባል።

ኦነግ ፣ ኦነግ ወለድ ድርጅቶችና ትሕነግ ኢትዮጵያን ለመበታተን ለሚሹ የውጪ ኃይሎች የውስጥ ተባባሪ በመሆን ለዘመናት የኢትዮጵያን አንድነት ሲፈታተኑ የቆዩና ያሉ፤ ፀረ-ኢትዮጵያ፣ ፀረ-ኦርቶዶክስ እና ፀረ-ዐማራ ስብስቦች መሆናቸው ይታወቃል። የድርጅቶቹ ፕሮግራሞችና የፕሮፓጋንዳ ጽሑፎቻቸው በግልጽ ይህንኑ የሚያመለክቱ ናቸው። በመሆኑም ባለፉት 50 እና ከዚያም በላይ በሆኑ ዘመን ጠገብ እንቅስቃሴዎቻቸው፣ የኢትዮጵያ አንድነት ዋልታ የሆኑ ማኅበራዊ፣ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ የወል ዕሴቶች ሲንዱና ሲያወግዙ ኖረዋል። በዐማራ፣ በአኙዋክ፣ በሶማሌ፣ በጉራጌ፣ በጌዲዮ፣ በጋሞ ወዘተ ነገዶች ላይ ሠፊ የማፈናቀልና የዘር ጥቃት ፈፅመዋል። አያሌዎች ለዘመናት ከኖሩባቸው አካባቢዎች በአሰቃቂ ሁኔታ እንዲፈናቀሉ ተደርገዋል። ስለፖለቲካ ምንም የማያውቁ ንፁኀን ዜጎች ኦሮሞ ባለመሆናቸው  ብቻ፣ በተወለዱበት እና ባደጉበት ሥፍራ ዘግናኝ በሆነ ሁኔታ ተገድለዋል። ከተገደሉም በኋላ በሌሎች ላይ ሽብር ለመልቀቅ ሲባል በአሰቃቂ ሁኔታ አስከሬናቸው በየመንገዱ እንዲጎተት፣ እንዲሰቀል፣ እንዲቆራረጥና እንዲቃጠል ተደርጓል። ንብረታቸውም እንዲሁ በእሳት እንዲጋይና እንዲወድም ተደርጓል። በቦታው የነበሩ የክልሉ የፀጥታ አባላትም ነገሩን ለማስቆም ምንም ዓይነት ሙከራ አላደረጉም።  ይህም በመንግሥት መዋቅር ውስጥ ያሉት ኀላፊዎች  ሆን ብለው ወይም በሌሎች ምክንያቶች የጥፋት ቡድኑ ተባባሪዎች እንደሆኑ ያሳያል።

ዐማርኛ ቋንቋን፣ ዐማራንና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን በአውራ ጠላትነት ፈርጀው ሠፊ የማጥፋት ዘመቻ ከከፈቱ ዓመታት ተቆጥረዋል። በዚህም መጠኑ እጅግ ከፍተኛ የሆነ ዐማራ እንዲገደልና እንዲፈናቀል ከመደረጉም በላይ፣ ማንነቱን መሠረት ያደረጉ የማንቋሸሽና የማዋረድ ተግባሮች ተፈጽመዋል።

ትሕነግ/ኢሕአዴግ የአገሪቱን የፖለቲካ ሥልጣን እንደተቆጣጠረ፣ ኦሮሚያ ብሎ በከለለው የኢትዮጵያ ሠፊ ግዛታዊ አካል ውስጥ በሚኖሩ ሌሎች ነገዶች ላይ በተከታታይ የተፈፀሙና እየተፈፀሙ  ያሉ የዘር ጥቃቶችና ማፈናቀሎች ክልሉን የኦሮሞዎች ብቻ የማድረግ ዓላማ ያለው መሆኑ በግልጽ ይታወቃል። ባለፉት ሁለት ዓመታት በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች በኦነግ ሸኔ፣ ኦነግ ወለድ ድርጅቶችና በትሕነግ ትብብር ኦሮሞ ባልሆኑ ኢትዮጵያውያን ነገዶች ላይ የተካሄደው የዘር ፍጅት  ኦነግ «ኦሮሙማ» የሚለውን ትርክቱን ዕውን የማድረግ እንቅስቃሴ በይፋ መጀመሩን ከማሳየቱም በላይ፣ የትግሬ ነፃ አውጭ ነኝ ባዮች ላለፉት አርባ ዓመታት ዐማራና ኦሮሞን እሳትንና ጭድ በማድረግ የሥልጣን ዘመናቸውን ለማራዘም ሲያራምዱት የነበረው ኢትዮጵያን የማፈራረስ ዕኩይ ተግባር መሆኑን የተፈጸሙት ዘር ተኮር ጥቃቶች ጉልኅ ማሳያዎች ናቸው።

