የበለፀጉት ሀገሮች አፍሪካን የበለጠ ደሃ ለማድረግ ለምን ይጥራሉ? – መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ 

መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ
የበለፀጉት ሀገሮች አፍሪካን የበለጠ ደሃ ለማድረግ ለምን ይጥራሉ?ከዳያቢሎሥ ጋራ የሚመሳሰሉ አለቆች ሥላላቸው ነውን?!( ቫይረሱም መድሃኒቱም በእጃቸው መሆኑን ሥታዩ ይህንን ድምዳሜ አትቀበሉምን?
 ”  ሂድ አንተ ዲያቢሎስ !” ብለን በፍቅር ተባብረን ለመበልፀግ እሥካልተነሣን ድረሥ አፍሪካውያን የመላአክትን አገልግሎት አናገኝም።
  ይህ ኃይማኖታዊ ቅስቀሳ ይመሥላል።ነገር ግን አይደለም።ከዚህ በፊት እንደፃፍኩት ክፉና መልካምን የማያመዛዝን፣በጭፍን የሚጎዝ፣ስሜታዊ ሰው በበዛበት ሀገር እና ድህነት አንገቱን በሰነገው ህዝብ በሞላባት አፍሪካ በቀላሉ እድገትና ብልፅግና ማምጣት ስለማይቻል፣ጠንካራ እሴቶቻችንን የሚያጎለብት የባህል አብዮት ያሥፈልገናል።
    በዚህም የባህል አብዮት ዳቢሎሥን መካድ እና በህሊናችነ ፍቅርን ማንገሥ እንችላለን።
 ይህ ብቻ ነው የሀገራችን እና የአህጉሪቱ መፍትሄ።
 ልብን ነው ማየት
ሁለትም ሦሥትም
ሠባትም ሥምንትም
ዘጠኝም አሥርም…
ሆናችሁ ሥትሠበሰቡ…
ከእናንተ መካከል
አንደኛው ይሁዳ
መሆኑን አሥቡ።
 መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ
ጥር 23/5/2012
  8.  ደግሞ ዲያብሎስ እጅግ ረጅም ወደ ሆነ ተራራ ወሰደው፥ የዓለምንም መንግሥታት ሁሉ ክብራቸውንም አሳይቶ፦
 9. ወድቀህ ብትሰግድልኝ ይህን ሁሉ እሰጥሃለሁ አለው።
 10. ያን ጊዜ ኢየሱስ፦ ሂድ፥ አንተ ሰይጣን ለጌታህ ለአምላክህ ስገድ እርሱንም ብቻ አምልክ ተብሎ ተጽፎአልና አለው።
 11. ያን ጊዜ ዲያብሎስ ተወው፥ እነሆም፥ መላእክት ቀርበው ያገለግሉት ነበር።
                     የማቲዎስ ወንጌል ም/4:8-11
     የበለፀጉ ሀገራት ውስጥ የሚኖሩ በቁሥ ሰቀቀን የተለከፉ ፣አምላካቸው ገንዘብ የሆነ የሤጣን አገልጋይ የሆኑ፣ አንድ ፐርሰንት የሆኑ ሀብታሞች የዚች ዓለም ባለቤቶች እንደሆኑ በመፀሐፍ ቅዱስ ተመልክቷል።ከላይ ባሥቀመጥኩት ጥቅስ።
   አፍሪካውያን የመላአክትን አገልግሎት አግኝተው እንዳይበለፅጉ፣ሁሌም በድህነት ተኮራምተው በመኖር አምላካቸውን እንዲያማርሩ ማድረግም ሥራቸው ነው።
  መንግሥታቶቻቸውም   ለሃያላኑ የአውሮፖ መንግሥታት እና ለፊት አውራሪዋ አሜሪካ እንዲሰግዱ እጃቸውን መጠምዘዝ የለመዱት ተግባር ነው።
