በውኑ የጠላቴ ጠላት ወዳጄ ነውን? – ሰሎሞን ጌጡ

“የጠላቴ ጠላት ወዳጄ ነው” የሚለውን አባባል ብዙዎቻችን እናውቀዋለን : ምናልባትም እንኖረዋለን። ይህ አባባል ከክርስቶስ ልደት በፊት በ 4ኛው ዓ.ዓ ለመጀመሪያ ግዜ በፅሁፍ ደረጃ ጥቅም ላይ እንደዋለ ይታመናል። ይህ አባባል ተራ አባባል ሳይሆን : የግለሰቦችን፣ የማህበረሰቦችን እንዲሁም የሀገራትን የእርስ በእርስ ግንኙነት ልንመረምርበት የምንችልበት ሀሳብ ጭምር ነው። የማህበረሰብ ጥናት ተመራማሪው Fritz Heider በ1946  Social Balance በሚለው ንድፈ ሀሳቡ “ የጠላት ጠላት ወዳጅ ነው : የጠላት ወዳጅ ደግሞ ጠላት ነው” በሚል መነሻ ሀሳብ የማህበረሰብ ቡድኖችን የእርስ በእርስ ግንኙነት በመተንተን የሀሳቡን ቅቡልነት በራሱ መንገድ ለማስረዳት ሞክሮ ነበር። በእርግጥ ከታሪክ ማህደርም ስንመለከት ሀሳቡን በመቀበልና በመተግበር የተጠቀሙበትም : ብሎም የተጎዱበትም ነበሩ። እንደ ምሳሌ ለመጥቀስ ያህል በሁለተኛው የአለም ጦርነት ወቅት አሜሪካ እና እንግሊዝ በአይዲዮሎጂ በፍፁም ከማይመስላቸው ክሶሻሊስቱ ሶቪየት ህብረት ጋር ጥምረት በመፍጠር የጋራ ጠላታቸውን መስበር የቻሉት ይህንኑ ሀሳብ በመቀበል ነው። ለመጠፋፋት ሚፈላለጉት የቻይናው ኮሚኒስት እና ናሽናሊስት ፓርቲም በጃፓን ወረራ ጊዜ በማስተዋል ህብረት በመፍጠራቸው ነው ሀገራቸውን ከጥፋት የታደጉት። ታላቁ አፄ እምዬ ሚኒሊክም አድዋ ላይ የጥቁሮች ሁሉ ድል የሆነውን ታሪክ የሰሩት በብልህነት የጣልያን ጠላት ከሆኑት ሀገራት ባገኙት የመሳርያና የዲፕሎማሲ ድጋፍ ጭምር እንደሆነ ልብ ይሏል። በእርግጥ የአፄ ሚኒሊክ ብልህነት የተለየ በመሆኑ ከጠላት ወዳጅ ሀገራት አረ ከራሱ ጣልያን ጭምር በጊዜ ድጋፎችን አሰባስበው ነበር።

ይህ የጠላቴ ጣላት ወዳጄ ነው የሚለው ሀሳብ ግን በእርግጥ የሚሰራው እና ስኬትን ሊያመጣ የሚችለው ለተመረጡ ወዳጅ እና ጠላቶቻቸውን በግልብ ስሜት ሳይሆን በሚገባ አብጠርጥረው በሚረዱ ብልህ መሪዋች/ቡድኖች ነው። ይህን ሀሳብ እንደወረደ በመጠቀማቸው እና ወዳጅ ጠላቶቻቸውን በእርግጥ ባለማወቃቸው ብቻ የስህተት እና የሽንፈት ታሪክ ታቅፈው የቀሩ ሀይሎች ቁጥራቸው ቀላል አይደለም። ለዚህ ጥሩ ምሳሌ የሚሆነን የመኢሶን-ኢህአፓ ታሪክ ነው : መኢሶን ከኢህአፓ ጋር የነበረውን ሽኩቻ በድል ለመወጣት በሚል ብቻ የራሱ ዘላቂ ጠላት ከሆነው ደርግ ጋር በማበር ለእርስ በእርስ መጠፋፋቱ የራሱን ሚና በመወጣት በኢትዮጵያ ውስጥ የከሸፈ ታሪክ እንዲመዘገብ ሆኗል።