በትሕነግ እና ኦነግ ሼኔ ትብብር ሰሞኑን በኦሮሚያ ክልል በተለይም በሻሻመኔ፣ ዝዋይ፣ አዳሚቱሉ፣ አርሲ ነገሌ፣ ባሌ፣ ሐረርጌ፣ ወዘተ ኦሮሞ ባልሆኑና በክርስቲያኖች ላይ የዘር ማጥፋት ዓለም አቀፍ ወንጄል በንፁኀን ሰዎች ላይ ተፈጽሟል የምንለው ያለምክንያት አይደለም። ጄኖሣይድ ዎች የተባለው ዓለም አቀፋዊ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅት፤ የዘር ማጥፋት ሂደቶች መለያ መገለጫዎች በማለት የዘረዘራቸው ማሳያዎች ባለፉት 28 ዓመታት በዐማራ፣ በጒራጌ፣ በአኙዋክ፣ በጌዲዮ፣ በሶማሊ እና በጋሞ ነገዶች ላይ ትሕነግና ኦነግ በትብብር ሁሉንም የዘር ፍጅት መገለጫ መለያ ባሕሪት ባሟላ መልኩ ፈፅመዋል።  የዘር ፍጅቱንም የፈፀሙት ኦሮሞና ሌሎች ተባባሪዎች ከእነርሱ ውጭ ያሉትን፣ “ዐማራ፣ ጒራጌ፣ ጋሞ፣ ክርስቲያን” ብለው በመለየትና «ነፍጠኛ፣ የምኒልክ ሠፋሪ፣ መጤ፤ ጉራጌ፤ ጋሞ» የሚሉ መለያዎችን በመስጠት ነው። ኦሮሞ ያልሆኑትንና ክርስቲያኖችን ከእነርሱ በመለየት የስም ዝርዝር የያዙና በዚያ እየተመሩ የፈጸሙት መሆን፤ ለጥቃቱ ልዩ ዝግጅትና የተቀነባበረ ቅስቀሳ በማኅበራዊ መገናኛዎች፣ ኦኤምኤን (OMN) እና ትግራይ ሜዲያ ሀውስ (Tigrai Media House) በተሰኙ ቴሌቪዥኖች የተቀነባበረ ዘመቻ ማካሄዳቸው፤ በዚህም «እነርሱ» ብለው በለዩአቸው ላይ ዐረመኔአዊ ጭፍጨፋ ማካሄዳቸው የዘር ፍጅት ለማካሄዳቸው ነቃሾች ናቸው።  ይህን ሐቅ ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ በትክክል እንዳይገነዘብ «ኦሮሞ ተጨፈጨፈ፣ ዶ/ር ዐቢይ ኦሮሞ አይደለም፤ ነፍጠኛ ነው» የሚሉ የክሕደት ቅስቀሳዎችን ይዘዋል። እነዚህ ተግባሮች በአንድነት ሲጠቃለሉ ኦነግና ትሕነግ/ሕወሓት በጋራ ኦሮሞ ባልሆኑ ነገዶች ላይ ጄኖሣይድ (የዘር ፍጅት) በማያሻማ ሁኔታ የፈጸሙና እየፈጸሙ ያሉ እንደሆነ ድርጊቶቹ በግልጽ ያሳያሉ።