     እነዚህ ቢሊዮነሮች  የሚዘውሯቸው የአውሮፓ መንግሥታት፣ የአፍሪካ መንግሥታት ለእነሱ ሰግደው በሀገሬ እንዳሻችሁ ፈንጥዙበት እስካላሏቸው ጊዜ ድረስ ፣አህጉሪቱን የደም ምድር ለማድረግ የማይሸሩበት ሴራ፣የማይፈነቅሉት ድንጋይ የለም።  የእነሱን ጥቅም ለማሥጠበቅ የሚቆም መንግሥት በእያንዳንዱ አፍሪካ ሀገር እንዲኖርም አበክረው ይሰራሉ። የነሱን ጥቅም የማያሥጠብቅ   ሀገር ህዝብ በሰላም እንዲኖር  አይፈቀዱለትም።
   በእያንዳንዱ የአፍሪካ ሀገር ሲያሥፈልግ የሚያፈነዱት የጥላቻ ፈንጂ በመቅበራቸው ምክንያትም፣ህዝቡ እርስ በእርሱ ተዋዶና ተፋቅሮ ለመኖር በሚያደርገው ጥረት ላይ ሁሌም ጥላቻን ሲጭሩ ይስተዋላሉ።በጫሩት ጥላቻ ምክንያትም የተገነባው ሁሉ ይፈርሳል።ንብረት ይወድማል።የእድገት እና የብልፅግና ጅምር ከአፈር ጋር ይደባለቃል።…የትላንትና ቅኝ ገዢዎቻችን፣ ህልምም ይሳካል።
    የአፍሪካውያንን ዕድገት፣ልማት ና ብልፅግና የትላንት ቅኝ ገዢዎቻችን ከቶም አይፈልጉም ። ቢፈልጉ ኖሮ ትላንት በቅኝ ግዛት ዛሬ ደግሞ ” በእጅ አዙር ቅኝ አገዛዝ ” በአፍሪካ ጠንካራ መንግሥት እንዳይኖር በተለያየ መንገድ ሢጥሩ አይሥተዋሉም ነበር።
    የአውሮፓና የአሜሪካ ፣መንግሥታት ድርጊታቸው እንደሚያሳብቀው ፣የአፍሪካ ህዝቦች ፣ከእንቅልፋቸው ነቅተው፣”ድር ቢያብር አንበሣን ያሥር”በማለት እጅ ለእጅ በመያያዝ በፍቅር ተዋደው፣ በህብረት ሠርተው  በልፀገው ማየት  ከቶም አይፈልጉም።
     ይህንንም ለማረጋገጥ፣አውሮፓውያን፣እጅና እጅ ሆነው፣በመከባበር  በ፣ የአፍሪካን  ህዝብ በባሪያ ንግድ በወርቅ እና በሸቀጥ እየለወጡ እንዴት  እንደከበሩበት እና የሲዊዝ ካናልን ከፍተው ጥሬ ሀብቱን እያጋዙ እንደወሰዱ ከታሪክ መገንዘብ ይቻላል።
   አውሮፓውያኑ አፍሪካን ለመቀራመት በሚያደርጉት መሯሯጥ በመካከላቸው ያለመግባባት በመፈጠሩ በበርሊን
 በ1884  ፣እንግሊዝ፣ጀርመን፣ስፔን፣ፖርቹጋል፣ፈረንሳይ እና ኢጣሊያ አፍሪካን በሥርዓት ለመቀራመት  ኮንፍረንስ ማድረጋቸው እና ሥምምነት ላይ መድረሳቸውን ሥናሥተውል በጋራ ተጠቃሚ በሚያደርጋቸው ጉዳይ ላይ በመሥማማት ዘላቂ ጥቅማቸውን እንጂ ዋናው በዝባዥ ማንም ቢሆን ደንታ እንደሌላቸው ያሳየናል ።
    በዛ በ1884 የበርሊን የቅኝ ገዢዎች ሥምምነት እንግሊዝ ግብፅን በቅኝ ግዛትነት ይዛ እንድትቀመጥ መወሰኑ ይታወቃል። ግብፅ ከእንግሊዝ  ቀጥታ አገዛዝ በ1922 ነፃ ብትወጣም ከእንግሊዝ ና ከአሜሪካ ጥገኝነት ዛሬም አልተላቀቀችም።ሲውስ ካናል እያለም አትፋታም።