በእርግጥ የጠላቴ ጠላት ወዳጄ ነውን? ከማይመስሉን ቡድኖች እና ሀገራት ጋር ያላቻ ጋብቻ ከመፍጠራችን በፊት ይህንን ጥያቄ በእርግጥ በደንብ ልንመረምረው እና መልስ ልናገኝለት ይገባል። የFritz Heider ን ሀሳብ ተቀብሎ በግብታዊነት ለትግበራ ከመገስገስ በፊት ቆም ብሎ ዘላቂ ወዳጄ : ዘላቂስ ጠላቴ  ማነው፣ ከየትኛው ሀይል ጋር ማበር ዘላቂ የጋራ ጥቅም እንደ ሀገር ያስገኝልናል የሚለውን ሀሳብ አስቀድሞ መመርመር እና ለጥያቄዋቹም ተገቢ መልስ ማግኘት ያሻል።

በጣም የሚያሳዝነው አሁንም በሀገራችን ከዚህ የክሽፈት አዙሪት ውስጥ መውጣት አለመቻላችን ነው። ጠላት ወዳጅአቸውን በውል ያለዩ በክሽፈት አዙሪት የተለከፋ ሀገራችንን ለማፍረስ ቁልቁል የሚንደረደሩ ሀይሎች እና በስሜት የሚጋለቡ ወጣቶች ዛሬም አሉን።

እኛስ እንላለን : በምን መስፈርት ህወአት እና ኦነግ ሸኔ ከግብፅ ጋር በማበር ለጊዜአዊ ጥቅም ሲሉ ኢትዮጵያን እና ኢትዮጵያውያንን ለማጥፋት ተነሱ? በውኑ ግብፅ ለህወአት እና ኦነግ ሸኔ ወዳጅ ሆና ነው? ወይስ የከሸፈ ታሪክ ለመድገም ነው? በእርግጥ ባንዳ ድሮም ነበር አሁንም ይኖራል። በውኑ ህወአት እና ኦነግ ሸኔ በባንዳነት ሊፈረጁ እና ከወጣቱ አይምሮ ውስጥ ሊፋቁ እና ሳያጠፋን ታሪክ ልናረጋቸው የሚገቡን እንግዴዋች ናቸው። የትግራይ ህዝብም ከጉያው የወጡትን የወያኔ ባንዳዋች በመቆንጠጥ እና አሳልፎ በመስጠት እንደ ሁል ግዜ የኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያውነት ጠበቃ መሆኑን የሚያስመሰክርበት የታሪክ ምዕራፍ ላይ ነው ያለነው።

በምንስ መስፈርት ቤተክርስቲያን በጠላትነት ትፈረጃለች? ለምንስ ትቃጠላለች? ለአገር ሰላም እና አንድነት ስለፀለይች ወይስ ጠላትን ምንመክትበትን ያለመከፋፈል በሰላም እና በህብረት የምንኖርበትን የድል አድራጊነት ስሜት የሆነውን ኢትዮጵያዊነትን ስላጠናከረችልን። ቢገባን እና ጠላት ወዳጆቻችንን በቅጡ ብንለይ ኖሮ ኢትዮጵያውነት ለገሌ ብሔር ሳይሆን ለሁሉም ብሔር ብሔረሰቦች : ለሁሉም ኢትዮጵያውያን የሰላም፣ የአንድነት እና የብልፅግና ዋስትና ነበር። ሂትለራዊ እባጭ በጀርባቸው ተሸክመው በፋሺስታዊ/ኦሮሞ ብቻ ቅኝት የሚያምኑት ኦነግ ሸኔ እና ወዳጅ ጠላቱን በቅጡ ለይቶ ሳያውቅ በግብታዊነት የሚከተለው ጥቂት የኦሮሞ ወጣት የሰጡንን ዋስትናማ ይኸው እያየነው ነው : የዘር ማጥፋት እና የእርስ በእርስ የመጠፋፋት አደጋ ዋስትና ¡ በኦሮምያ ክልል እና በአዲስ አበባ የዚሁ የከሸፈ የታሪክ አዙሪት ሰለባ በሆኑ ኢትዮጵያውያን ወገኖቼ እልቂት የተሰማኝን መሪር ሀዘን በዚሁ አጋጣሚ ለመግለፅ እወዳለው : ነፍስ ይማር!!! ልንደርስላቸው አለመቻላችን ልብን ያደማል : በእርግጥ ለቀሪዋቹ ግን በዘላቂነት ዋስትና ልንሆናቸው ይገባል!