ተጨማሪ ያንብቡ:  የእስረኛው ‹‹ጋዜጠኝነት›› ሌላ ፈተና

ይህ የሰሞኑ በኦሮሚያ ክልል በኦነግ ሼኔ እና በትሕነግ/ሕወሓት ትብብር የተፈጸመው የዘር ዕልቂት፤ በዘር ዕልቂት ፈጻሚዎቹ ጥንካሬና ድርጅታዊ ብቃት ብቻ የተፈጸመ ነው ለማለት አይቻልም። «በዕንቁላሉ በቀጣሽኝ» እንደተባለው፤ ባለፉት ሁለት ዓመታት በተለያዩ ያገሪቱ ክፍሎች መጠነ ሠፊ የሆነ ሕዝብ ሲፈናቀል፣ የጅምላ ግድያ ሲፈጸም፣ ባንኮች ሲዘረፉ፣ በሁሉም ያገሪቱ ክፍሎች ዘር ተኮር ግጭቶች ሲፈጸሙ ወዘተ መንግሥት የመንግሥትነቱን ሚና «ታፍኖ የኖረ ቤት ሲከፈት ብዙ የሚተነፍግ ነገር ይኖራል» በሚል መርሕና መጠኑን ባለፈ ትዕግሥት ኀላፊነቱን ባለመወጣቱ፣ ይኸውና ሰሞኑን ኦሮሚያ ክልል ውስጥ ኦሮሞ ባልሆኑትና ክርስቲያን በሆኑ ሰዎች ላይ በሁለቱ ፀረ ኢትዮጵያ በሆኑት ኦነግ እና ትሕነግ እጅግ ዘግናኝ ጭፍጨፋና የንብረት ውድመት ሊፈጸም ችሏል። ከሁሉም በላይ የሚያሳዝነው ግን «ጅራፍ ራሱ ገርፎ እራሱ ይጮኻል» እንደሚባለው፣ እነርሱ ጥቃቱን ፈፅመው ተጠቃን የሚል ጩኸት ለዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ በማሰማት ላይ መጠመዳቸው ነው።  ይህን እንዲያደርጉ ያስቻላቸው ደግሞ የመንግሥት እንደመንግሥት የዜጎችን ደኅንነትና ሰላም የማስጠበቅ ኀላፊነቱን መወጣት አለመቻሉና ሌሎች የጥቃቱ ሰላባ የሆኑት ነገዶችም፤ በጥቃት አድራሾቹ ላይ ተመጣጣኝ መልስ ለመስጠት ዝግጁ አለመሆናቸው  ነው።

ይህ በግብፅ አይዟችሁ ባይነት፣ በኦነግ ሼኔ እና በትሕነግ የተቀነባበረ ሤራ በኦሮሚያ ክልል ነዋሪ በሆኑ ኦሮሞ ባልሆኑት ነገዶች ላይ የተፈፀመው የዘር ፍጅት፤ ከክልሉ የፖሊስ፣ የልዩ ኃይልና የፀጥታ መዋቅር ዕውቅና ውጪ ነው ለማት አያስደፍርም። በሁሉም ክልሎች የተፈፀመውን ጥፋት፤ ይህ አካል የድርጊቱ ተባባሪ ወይም ቋሚ ተመልካች ባይሆን ኖሮ፣ ጥፋቱን ሳይጀመር ማክሸፍ ወይም ከተጀመረም በኋላም ቢሆን ከግማሽ በታች መቀነስ ይቻል እንደነበር ይታመናል።  የዚህም ምክንያቱ «ተለውጫለሁ፣ ለለውጥ ቊሜአለሁ» በሚለው መንግሥታዊ መዋቅር ወስጥ የኦነግና የትሕነግ/ሕወሓት ዓላማ አራማጆች በወሣኝ መዋቅሮች ውስጥ ሁነኛ ቦታ እንደያዙ ድርጊቶቹ በጉልህ እያሳዩ ነው። የኦነግና የትሕነግ/ሕወሓት የጋራ መግለጫዎች፣ በኦኤምኤን (OMN፣ ትግራይ ሜዲያ ሀውስ (TMH) መገናኛ ብዙኃን የሚተላለፉት መልዕክቶች የዚህ አባባል ነቃሾች ናቸው።