    በ1750 በይፋ የጀመረው የቅኝ አገዛዝ ከ1922 ጀምሮ    እያከተመ መጥቶ ፣ሌሎች የሰሜን የደቡብ፣የምሥራቅ እና የምእራብ  አፍሪካ ሀገራት ነፃ ሀገርነታቸውን በየተራ ቢቀዳጁም ፣በአንድ በምእራብ አፍሪካ ሀገር ብቻ ቅኝ አገዛዝ   አልተወገደም ነበር።
   እንደ ጎርጎሮሳዊያን ካሌደር በ1980  ምዕራብ ሮዴሽያ ” ብለው እንጊሊዞች በባለቤትነት  ሲያሥተዳድሯት የነበረችውን  ጥቁር አፍሪካዊት ሀገር፣አፍሪካውያን  በተባበረ ትግል ነፃ አውጥተው፣ “ዚምባቡዬ” ተሰኝታ ነፃ አገር እንድትሆን እሥካስቻሏት ጊዜ ድረስ  …
    ዛሬም፣ የአውሮፓና አሜሪካ ሀገራት፣  ዓለምን እየመሩ ካሉት አንድ ፐርሰንት ሀብታሞቻቸው ጋር ሆነው ፣በአንድም በሌላ መንገድ ብዙም ሳይለፉ ጥቅም የሚያጉኙት ከደሃ ሀገሮች ነው።
    የአፍሪካ ሀገራትን ደሃ ያደረጉት እነሱ ናቸው።ዛሬም  ድሃ ሀገሮች የበለጠ ደሃ እንዲሆኑ አንበጣ እንዲበዛ ያደርጋሉ እንጂ አንበጣ እንዲጠፋ አይፈልጉም።የወባ በሽታ እንዲሥፋፋ እንጂ፣የወባ በሽታ እንዲጠፋ  እውቀታቸውን አይለግሱም።በድሆቹ ሀገራት የእርስ በእርስ ጦርነት እንዲሥፋፋ እንጂ ሰላም እንዲፈጠር አይተባበሩም። ሁሉም እንጀራ ሠርቶ እንዲበላ  ከመደጉፍ ይልቅ ሥራ አጥነት እንዲባባሥ ወጣቱ በሱሥ እንዲጠመድ በተለያየ መንገድ ይገፋፉታል እንጂ በሰብአዊነት የተሞላ ድጋፍ አያደርጉም። ሥርአተ አልበኝነት እንዲሥፋፋ፣ይጥራሉ እንጂ በዓለም ላይ ጠንካራ ዲሲፕሊን እንዲኖር እገዛ አያደርጉም።…ዴሞክራሲ እና ፍትህ እንዲሠፍን እውቀት እንዲሥፋፋም  አይሹም።
   የሀገራቸውን በር ለብዝበዛቸው  ወለል አድርገው ያልከፈቱላቸውን፣ኢራን ፣አፍጋኒሥታን እና ሰሜን ኮርያን ዛሬም እንዴት እያደረጓቸው እንደሆነ ታሥተውላላችሁ። ሥለሶርያ ደግሞ፣ በሀገራችን ዋና ከተሞች ናዝሬትን ጨምሮ የሚለምኑትን የሶሪያ  ዜጎችን ምሥክር ማድረግ ይቻላል።
   በአንድ ፐርሰንቶቹ ለሚሙሩት ቱጃሮች  ሁሉም ነገር ቢዝነስ ነው።ንግድ ነው።ያውም ሥንጥቅ ትርፍ የሚያሥገኝ ንግድ።በሀብት ላይ ሀብት የሚከምር ንግድ።
  እናም አፍሪካ ትላንትም ሆነ ዛሬ የአውሮፓውያኑም ሆነ የታላቋ አሜሪካ የንግድ መነሃሪያ ናት።
    ጥንትም ሆነ ዛሬ የኃያላኑ ሀገራት መሪዎች፣ አፍሪካን የመበልፀጊያ መሣሪያ ሲያደርጓት እንጂ ሲያበለፅጓት አልታዩም።የአፋሪካን ህዝብ ሳይሆን በከርሰ ምድሯ እና በገፆ የያዘችውን ኃብት ነው የሚፈልጉት።በተፈጥሮ ሀብቷ ለመክበር እንጂ ህዝቡ እንዲነቃ እና እንደነሱ ሥልጡን እንዲሆን አይሹም።