በምንስ መስፈርት ነው ለአገሩ አንድነትና መከበር አጥንቱን በይክፍላተ ሀገራቱ የዘራው ደሙን በየቦታው ያፈሰሰው ነፍጠኛ : ለኦሮሞ ወጣት ጠላት የሚሆነው : ይህ ወዳጅ እና ጠላትን ለይቶ አለማወቅ/መታወር ወይም የክሽፈት ታሪክ አዙሪት ካልሆነ በስተቀር ሌላ ምን ሊሆን ይችላል? ዉሸት ሲበዛ እውነት ይመስላል እንዲሉ: ህወአት ለ 27 አመታት በየዋሀው እና ቅኑ የኦሮሞ ወጣት ጭንቅላት ውስጥ የዘራችው የውሸት ገዳይ ተገዳይ ትርክት ለዚህ የሀሰት ፍረጃ እና የመጠፋፋት አደጋ አድርሶናል። በፍጥነት መርዙን ማክሸፍ ይኖርብናል : አዋ ነፍጠኛው የኦሮሞ ወዳጅ እንጂ ጠላት እንዳልሆነ : ፋሺስታዊ ዘረኝነት ለራሱ ለኦሮሞ ወጣትም የህልውና አደጋ እና አሳፋሪ እና አስነዋሪ የሰውነትን እና አለማቀፍ ህጎችን የሚጥስ የክሽፈት አዙሪት/ ተላላፊ በሽታ እንደሆነ አሁንም ደግመን ደጋግመን መንገር ማስረዳት ሀሰቱን በእውነት መሸፈን፣ መርዙንም ማርክስ ይኖርብናል። ይሰሙናልም ብለን እናምናለን : ለዚህም ተግተን እንፀልያለን። የማይሰሙትን እና በእኔ ብቻ ልብላው በፋሺስታዊ የዘረኝነት በሽታ የተለከፋትን ደግሞ በአግሪቷ ህግ እና በአለም አቀፍ ህግ መሰረት መፋረድ እና በጥባጩን ከበረት ውስጥ ማስወገድ በየትኛውም መስፈርት ተቀባይነት ያለው ቀጣይ እርምጃ ነው። በውኑ ከ ሀገር ሰላም እና አንድነት በላይ ምን አለ?

በምን መስፈርት ነው እውነት ከሀሰት ጋር ፣ ተበዳይ ከበዳይ ጋር ፣ ብርሀን ከጨለማ ጋር ፣ ተስፋ ከጥፋት ጋር ፣ የጋራ ተጠቃሚነትን መሰረት ያደረገ ኢትዮጵያዊነት ከፋሺስታዊ ኦሮሞነት ፣ እስክንድር ከጀዋር ጋር በአንድ መስፈሪያ የሚሰፈሩት። እኛስ እንላለን እውነት ብቻ ከዘላቂ ጥፋት ይታደገናል : ቁጣ ለማብረድና አንዱን ቅር ላለማሰኘት እየተባለ ግን ወንጀለኛውን ከንፁህ መደባለቅ በቀጣይነትም ንፁኹን ሰለባ የሚያደርግ እና ወንጀለኛውንም በወንጀሉ እንዲገፋበት የሚያደርግ የስህተት መንገድ ነው። እውነትን ይዞ ቁጣን/ፈተናን መጋፈጥ እውነተኛው የስኬት መንገድ ነውና አስተዳደሩ ሊታረም ይገባል ብለን እናምናለን።