በሌላ በኩል መቀመጫቸውን ካገር ውጪ ያደረጉ ፀረ-ኢትዮጵያና ፀረ-አንድነት የሆኑ ቡድኖችና ግለሰቦች እንዲሁም የመገናኛ ብዙኃን ለሚያሰራጩት ፀረ-ኢትዮጵያና የዘር ፍጅት ተጠያቂ እንዲሆኑ፣ ኢምባሲዎችና ቆንጽላዎች፣ ኢትዮጵያን አፍቃሪ በሆኑ በውጭ አገር የሚኖሩ ኢትዮጵያውን በጥምረት የተቀነባበረ ሥራ ባለመሠራቱ፤ አጥፊዎቹ በጠፊዎቹ ላይ ሌላ ተደራራቢ ጥፋት እንዲፈፀምባቸው ድምፃቸውን ከፍ አድርገው ሲጮኹ እየሰማን ነው። ኦነግ ሼኔ እና ትሕነግ/ሕወሓት በትብብር አገራችን እያተራመሱና እያኮሰመኑ እያለ፣ በተቃራኒው የተበደልን ጩኸት ለዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ሌት ተቀን እያሰሙ ይገኛሉ። በአውሮፓ፣ በአሜሪካና በካናዳ በተከታታይ የተካሄዱት የሁለቱ ፀረ-ኢትዮጵያ ቡድኖች አባሎች ሰልፎች ኢትዮጵያን ለመበተን ላቀዱት የረጅም ጊዜ ግብ፤ ዓለም አቀፉን ማኅበረሰብ ከጎናቸው ለማሰለፍ የታቀደ መሆኑ ጥርጥር የለውም። የኢትዮጵያ ጠላቶች በዚህ መጠን ተደራጅተው በውስጥና በውጭ ተናበው እየሠሩ ባለበት ወቅት፣ ለኢትዮጵያ አንድትነ ቈሜአለሁ የሚለው ወገን በውስጥም በውጭም ነጠላ ነው።

ባንድ እጅ ማጨብጨብ እንደማይቻል ሁሉ፤ በነጠላ ትግልም ማሸነፍ አይቻልም። ስለሆነም የአንድነት ጎራው ከነጣላ ጒዞ ወጥቶ ድርብ መሆን መቻል አለበት። ይህን መረን የለቀቀ የፀረ-ኢትዮጵያ ቡድኖች ዓላማ ለማክሸፍ አገር ወዳድ የሆኑ ወገኖች አንሰው ከሚያሳንሱን ጥቃቅን አጄንዳዎች ወጥተን፣ ትልቋን ኢትዮጵያ ከተደገሠላት የብተና አደጋ ለመታደግ በአንድነት ልንቆምና ድምፃችን ልናሰማ ግድ ይለናል። ከዚሁ ጋር ተያይዞ «በጉግሥ ጨዋታ መካከል ፈረስ አይቀየርም» የሚለው አባባል አገራችን ላለችበት ነባራዊ ሁኔታ ልንከተለው የሚገባ መርሕ ይመስለናል። በዚህ ጊዜ መቆም ያለብን አፍአዊም ይሁን ልባዊ ኢትዮጵያና የኢትዮጵያ አንድነት ከሚለው ኃይል ጋር እንጂ፣ የዚህ ተቃራኒ ከሆነውና በግልጽ «ኢትዮጵያ ትፍረስ፣ ኦሮሙማ ይንገሥ» ከሚለው ጠላት ጋር መሆን የለበትም። በመሆኑም የአገራችን ቀጣይነትም ሆነ፣ አሁን የገጠሟትን ችግሮች ድል ለመንሳት ሰልፋችን፤ ለኢትዮጵያ አንድነት ተጠብቆ መዝለቅ ከሚታገሉ ወገኖች ጎን መሆን ወቅቱ ያቀረበልን የእናት አገር ጥሪ ነው።  ይህን ስንል በእርግጥ የዶ/ር ዐቢይ አስተዳደር የሚሠራቸው ሥራዎች ሁሉም ትክክል ናቸው፤ ሥልጣን ሲረከቡ ለገቧቸው ቃሎችና ሁሉንም ላማለለው « ስንኖር ኢትዮጵያዊ ፣ ስንሞት ኢትዮጵያ ነን» ላሉን  ሐሳቦች ፀንተው ወዲዚያ አቅጫጫ እየመሩን ነው ማለታችን እንዳልሆን ግንዛቤ ሊያዝ ይገባል። እያልን ያለነው፤ በአሁኑ ሰዓት ግብፅ እያደረገችው ካለው ከበባ፣ ኦነግ ሼኔ እና ትሕነግ/ሕወሓት «እኔ ካልበላሁት ጭሬ አፈሰዋለሁ» በሚለው እሳቤአቸው ገፍተው እያደረሱት ካለው ኢትዮጵያን የመበተን ዓላማ አንፃር፣ እንዲሁም ከተለያዩ ዙሪያ ገብ ሁኔታዎች ምዘና አኳያ፣ «ጅቡ ከሚበላህ በልተኸው ተቀደስ» እንዲሉ፣ በሥልጣን ላይ ያለውን መንግሥት ከነችግሮቹ መደገፍ፤ ኢትዮጵያን ከጥፋት የመታደግ ትልቁን ሥዕል መመልከት መሆኑን መገንዘብ እጅግ ተገቢ ነው ።