    የነሱ ልብ ያለው ሁሌም፣በአፍሪካ ውብ ተፈጥሮ ላይ እንጂ በሥልጣኔዋ ላይ አይደለም።እንዴት አድርገው በናጠጠ  ሀብት፣በብልፅግና  ፣በድሎት እና በምቾት ህይወታቸው ላይ ተጨማሪ “መሞላቀቅ” የሚፈጥርላቸውን ፣ወርቅ ፣አልማዝና ፣መአድን ወደሀገራቸው እንደሚያግዙ ነው፣ዘወትር የሚያሥቡት።
      መሞላቀቃቸውን ዘላቂ ለማድረግም አፍሪካን ሥልጣኔ አልባ ማድረግ እንደሚያሥፈልግም ያምናሉ።የአፍሪካ መንግሥታትም የጠራ ህልም እና ግብ እንዳይኖራቸው ያደርጋሉ።የሞግዚት አሥተዳደርንም ይፈጥራሉ።የጎሣ እና የዘር ክፍፍልን ይዘራሉ።ይተክላሉ።እየተንከባከቡም ያሳድጋሉ። መከራውን እኛ እናጭዳለን።
እንሆ የብዝበዛ  ሥልታቸውንም በሦሥት መንገድ ይዘረጋሉ።
  1ኛ / ከፍተኛ እርዳታ እና ብድር በመሥጠት ወዳጅ መሥሎ በመቅረብ
   2ኛ/ እርዳታውን ተቀብሎ እነሱን ተጠቃሚ የማያደርግ ተግባራትን የማያከናውን እና በሩን ለብዝበዛ የማይበረግደውን ፣መንግሥት ከሥልጣኑ በተለያየ ዘዴ ማውረድ። አልያም ተረጋግቶ ሠርቶ ሀገሩን እንዳያበለፅግ ፣በተለያዩ ጥቅማ ጥቅሞችና እና ተሥፋ በመሙላት ፣ከሥልጣኑ የሚያወርደውን ጠላትእዛና እዚህ  መፍጠር።
3ኛ/ በርእዮት ፣በህግ እና በጠንካራ መንግሥታዊ ተቋም የሚመራ፣   መንግሥት በአፍሪካ ከተፈጠረ፣ ያጠንካራ ኩሩ መንግሥት  እንዲዳከም፣እሥከነ  አካቴው ምንም ዓይነት ድጋፍና እርዳታ እንዳይደረግለት ማድረግ።….
   ይኸው ነው።  ኃያላኑ አውሮፓውያን፣የአፍሪካን እድገትና ብልፅግና  አይሹም። እድግታቸውን አይፈልጉም። በምሥጢር ተቀናቃኞቻቸውን በማሠልጠን፣ በፋይናሥ እና በሎጀሥቲክ በመደገፍ በየበረሃው ፣ ጫካው ባሥ ሲልም  በየከተሞች እንደሩዋንዳ የእርስ በእርስ እልቂትን የሚፈጥሩትም በቀጥታ እነሱ ተጠቃሚ እንዲሆኑ በመፈለግ ነው። …
  ተጠቃሚነታቸውን ለማጠናከር ወይም ሥውር ብዝበዛቸውን አሥተማማኝ ለማድረግ፣   የዘር፣የቋንቋ እና የኃይማኖት ግጭቶችን በሥተጀርባ ሆነው ይፈጥራሉ።… ለዚህ ውጥናቸው ሥኬትም፣ለሆዳቸው ያደሩ የገዛ ሀገራቸውን በዶላር የማሸጡ ተባባሪ አያጡም። አልበዘበዝም   ባለችው ሀገር  እነዚህን የተማሩ ሰዎች አሠልጥነው ያሰማራሉ።
   …..   የጦር መሣሪያዎች በኮንትሮባንድ መልክ በገፍ ወደሀገሪቱ እንዲገቡ በማድረግ፣የሀገሪቱ መንግሥት ባለው ኃብት ተረጋግቶ ሀገርን እንዳያበለፅግም ያደርጋሉ ።