ፍሬ መልክቴ :-ካዙሪት እንውጣ የከሸፈ ታሪክ እንዳንደግም እንጠንቀቅ፣ በተለይ ወጣቱ እውነተኛውን ወዳጅህን እና የወዳጅ ለምድ የለበሰ ጠላትን በቅጡ ለይ ፣ እውነትን አቅፎ መተኛት ከጥፋት አያድንም: በጣም በተደጋጋሚ እና በተለያዩ አጋጣሚዋች በመጮህ እውነቱን ለአለም ልናሳውቅ ፣ ውሸቱን አደባባይ ልናሰጣው እና የታወሩትንም አይናቸውን ልንገልጥላቸው ይገባል።

 

ይቆየን

ሰሎሞን ጌጡ

ኑርምበርግ 05.07.20

1 Comment

  1. ሰሎሞን ከሚሉህ አቃጣሪ ቢሉህ ይሻል ነበር ወደድክም ጠላህም ግድቡ ከነ ብዙ ችግሮቹ አስጀምሮ እስከ 66% ያደረሰው ህወሀት ነው ምነው አሁን ባንዳ ተባለ የአንተው ባንዳ አብይ አይደለም እንዴ ወላሂ ወላሂ ብሎ ካይሮ ሂዶ ሽጦት የመጣ አረ ተው እውነት ተናገሩ፡፡ ያኔ ሲጀመር አንተ አና አቃጣሪዎችህ ግድቡ መገንባት የለበትም ስትል የነበረው

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Previous Story

የከርሞ ሰው በለን (ዘ-ጌርሣም)

i bewketus social commentar
Next Story

ደም አፍሳሾች እና ደም አፍይዎች I Bewketu’s Social commentary

Latest from Blog

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤ/ክ የውጪ ግንኙነት የቤተክርስቲያኒቱን የሺሕ ዘመናት ታሪክ እና እሤቶቿን የሚመጥን መሆን ይኖርባታል!!

በተረፈ ወርቁ (ዲ/ን) (ለሪፖርተር ጋዜጣ እንደጻፈው) እንደመንደርደሪያ ለዛሬው የግል ትዝብቴንና ታሪክን ላዛነቀው ጽሑፌ መነሻ የሆነኝ- ባሳለፍነው ሳምንት በአፍሪካ ኅብረት ኔልሰን ማንዴላ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ለአንድ ቀን የተካሄደው፤ ‹‹የአፍሪካ  መንፈሳዊ ቀን/The African Spiritual

የአበባው ታደሰ እና የአረጋ ከበደ ፍርጠጣ | ስለአማራ ክልል ከነዋሪዎች የተሰማው | አበባው ጉ’ድ ሆነ – “አበባውን ሳትይዙ እንዳትመጡ”|“በባህርዳር ተከበናል፣ ከፍተኛ አዛዦች ተመተዋል” | “ፋኖ መንግ’ስት ሆኗል” ጄ/ሉ |

የአበባው ታደሰ እና የአረጋ ከበደ ፍርጠጣ አበባው ጉ’ድ ሆነ – “አበባውን ሳትይዙ እንዳትመጡ”|“በባህርዳር ተከበናል፣ ከፍተኛ አዛዦች ተመተዋል”| “እጅ ከመስጠት ውጭ አማራጭ አይኖረንም” ፊ/ማ “ፋኖ መንግ’ስት ሆኗል” ጄ/ሉ |
Go toTop