ተጨማሪ ያንብቡ:  ኦሪት ዘፍጥረት ኦሮሞ ከውሃ ነው የመጣው! የእርግማን ትውልድ! - ሰርፀ ደስታ

ስለሆነም፤ እኛ ከመንግሥት ጐን ስንቆም፣ መንግሥትም ለሚከተሉት ጥያቄዎች ሁነኛ መልስ እንዲሰጠን እንጠብቃለን።

  1. ቀደም ሲልም ሆነ ሰሞኑን በኦሮሚያ ክልል ለተፈጸመው የዘር ፍጅት ከዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች በአባልነት የሚገኙበት ገለልተኛ አጣሪ ኮሚሽን ተቋቊሞ ዕውነቱን የኢትዮጵያ እና የዓለም ማኅበረሰብ እንዲያውቅ ማድረግ፤ የአርቲስት ሐጫሉ ሑንዴሣን ገዳዮች ማንነት እና በግድያው ምክንያት የተፈፀመውን የዘር ፍጅት ያቀነባበሩ ቡድኖች እየነዙት ያለውን የሐሰት ፕሮፓጋንዳ ለነፋስ ለመስጠት ስለሚያስችል ይህን ኮሚሽን መንግሥት ፈጥኖ እንዲያቋቊም ጥሪያችን እናቀርባለን።
  2. መንግሥት በሕግና በሥርዓት እንጂ፣ በንግግርና በማስፈራራት አይመራም። በመሆኑም ላለፉት 30 ዓመታት በሕዝብ ላይ ግፍ የፈፀሙ፣ የዘር ፍጅት በዕቅድ ያከናወኑ፣ የአገርና የሕዝብ ሀብትና ንብረት የዘረፉና ያስዘረፉ ግለሰቦችና ቡድኖች ባስቸኳይ ለፍርድ  እንዲቀርቡ እንጠይቃለን።
  3. የብልጽግና ፓርቲ የኦሮሚያው ክንፍ፣ በኦነግ -ሼኔ ዓላማ አራማጆች የተሞላ ስለሆነ፣ የኢትዮጵያን አንድነት ተገዳዳሪ የሆኑት በፓርቲውና በመንግሥት ልዩ ልዩ መዋቅሮች ውስጥ ያሉት ግለሰቦች ተለይተው ለፍርድ እንዲቀርቡ እንጠይቃለን። በተመሳሳይ ሁኔታ በዐማራውና በሌሎች ክልሎች ያለው የብልጽግና ፓርርቲና የመንግሥት መዋቅርም በትሕነግ ዓላማ አራማጆች የተውተበተበ ስለሆነ፤ ባስቸኳይ የዕርምት እርምጃ ካልተወሰደ፤ የትሕነግ የወረራ ፍላጎት ከፕሮፓጋንዳ ወደ እውነት አይሸጋገርም ማለት አይቻልምና የፓርቲውና የመንግሥት መዋቅር ለኢትዮጵያ አንድነት በቆሙ ግለሰቦች እንዲያዝ እንዲደረግ እንጠይቃለን።