    ይህንን ሤጣናዊ ግብራቸውን ግን ፣ብዙዎቻችን የአፍሪካ ዜጎች አንገነዘብም።ምክንያቱም አሥቀድመው ከእውቀት እና ከጥበብ እንድንርቅ አድርገውናልና። ፈፅሞ በእነሱ ቁሥ እንድንማረክ እና እንድንሰግድላቸውም በማድረጋቸው የገዛ ሥልጣኒያችንን ኮፒ በማድረግ (“መፀሐፈ ሄኖክን ይጠቅሷል” )  እነሱ ገናና ሆነው እኛን ድንክ አድርገውናል።
   መላእክትም እንዳያገለግሉን ለእነሱ እንድንሠግድ አድርገውናል። በዚህ ሰበብም ዛሬም ፍቅር አጥተን ሰው ሆነን ሣለ እንደአውሬ እየተባላን ነው።
    ይህ እውነት በአፍሪካ ላለ ሰው ሁላ ካልተገለፀለት ዛሬም ከባርነት መውጣት አይችልም።የአፍሪካ መንግሥታትም ህዝብን ለማገልገል እንጂ በህዝብ ለመገልገል ያሰፈሰፉ ከርሳሞች እንዳይሆኑ  ህዝቡ ፍቅር ኖሮት በጋራ ካልታገለ የሚመኘውን ብልፅግና አያገኝም።
     የየመንግሥታቱ ተቋማት የሚመሩ ባለሥልጣና እና አገልጋዮች፣ ዛሬ ወይም ነገ፣ እንደሚሞቱ እና ከሆድ የዘለለ ዘመን ተሻጋሪ  ታሪክ ሠርተው ማለፍ እንደሚገባቸውእና የህዝቡም ፍላጎት ይኸው መሆኑን ካልተረዱ ፣ ሌብነትን እርግፍ አርገው ትተው ለህዝባቸው አርአያ ካልሆኑ (አሜሪካ እና አውሮፓ ልጆቻቸውን ከማሥተማር ፣ከማሳከም፣የወሊድ አገልግሎት እንዲያገኙ ከማድረግ አልፈው ቤት ገዝተው የሚኖሩ አሉና…)   እና በፍቅር እሥካልተገዙ ጊዜ ድረሥ መላአክቶች ቀርበው ሀገራቸውን እና ህዝባቸውን ሊያገለግሏቸው ከቶም  አይችሉም።…

2 Comments

  1. ውድ መኮንን፣
    መልካም ብለሃል፣ እስካሁን ብዙ ኮሜንቶች አለመምጣታቸው በጣም ገርሞኛል:: ከታች ያስቀመጥኩትን የአባባልህ ጥቅስን ሳነብ፣ እኔንም ጭምር እና እንዲሁም ብዙ ሌሎችን ሲሰርቁ እጅበእጅ እንደተያዙ አይነት ነገር ሆኖ ተሰማኝ:: ለማንኛውም ብርታቱን ይስጥህ፣ ቀጥልበት::

    “ለዚህ ውጥናቸው ሥኬትም፣ለሆዳቸው ያደሩ የገዛ ሀገራቸውን በዶላር የማሸጡ ተባባሪ አያጡም። አልበዘበዝም ባለችው ሀገር እነዚህን የተማሩ ሰዎች አሠልጥነው ያሰማራሉ።”

  2. ዉድ መኮንን or dawit

    “የበለፀጉት ሀገሮች አፍሪካን የበለጠ ደሃ ለማድረግ” የምጥሩት የቅኝ ገዥዎች መሠረታዊ ባህርይ ስላላቸዉ ነዉ። ይህም የተገዥዉን ሕዝብ ሀብት መዝረፍ ነዉ። ታስተዉል እንደሆን በአገራችንም የአማራ ቅኝ ገዢዎች እነሆ እስከዛሬ ድረስ የኦሮሞንና የደቡቡን ሕዝብ እስክነሥጋዉ ካልበላን ብለዉ እያተራመሱ ነዉ። ያንተዉ ሰዉ እንደዚህ እያደረገን የፈረንጁ ለምን ይደንቃል?እናትህ አፈር ድሜ ትግጥና!

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share