አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ በተለይ ለDW በሰጡት ቃለ ምልልስ ዶክተር አብይ ስልጣን እንደያዙ የፖለቲካ ምህዳሩ መስፋት ቢጀምርም በየክልሉ ያሉ የኢህአዴግ አባላት ከቀደመው ሥርዓት በከፋ መልኩ ሙሉ ለሙሉ የፖለቲካ ምህዳሩን እንደዘጉት ይፋ አድርገዋል::የዜግነት ፖለቲካ አራማጅ ድርጅቶችን በጠላትነት ፈርጀው እንቅስቃሴያቸውን ገድበዋል ሲሉም ተናግረዋል።
የኢትዮጵያ መንግሥት ካለው ጉልበት በላይ በፌደራሊዝም ሥርዓት ስም የራሳቸውን የደህንነት መዋቅር ወታደራዊ ኃይል እና በዘር ላይ የተመሰረተ ሚድያ ያደራጁ የክልል አስተዳደሮች በዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታው ላይ ትልቅ ማነቆ መፍጠራቸውን የአርበኞች ግንቦት 7 ከፍተኛ አመራር አስታወቁ:: የድርጅቱ ዋና ጸሃፊ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ በተለይ ለ DW በሰጡት ቃለ ምልልስ ዶክተር አብይ ስልጣን እንደያዙ የፖለቲካ ምህዳሩ መስፋት ቢጀምርም በየክልሉ የሚገኙ የኢህአዴግ አባላት ከቀደመው ሥርዓት በከፋ መልኩ ሙሉ ለሙሉ የፖለቲካ ምህዳሩን እንደዘጉት ይፋ አድርገዋል:: እነዚህ አባላት የዜግነት ፖለቲካ አራማጅ ድርጅቶችን በጠላትነት ፈርጀው እንቅስቃሴያቸውን ገድበዋል ሲሉም ተናግረዋል። በዚህ የተነሳም የሕብረተሰቡም ሆነ የአገሪቱ ህልውና በአሁኑ ወቅት ከመቼውም ጊዜ በላይ ከፍተኛ አደጋ እና ስጋት ውስጥ ወድቋልም ብለዋል:: ዝርዝሩን እንዳልካቸው ፈቃደ አጠናቅሮታል::
እንዳልካቸው ፈቃደ
ኂሩት መለሰ
እሸቴ በቀለ
DW