  4. መንግሥት የሚሰጣቸው መግለጫዎች ትክክልና የማይጣረሱ መሆናቸውን ማረጋገጥ ይጠበቅበታል። የሚወጡ መረጃዎች እርስ በእርሳቸው የሚቃረኑ ከሆነ፣ ሕዝቡ ዕውነቱን ለማወቅ ይቸገራል። ይህም ከጐኑ እንዳይቆም ያደርገዋል። ለምሳሌ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሰበሰቡት የደኅንነትና የፀጥታ ከፍተኛ አካሎች ስብሰባ ላይ የፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነሩ የሰጠው መረጃና የአገሪቱ ዋና ዐቃቢ ሕግ ኀላፊ የሆነቸው ወ/ሮ አዳነች አበቤ ፍፁም ተቃራኒዎች ናቸው። በፖሊስ ኮሚሽነሩ የቀረበው ሙያዊና በመረጃ የተደገፈ ሲሆን፣ በዐቃቢ ሕግ ኀላፊዋ የቀረበው ደግሞ ያለመረጃ በነገድና ተገዳዳሪ የፖለቲካ ድርጅት ጥላቻ ላይ የተመሠረተ እንደሆነ አድማጩ ታዝቧል። የወንጀል መነሻው የፖሊስ የምርመራ ውጤት መሆኑ እየታወቀ፤ ከፖሊስ መረጃው ውጪ የዐቃቢ ሕግ ኀላፊዋ አቶ እስክንድር ነጋንና ባልደራስን እንዲሁም ዐሥራት ቴሌቪዥንን ወንጀለኛ ያደረገችበት ሁኔታ ለአድማጩ ያስተላለፈው መልዕክት ሴትዮዋ የኦነግ ዓላማ አራማጅ መሆኑዋን ነው። ሌት ተቀን የዘር ፍጅት የሚቀሰቅሱትን ኦኤምኤንና ትግራይ ሜዲያ ሀውስ እያሉ፤ እነዚህን በቅድሚያ ከመጥራት ተቆጥባ፤ ቀድማ በጠላትነት የፈረጀችው ዐሥራት ቴሌቪዥን እና ባልደራስን ነው። ይህ አካሄድ የዘር ፍጅት የተፈጸመበትንና እየተፈጸመበት ያለውን ዐማራ የሚያገልና በፍትሕ አካላቱ ጭምር ኀላፊነት የተቀመጡ ሰዎች ፀረ-ዐማራ መሆናቸውን የሚያመላክት ስለሆነ፤ የባልደራስና የዐሥራት ቴሌቪዥን ክስ ከተፈፀመው ወንጀል ጋር ተያያዥነት አላቸው ብሎ ለማለት የሚያስችሉ መረጃዎች በእስካሁኑ ለሕዝብ አልቀረቡምና የመንግሥትን ታማኒነት እያረጋገጡ ለመሄድ፣ በነዚህ አካሎች ላይ የወሰደውን እርምጃ በፍጥነት መርምሮ ዕውነቱን ሕዝብ እንዲያውቀው እንዲያደርግ ጥሪ እናቀርባለን።
  5. ባሁኑ ሰዓት የኢትዮጵያ መንግሥት ከትሕነግ/ሕወሓትና ከኦነግ ሼኔ የከፋና የውጪ ኀይሎች መጠቀሚያ የሆነ ጠላት የለውም። ጠላትን ማሸነፍ የሚቻለውም ጠላትነቱን አውቆ በሚመጥነው መልኩ መዋጋት ሲቻል ነው። ይህ ዕውን እንዲሆንም እነዚህን ፀረ-ኢትዮጵያ ቡድኖች በአሸባሪነት በመፈረጅ መንግሥታዊ መዋቅሩና ሕዝቡ በግልጽ እንዲታገላቸው እንዲያደርግ እንጠይቃለን።
ተጨማሪ ያንብቡ:  ግሩም ጫላ ጋዜጠኝነትን መሸቀጫ ያደረገ የአብይ አህመድ ካድሬ

በውጪው ዓለም ለሚኖሩ የኢትዮጵያ አንድነት ፈላጊዎች፦

አገራችን ከምንጊዜውም በከፋ ሁኔታ ለግብፅ ጥቅም በቆሙ የኦነግ ሼኔና ትሕነግ/ሕወሓት ቅንጅታዊ ሤራ ወደ እማያባራ የእርስ በእርስ ጦርነት ሊከቷት ከፍተኛ ዝግጅት ላይ መሆናቸውን እየሰማንና እያየን ነው። ይህ ወቅት ከመቼውም ጊዜ በላይ የአንድነት ኃይሉን ትብብር ይጠይቃል። ስለሆነም፦

  1. በሰፊው እንደሚነገረው የኦነግ ሼኔና ትሕነግ አርቲስት ሐጫሉ ሑንዴሣን አስገድለው፣ በዚህ ሰበብ በኦሮሚያ ክልል ለፈፀሙት የዘር ፍጅት ተጠያቂ እንዳይሆኑ፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ የተያያዙትን ዘመቻ እንቅስቃሴ ለመግታትና  ዕውነቱን ለማሳዬት የተቀነባበረ ሠላማዊ ሰልፍ በየምንኖርባቸው ከተሞች እንድናደርግ ጥሪያችንን እናቀርባለን።
  2. ባሁኑ ወቅት ከፍተኛ የሆነ የሽብር እንቅስቃሴ በሚካሄድበት ጊዜ በዶ/ር ዐቢይ ላይ የተጀመረው ዘመቻ ኢትዮጵያን የመበታተን አካል ስለሆነ፣ ይህን ዘመቻ መመከት ኢትዮጵያዊነትን መታደግ ስለሆነ፤ በዚህ ላይ ያሉንን መለስተኛ ልዩነቶች አቻችለን ከመንግሥት ጐን ልንቆም ግድ የሚለን ሰዓት ላይ ነን። በዶ/ር ዐቢይ አስተዳደር የተከናወኑና እየተከናወኑ ያሉ ብዙ ስሕተቶች እንዳሉ ብንገነዘብም፤ ከስሜታዊነት ወጥተን ኢትዮጵያ እንደ ኢትዮጵያ እንድትቀጥል የሚያስችለውን አማራጭ መያዝ ዐዋቂነት ብቻ ሳይሆን ብልኅነት ነው።

ለዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ፦

ኢትዮጵያ ጥንታዊና ለረጅም ጊዜ የፀና መንግሥታዊ አደረጃጀት ያላት ከመሆኗም በላይ፤ የሰው ዘር ምንጭ (the Cradle of Humanity)እንደሆነች ይታወቃል። በዘመነ ቅኝ አገዛዝም ብቸኛ ነፃ አፍሪካዊት አገር ከመሆን አልፋ፤ የተባበሩ መንግሥታት ማኅበር (League of Nation) አባል እና ይህ ማኅበር በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ፈርሶ እርሱን የተካው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት(ተመድ) ሲመሠረት አሁንም ከሦስቱ የአፍሪካ ሀገሮች ውስጥ አንዷ መሥራች አገር ከመሆኗም በላይ  የተመድን መተዳደሪያ ደንብ በማርቀቅ ጉልህ ሚና መጫወቷ ይታወቃል። ባለመታደል አገሪቱ የተለያዩ የዓለም አመለካከቶች መፈተኛ በመሆኗ፤ ከሁሉም በላይ ላለፉት 29 ዓመታት አገሪቱን የመራው ኢሕአዴግ የሚባለው ድርጅት አገሪቱንና ሕዝቡን በነገድ ከፋፍሎ የዘረኝነት(አፓርታይድ) ሥርዓት በመዘርጋቱ ሆን ተብሎ በሚቀነቀን የዘር ጥላቻ የአገሪቱ አንድነት አደጋ ላይ ወድቋል። የችግሩ መንስዔም የአገሪቱ ሕገመንግሥት የግለሰብንና የዜጋን ማንነት የሚፃረር፣ በአንፃሩ በነገድ ላይ መመሥረቱ ነው። ይህ አብሮነትንና አንድነትን ሳይሆን፣ መነጠልንና መለያየትን የሚያራምድ ሕገመንግሥትና መንግሥታዊ አደረጃጀት ከ85 በላይ  ነገዶች የሚኖሩባትን አገር በማንነታቸው፣ በደንበር፣ በግጦሽ መሬት፣ በውኃ ወዘተ በመሳሰሉት መብትና ጥቅሞች ተፃራሪ ሆነው እንዲቆሙ በማድረግ፤ ላለፉት 29 ዓመታት ከፍተኛ የሆነ የሰዎች ዕልቂት፣ መፈናቀል፣ መሰደድና መቸገር  የሕዝቡ የዕለት ተዕለት ኑሮ መገለጫ  ሆኖ ዘልቋል።

ይህ በልዩነት ላይ የተመሠረተ የመንግሥት አደረጃጀትም ያለፉት ዓመታት ቀጣይና ተያያዥ የሆነ ሰሞኑን ኦሮሚያ በሚባለው ክልል በኦነግ ሼኔና በትሕነግ/ሕወሓት ትብብር ማንነትን መሠረት ያደረገ የዘር ፍጅት እንዲፈጸም ምክንያት ሆኗል። ዝዋይ፣ ሻሻመኔ፣ አርሲ ነገሌ፣ አዳሚቱሉ፣ ባሌ፣ ሐረርጌ፣ ወዘተ በሚኖሩ ዐማሮች፣ ጒራጌዎች፤ ሐዲያዎች፣ ጋሞዎችና ክርስቲያኖች ላይ ከፍተኛ የሆነ የሰው ግድያና የንብረት ውድመት በታቀደ መልኩ እንዲፈፀም ሆኗል። ይህ የዘር ዕልቂት እንዳይቀጥል፣ ፍጅት የፈፀሙ አካሎችም ለፍትሕ እንዲቀርቡ ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ለሚከተሉት ጉዳዮች ትኩረት ሰጥቶ የሰው ዘር መገኛና ጥንታዊት የሆነችው ኢትዮጵያን እንዲታደጋት በሰው ዘር ስም ጥያቄ ስናቀርብ በማክበር ነው፦

  1. በኦሮሚያ ክልል የተፈፀመውን የዘር ፍጅት በገለልተኛ አካል ተጣርቶ ዕውነቱ እንዲታወቅ አስፈላጊውን ዲፕሎማሲያዊ ግፊት እንዲያገርግ፤
  2. ታዋቂውን የኦሮሞኛ ቋንቋ አቀንቃኝ አርቲስት ሐጫሉ ሑንዴሣን የገደሉና ያስገደሉ አካሎች ከወንጀላቸው ነፃ ለመሆን የያዙት ፀረ መንግሥት ቅስቀሳና ሰልፍ ፍትሕን እንዳያዛባ ትክክለኛውን ለመረዳት ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ የራሱን እውነት ከሐሰቱ የሚለይበትን መንገድ እንዲከተል፤
  3. ወንጀሉ የተፈጸመባቸው ቦታዎችና አካባቢዎች ለዓለም አቀፉ የሰብአዊ መብት ጥበቃ ድርጅት እንዲከፈትና ምርመራ እንዲደረግ አስፈላጊውን ሕጋዊና ተገቢ የሆኑ ሥራዎች እንዲሠሩ እንጠይቃለን!

ዐማራው በማንነቱና በእምነቱ ላይ ያነጣጠረውን የዘር ዕልቂት  በአንድነቱ ይመክታል!

የኢትዮጵያ አንድነት በሐቀኛ ልጆቹዋ ተገቢ መሥዋዕትነት ይከበራል!

ኦሮሞና ትግሬ ባልሆኑ ኢትዮጵያውያን ላይ ያነጣጠረውን የዘር ፍጂት በተቀነባበረ ሕዝባዊ ትግል እንመክታለን!

ድል ለኢትዮጵያ!

2 Comments

  1. “«ጅቡ ከሚበላህ በልተኸው ተቀደስ» እንዲሉ፣ በሥልጣን ላይ ያለውን መንግሥት ከነችግሮቹ መደገፍ፤ ኢትዮጵያን ከጥፋት የመታደግ ትልቁን ሥዕል መመልከት መሆኑን መገንዘብ እጅግ ተገቢ ነው ።“ ግሩም እይታ ነው!

    ችግሩ ግልፅ ነው:: ጎራ ለይቷል:: ባንዳው ወያኔ ከተላላኪው ኦነግ ሸኔ ጋር ተጣምሮ ኢትዮጵያን ለማፍረት ጦርነት አውጇል:: እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ትርክምርኪ ፖለቲካውን ለነገ አሳድሮ ከዐቢይ የኢትዮጵያ ፌዴራል መንግስት ጋር ይቁም:: ይህ የአማራም ኦሮሞም ትግሬና ሱማሌና አፋር የሁሉም ኢትዮጵያዊ በአንድነት የሚቆሙበት ወቅት ነው::

  2. Relaying on PM Abiy who is surrounded himself with protestant oromo officials, who hated Ethiopia and Orthodox church to their bone, is like putting all your eggs in one basket. Well, I will give him some percentage. But Amara should have plan B, and fast. TPLF, I heard is armed with modern weapons all to kill Amaras. Oromo region was training hundreds of thousands of special forces (who may be participated in the genocide) while PM Abiy accused Amara region spending some budget to train 200 personnel. At this moment, the most important thing to do is to arm Amaras or prepare to arm one way or the other to defend themselves from all directions. This is particularly important to save the country too. Based on TPLF plan, the genocide we witnessed is the tip of the iceberg. Trusting international community to save us from genocide is like “ lam alegn besemay”. While working with PM Abiy, please has plan B too. AS we know, the primary target of TPLF, OLF and Egypt is the Amaras. Arm Amaras and save Ethiopia. A well-articulated petition and demonstration by a well-educated intellectual coward Amaras cannot save Amaras.

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share